TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት በምክር ቤቱ ተገኝተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ። @tikvahethiopia
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

ኡስታዝ ከሚል ሸምሱ ፦

" እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ሀገራችን ከሌሎች ሀገራት ያላትን ዲፕሎማሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለማሻሻል እና ዲፕሎማሲውም የሀገራትን የጋራ ጥቅም ያስጠበቀ እንዲሁም የሀገሩን ክብር እና ሉዓላዊነት በጠበቀ መልኩ እንዲጎለበት ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።

ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሀገራትን የፖለቲካ አስተላለፍ በመከተል ወዳጅ የነበሩ ሀገራት ጎራቸውን የቀየሩበት ሁኔታዎች ይስተዋላሉ።

እንደማያሳያም በርካታ ዜጎች በተለያዩ ሀገራት ለእስር ተዳርገው ለአላስፈላጊ እንግልት እና ስቃይ እንዲሁም ለሞት እየተዳረጉ ይገኛሉ ለምሳሌ በሳዑዲ አረቢያ ፣ እንዲሁም በኤምሬት አንዳንድ ቦታዎች ያለው ችግር መጥቀስ ይቻላል።

እንዘህ ዜጎች ከእስር ተፈተው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ በመንግስት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም በምብ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ቢገለፅልን "

@tikvahethiopia