TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች ጋር በመሆን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ተርባይን ኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ስነ ስርዓት ላይ።

ፎቶ ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች ጋር በመሆን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ተርባይን ኃይል ማመንጨት ማብሰሪያ ስነ ስርዓት ላይ። ፎቶ ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት በይፋ ሲያስጀምሩ ባሰሙት ንግግር " ኢትዮጵያ ማንንም የመጉዳት ፍላጎት የላትም፤ ፍላጎቷም ኤሌክትሪክ አይተው የማያውቁ ዜጎቿን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ነው " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ " ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንድነታችን፣ የመነሳታችን፣ የማደጋችን እና የአይበገሬነታችን ምልክት ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

ግድቡ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ከጨለማ እና ከድህነት መውጫ ድልድይ ሆኖ በማገልገል ረገድ ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ እንደሆነም ገልጸዋል።

ግድቡ ኃይል የማመንጨት ስራውን መጀመር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለታችኛው ተፋሰስ አገራትም ጭምር ታላቅ የምሥራች ነው ብለዋል። ግድቡ የሚያመነጨውን ኃይል ከጎረቤት አገራት ባለፈ አፍሪካን ለማስተሳሰር ጉልህ ሚና እንዳለውም ገልፀዋል።

" ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውሃ ሃብት ያላት አገር እንደመሆኗ መጠን በርካታ ግድቦችን በመገንባት ሃይል የማምረት እና የመሸጥ እምቅ አቅም አላት " ያሉት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ " የበለጸጉ አገራት አሁን ያለውን የውሃ ፖለቲካ መልክ በመቀየር በመስኩ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መስራት እንዳለባቸው ጠቅሰው፤ በዚህም በርካታ አገራትን ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል " ብለዋል፡፡

#ENA

@tikvahethiopia
ግብፅ እና ሱዳን ስለ ዓባይ ኃይል ማመንጨት ምን አሉ ?

በዓባይ ወንዝ ላይ የተገነባውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመርን ተከትሎ ግብፅ እና ሱዳን ተቃውሞ አሰምተዋል።

የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ እንዳሉት የኢትዮጵያ አካሄድ ግብጽ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2015 በካርቱም ያደረጉትን የመርህ ስምምነት የሚጥስ ነው ብለዋል።

በሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዳሴ ግድብ ተወካይ አምባሳደር ኦማር አልፋሩቅ ግድቡ ሀይል ማመንጨቱ 3ቱ ሀገራት የተናጥል እርምጃ እንዳይወስዱ በሚል የፈረሙትን የካርቱም ስምምነትን የሚጥስ እና ወዳጅነታቸውን የሚጎዳ ነው ሲሉ መናገራቸውን አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል።

ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በግድቡ ኃይል ማመንጨት ጅማሮ ማብሰሪያ ስነስርዓት ላይ " የግድቡ ሀይል ማመንጨት መጀመር ለአህጉራችን እንዲሁም አብረናቸው ሰርተን በጋራ ለመጠቀም ለምንሻ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የምሥራች ነው። ዐባይ ወንዛችንን ሀገራችንን አልምቶ ጎረቤቶቻችንን ሊያረሰርስ ጉዞውን ቀጥሏል " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ወንድም የሱዳን እና የግብጽ ህዝቦች ዛሬ የተጀመረው ኃይል የማመንጨት ስራ ለእናንተም በረከት ነው እና እንኳን ደስ አላችሁ ! " ሲሉም ተናግረዋል።

" ባልተገባ ሁኔታም ቢሆን ለፈጠራችሁት ተጽእኖ እና ፈተናም ለመሰግናችሁ እወዳለሁ ፤ መላው የዓለም ህዝብ እንዲገነዘብ የምፈልገው፤ ይህ ውሃ እንደምታዩት ኃይል እያመነጨ ወደ ሱዳን እና ግብጽ የሚሄደ እንጂ ፤ ሲነገር እንደነበረው ኢትዮጵያ ውሃውን ገድባ ወንድም የግብጽ እና የሱዳን ህዝብን የማስራብ እና የመስጠማት ፍላጎት እንደሌላት በተግባር ያሳየንበት ነው፤ ለዚህም ደስ ብሎናል " ሲሉ ነው ዶ/ር ዐቢይ የተደመጡት።

@tikvahethiopia
#GERD

" ግድቡን እኛ ሳንሆን እነሱ ናቸው የሚጠብቁት " - የቀድሞ የሀገራችን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ

@tikvahethiopia
#GERD

" ... በወንዞቻችን ለመጠቀም እና ድህነትን ለማስወገድ የምናደርገው ጥረት እራሳችንን እና ጎረቤቶቻችንን ጭምር ለመጥቀም እንጂ ማንንም ለመጉዳት እንዳልሆነ ለዓባይ ልጆች ሁሉ ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ " - የቀድሞ የሀገራችን ጠ/ሚ ሀኃይለማርያም ደሳለኝ

@tikvahethiopia
#GERD

" ... የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንጨርሰዋለን። የታላቁ ህዳሴ ግድብን የምንጨርሰው ልጆቻችንን መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስም እንደምንችል እንዲያውቁት ስለምንፈልግም ጭምር ነው " - የአሁኑ የሀገራችን ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ItsMyDam

የቀድሞ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ስመኘው በቀለ የተናገሩት ፦

" በዚህ ዘመን ላለነው ትውልድ አይደለም ለኢትዮጵያውያኖች ፣ ለትውልደ ኢትዮጵያውያኖች፣ በውጭ ለሚኖሩ ዜጎች ብቻ ሳይሆን ለመላው የዓለም ህዝብ የተለየ ልዩ መልዕክት እያስተላለፈ ያለ ፕሮጀክት ነው።

በአጠቃላይ ሀገራችንን በተለየ ገፅታ እንድትታይ (በበጎ መልኩ) ፣ በአጠቃላይ ትውልድ በስራ የሚያምን እንዲሆን ፣ በስራ የሚያምን ትውልድ ፣ በእራሱ የሚተማመን ትውልድ መፍጠር የቻለ ፕሮጀክት ነው።"

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አስተያየት ስጡበት ! የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህዝቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ምክር ቤቱ ዝርዝራቸውን ዛሬ ይፋ አድርጓል። በተለያዩ አግባቦች በተጠቆሙት 42 የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከዛሬ ጀምሮ የህዝብ አስተያየት ይሰበሰባል። ይህን 👉http://www.hopr.gov.et/am/web/guest/dialog-candidate ማስፈንጠሪያ በመጫን…
#Update

የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት የሚያገለግሉ የ11 ግለሰቦችን ሹመት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ አማካኝነት ለም/ቤቱ ከቀረቡ ተሿሚዎች መካከል፤ ኮሚሽኑን በሰብሳቢነት እንዲመሩ የታጩት ፕ/ር መስፍን አርአያ ናቸው።

ወ/ሮ ሂሩት ገ/ስላሴ ደግሞ የምክክር ኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሆኑ መመረጣቸውን ለፓርላማ አባላት በታደለ የተሿሚዎች ዝርዝር ላይ መስፈሩን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የተሿሚዎች ዝርዝር ፦

1ኛ. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ (ሰብሳቢ)
2ኛ. ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ (ምክትል ሰብሳቢ)
3ኛ. ዶ/ር አይሮሪት መሐመድ
4ኛ. ዶ/ር ተገኝወርቅ ጌቱ
5ኛ. ዶ/ር ዮናስ አዳዬ
6ኛ. ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ
7ኛ. አምባሳደር መሐመድ ድሪር
8ኛ. ወ/ሮ ብሌን ገብረመድህን
9ኛ. አቶ ዘገየ አስፋው
10ኛ. አቶ መላኩ ወልደማርያም
11ኛ. አቶ ሙልጌታ አጎ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ እያካሄደ ይገኛል። ምክር ቤቱ በስብሰባው የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት የሚያገለግሉ የ11 ግለሰቦችን ሹመት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። በአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ አማካኝነት ለም/ቤቱ ከቀረቡ ተሿሚዎች መካከል፤ ኮሚሽኑን በሰብሳቢነት እንዲመሩ የታጩት ፕ/ር መስፍን አርአያ ናቸው። ወ/ሮ ሂሩት ገ/ስላሴ ደግሞ…
#Update

የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮችን ሹመት በ5 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

በዚህ መሰረት ፦

1ኛ. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ (ሰብሳቢ)
2ኛ. ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ (ምክትል ሰብሳቢ)
3ኛ. ዶ/ር አይሮሪት መሐመድ
4ኛ. ዶ/ር ተገኝወርቅ ጌቱ
5ኛ. ዶ/ር ዮናስ አዳዬ
6ኛ. ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ
7ኛ. አምባሳደር መሐመድ ድሪር
8ኛ. ወ/ሮ ብሌን ገብረመድህን
9ኛ. አቶ ዘገየ አስፋው
10ኛ. አቶ መላኩ ወልደማርያም
11ኛ. አቶ ሙልጌታ አጎ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክርን በኮሚሽነርነት እንዲመሩ ተሹመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽንን የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮችን ሹመት በ5 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል። በዚህ መሰረት ፦ 1ኛ. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ (ሰብሳቢ) 2ኛ. ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ (ምክትል ሰብሳቢ) 3ኛ. ዶ/ር አይሮሪት መሐመድ 4ኛ. ዶ/ር ተገኝወርቅ ጌቱ 5ኛ. ዶ/ር ዮናስ አዳዬ 6ኛ. ዶ/ር አምባዬ ኦጋቶ 7ኛ. አምባሳደር…
ፕ/ር መሰፍን አርአያ ወልደተንሳይ ማናቸው ?

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ሹመት ዛሬ ፀድቋል። የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ደግሞ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ናቸው።

• በሕክምና የዶክተሬት ዲግሪ ( MD) ፣ ከፓቭሎቭ ዩኒቨርሲቲ ሩሲያ፤

• በሳይኮቴራፒ ፍልስፍና የፒኤች ዲ ዲግሪ (PhD)፣ ከኦማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰዊድን፤

• ስፔሻላይዝድ ድፕሎማ፤ በሳይኮሎጂካል ሜድስን እና ሳይካትሪ፣ ግሮኒጎኝ ዩኒቨርስቲ ኔዘርላንድስ፣

• በኤፒዲሞሎጂና ባዮስታትስቲክስ ሰርተፍኬት፤ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የሥራ ልምድ፤

• ለ6 ዓመታት በዓዲግራት በደሴ እና በአማኑኤል ሆስፒታሎች ሜዲካል ኦፊሰርና ዳይሬክተር፤

• ለ10 ዓመታት በአማኑኤል ሆስፒታል ሳይካትሪስት፤

• ለ6 ዓመታት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ፕሮቮስት፤

• ለ6 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይካትሪ ዲፓርትመንት ዲን፣

• ለ12 ዓመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ሆነው ፣ የዲፓርመንት ሃላፊ እና ልክቸረር ሆነው ካገለገሉ በኋላ ሙሉ የፕፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል።

• ለ11 ዓመታት የፌደራል ሆስፒታሎች አመራር ቦርድ አባል፤

• በአሁን ወቅት ከሙያዊ አገልግሎት በተጨማሪ በኢፌዴሪ የማንነትና የአስተዳር ወሰን ኮሚሽን አባል ሆነው ያገለግላሉ።

ምንጭ፦ የህ/ተ/ም/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፕ/ር መሰፍን አርአያ ወልደተንሳይ ማናቸው ? የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ሹመት ዛሬ ፀድቋል። የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት ደግሞ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ናቸው። • በሕክምና የዶክተሬት ዲግሪ ( MD) ፣ ከፓቭሎቭ ዩኒቨርሲቲ ሩሲያ፤ • በሳይኮቴራፒ ፍልስፍና የፒኤች ዲ ዲግሪ (PhD)፣ ከኦማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰዊድን፤ • ስፔሻላይዝድ ድፕሎማ፤ በሳይኮሎጂካል ሜድስን እና ሳይካትሪ፣…
ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ ኦዳ ማን ናቸው ?

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ወ/ሮ ሂሩት ገብረስላሴ ተሹመዋል።

• በህግ ሜትሪዝ ምሩቅ ሰርቦን ዩኒቨርሲቲ (ፈረንሳይ)

• ለ2 ዓመት በህግ እና ፍትህ ሚኒስቴር የህግ ተንታኝ ባለሞያ

• ለ2 ዓመት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር የአፍሪካ ህብረት የህግ ጥናት ኦፊሰር

• ለ2 ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ሌክቸረር

• ለ8 ዓመት በግል የንግድ ድርጅት ከፍተኛ የህግ አማካሪ

• ለ4 ዓመት በዓለም አቀፍ የንግድ አማካሪ በመሆን ለUN ፣ World Bank) ፣ OAU የጥናት እና የማማከር ስራ

• ለ6 ዓመታት የአፍሪካ የሴቶች የሰላምና ልማት ኮሚቴ ከፍተኛ ኦፊሰር

• ለ3 ዓመት በኦክስፋም አህጉራዊ የሰላም ግንባታ እና የግጭት አመራር አማካሪ

• 14 ዓመት በተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች የሰሩ፣ ለምዕራብ አፍሪካ እና ሳህል የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ ምክትል ወኪል ሆነው እያገለገሉ ያሉ

ምንጭ፦ የህ/ተ/ም/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጡረታ እንደሚወጡ ማሳወቃቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአዲስ አበባ ለሚገኘው ኤምባሲ አዲስ ሰው በተወካይነት በኃላፊነት ቦታ ላይ መድባለች። አሜሪካ በአዲስ አበባ ላለው ኤምባሲዋ ትሬሲ አን ጃኮብሰንን ነው በጊዜያዊነት በኃላፊነት ቦታ ላይ ያስቀመጠችው። አሜሪካዊቷ ዲፕሎማት ትሬሲ አን ጃኮብሰን በቱርክሜኒስታን፣ ታጂኪስታንና ኮሶቮ የአሜሪካ አምባሳደር…
ጊታ ፓሲ ተሰናበቱ።

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ጊታ ፓሲ ዛሬ አሰናበቱ።

አምባሳደሯ የሹመት ደብዳቤያቸውን ከአንድ ዓመት በፊት የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ማቅረባቸው እንደሚታወስ ከፕሬዚደንት ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጡረታ እንደሚወጡ ማሳወቃቸውን ተከትሎ አሜሪካ በአዲስ አበባ ለሚገኘው ኤምባሲዋ ትሬሲ አን ጃኮብስን በጊዜያዊነት በኃላፊነት ቦታ ላይ መመደቧ ይታወሳል።

@tikvahethiopia