TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Oromia, #WestGuji 📍 በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በሸኔ በመከበቡ ውሎ መግባት አስቸጋሪ መሆኑን አመለከቱ። ነዋሪዎች የታጣቂ ቡዱን በርካታ የወረዳውን ቀበሌዎችን መቆጣጠሩን በመግለፅ ሰዎች እንደሚገደሉ፣ ንብረትም እንደሚወድም እና እንደሚዘረፍ ገልፀዋል። ወረዳው ነዋሪ ፦ " ያለንበት ሁኔታ አሰቃቂ እና ተስፋ የሌለው ነው። በአሁን ጊዜ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ ነን።…
#GelanaWoreda

በገላና ወረዳ ታጣቂዎች በከፈቱት የተኩስ እሩምታ 3 ሰዎች ሲገደሉ ፣ 4 ሰዎች ቆሰሉ።

የአማሮ ልዩ ወረዳ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ ቤት ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጠው ቃል ፥ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን የፈጸሙት በጫኑት ሸቀጥ ላይ ሰዎችን አሳፍረው ከዲላ ከተማ ወደ አማሮ ኬሌ ሲጓዙ በነበሩ ኤፍ- ኤስ- አር የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ ነው።

ጥቃቱን ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ የደረሰ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ ውስጥ በተለምዶ የመከራ ዳገት በተባለ አካባቢ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ መቶ አለቃ ስላሴ ሽሎ ተናግረዋል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ሶስት ሰዎች የአንደኛው ተሽከርካሪ ሾፌር ፤ ረዳቱና አንድ መንገደኛ ሲሆኑ በሌላኛው ተሽከርካሪ ላይ የነበሩ አራት ሰዎች ደግሞ በጥይት ተመተው መቁሰላቸውን ገልፀዋል።

3ቱም ተሽከርካሪዎች ከዲላ በተነሱበት ወቅት በያዙት ጭነት ላይ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችን ጭነው እንደነበረ የጠቀሱት ሃላፊው ታጣቂዎቹ መተኮስ እንደጀመሩ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ከተሽከርካሪዎቹ ላይ በመዝለል ወደ ጫካ መሸሻቸውንና አስከአሁንም ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ አስረድተዋል።

ጥቃት ፈፃሚዎች ታጣቂዎቹ በመንገደኞቹ ላይ ካደረሱት ግድያ በተጨማሪ ንብረትነቻው የግለሰብ ነጋዴዎች የሆኑና በተሽከርካሪዎቹ ተጭነው የነበሩ ልዩ ልዩ ሸቀጣሸቀጦችንም ሙሉ በሙሉ መዘረፉቸውንም ተናግረዋል ።

በአሁኑ ወቅት የ3ቱን ሰዎች አስክሬን ወደ አማሮ ኬሌ ከተማ በማምጣት ዛሬ ቀትር የቀብር ሥነስረዓታቸው መከናወኑን የገለፁት የመቶ አለቃ ስላሴ የቆሰሉ ሰዎች ደግሞ በህክምና ተቋም ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ ሊመረቅ ነው። ባንኩ ፥ " ከምስራቅ አፍሪካ ረጅሙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ የዋና መ/ቤት ህንፃ ምርቃት ከባንኩ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ጋር ገጥሟል፡ " ብሏል። በትክክል የሚመረቅበት ቀን ይፋ ይሆንም በቅርቡ ግን ህንፃው እንደሚመረቅ ተገልጿል። @tikvahethiopia
#Update

ግዙፉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንፃ እሁድ ይመረቃል።

80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና የአዲሱን ዋና መ/ቤት ምርቃት በዓሉን አስመልክተው የባንኩ ፕሬዚዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ መግለጫ ሰጥተዋል።

መግለጫቸው ህንፃው የፊታችን እሁድ ዕለት ይመረቃል ብለዋል።

በሌላ በኩል እ.ኤ.አ በ1942 በ1 ሚሊዮን የማሪያትሬዛ ካፒታል ሥራውን የጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ጊዜ ፦
• 824 ቢሊዮን ብር የተቀማጭ ገንዘብ ፣
• 1.1 ትሪሊዮን ብር ጠቅላላ ሀብት ፣
• ከ1 ሺህ 800 በላይ ቅርንጫፎች
• ከ34 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንዳሉት አቶ አቤ ሳኖ በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Amhara , #SouthGondar📍

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በዞኑ እስረኞችን ለማስፈታት የሞከሩ 16 ሰዎች መገደላቸውን አስታወቀ።

ዞኑ ይህን ያሳወቀው ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ነው።

የዞን ም/አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ ለሬድዮ ጣቢያው ፥ " ትናንት ሌሊት 8 ሰዓት ሲሆን ነፋስ መውጫ ማረሚያ ቤትና ሌሎች ሁለት ፖሊስ ጣቢያዎች እስረኛ ለማስፈታት ከሞከሩት ዘራፊ ካሏቸው ታጣቂዎች መካከል 16ቱ ሲገደሉ 20 ተማርከዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከመንግስት በኩል ሶስት የፀጥታ አካላት መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።

አቶ ጥላሁን ፤ " ዘራፊ " ያሏቸው አካላት ከተለያዩ አጎራባች ዞኖች የተሰባሰቡ ነበሩ ብለዋል።

ከማረሚያ ቤት ወጥተው ከነበሩት ታራሚዎች መካከል 65ቱ በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳና በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንት ወረዳ በተውጣጡ ጥምር የፀጥታ አካላት ቅንጅት በያሉበት ተይዘው መመለሳቸውንም አቶ ጥላሁን አመልክተዋል።

ዛሬ የባህር ዳር - ወልዲያ መስመር ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ እንደነበር እና ታጣቂዎቹ በሶስት ተለያዩ መኪናዎች የመጡ እንደነበሩ፤ ተሸከርካሪዎቹም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ የሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Oromia , #KelemWolega📍

በአንድ አይነት ጉዳይ የመንግስት ባለስልጣናት የሚናገሩት 🤔

በተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች እጅግ በተደጋጋሚ በሚፈፀም ጥቃት በርካቶች እንደሚገደሉ፣ እንደሚጎዱ ፣ ከቤት ንብረታቸው እንደሚፈናቀሉ በተደጋጋሚ ሲገለፅ የነበረ ጉዳይ ነው።

ይህ የፀጥታ ችግር ሰሞነኛ ሳይሆን አመታትን የዘለቀ ዘላቂ መፍትሄም የሚሰጠው አካል ያላገኘ፣ የዜጎችን እምባ ማበስ ያልተቻለበት፣ አጥፊዎችን እንኳን ተለይተው ሊጠየቁ ያልተቻለበት ነው።

በተደጋጋሚ በወለጋ ጉዳይ መረጃ ተለዋውጠናል።

አካባቢው ተደራሽ ባለመሆኑ ፣ የትኛውም ሚዲያዎች ፣ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች በአካል ሊደርሱበት ስለማይችሉ መሬት ላይ እንኳ ምን እየሆነ እንዳለ በትክክል ማወቅ አዳጋች ነው።

የአካባቢው ችግር ሰሞነኛ መነጋገሪያ ሆኖ አጀንዳ ተደርጎ ይታለፋል፤ በዜጎች ስቃይ እና እምባ የዩትዩብ ገንዝብ ይሰራል ፤ በፀጥታ ችግር ግን የዜጎች ስቃይ ይቀጥላል።

የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የተቀመጠው መንግስት በተደጋጋሚ ችግሩን እንደሚፈታ ሲናገር ቢቆይም አመታት አልፈዋል ችግሩ ቀጥሏል።

ከሰሞኑን ደግሞ ከቄለም ወለጋ ጋር በተያያዘ ማህበራዊ ሚዲያው አጀንዳ የሆነ ጉዳይ አለ። በጉዳዩ ዙሪያ ላይ ግን በመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡት አስተያየቶች የሚጣጣሙ ሆነው አልተገኙም።

እኛም ኢሰመኮን ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ያውቀው እንደሆነ ጠይቀናል።

የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳደር ተወካይ እና የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሣ በሻ ለኢፕድ ፦

" ... በጊዳሚ ወረዳ አሸባሪው ሸኔ ዘግናኝ ግድያዎችን እና የንብረት ውድመት ፈጽሟል።

በወረዳው በተለያዩ ቦታዎች 81 ሰዎችን እንዲሁም በጅምላ ተገድለው አስከሬናቸው አንድ ቦታ የተገኙ 87 ሰዎችን በድምሩ168 ንጹሐን ተገድለዋል። "

የቄለም ወለጋ ዞን የፀጥታ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ ለዶቼ ቨለ ፦

" ትላንትና ተለቆ ነበረ መረጃ ፤ እኛ በዞናችን ደረጃ ጅምላ ጭፍጨፋ ተካሂዷል የተባለው እኛ እንደምናውቀው 87 ሰው በሸኔ ታግቶ ጫካ እንዳለ ነው። ሁለት ወር በላይ ወረዳው በሸኔ ተይዞ ነበር ከታገቱት ውስጥ የኛ አመራር ፣ የወረዳው የካቢኔ አባላት እና የፀጥታ አካል ፣ ከህብረተሰቡን የቀበሌ አመራሮች ሸኔ አግቶ ወደ ጫካ ወስዷል።

ወደ ጫካ የወሰዳቸውን ሰዎች የጅምላ ጭፍጨፋ ተካሂዷል የሚል ወሬ ሰምቼ ነበር ፤ በእርግጥ ሰዎቹ መሞታቸው እና አለመሞታቸው ግና እያጣራን ፤ስለሆነ ትላንት የተላለፈው መረጃ ያልተጣራ ነው።

ገና የፀጥታ አካል በኮሚቴ ያ ኢንፎርሜሽን ልክ ነው ወይስ ልክ አይደለም ብሎ ቦታውን እንደርሳለን ብለን ኮሚቴ አዋቅረን ያ ኢንፎርሜሽን የተገኘ ሰውዬ ጋር እየተገናኘን ነው።

የታገቱት የኛ ካቢኔ፣ የፀጥታ አካላት ፣ ምሊሻ ፣ ልዩ ኃይል ፣ መደበኛ ፖሊስ ናቸው። እስካሁን አልተገኙም እያጣራን ስለሆነ ካጣራን በኃላ የት እንደሆነና ስንት ሰው እንደሆነ የሞተው መረጃ እንሰጣለን እንጂ ሰዎቹ ሞተዋል ጅምላ ጭፍጨፋ ተካሂዷል የሚባለው በተጨባጭ የተገኘ ሳይሆን በኢንፎርሜሽን ስለሆነ ኢንፎርሜሽኑን ደግሞ ገና እያጣራን ነው።

አስክሬን እስካሁን አልተገኘም። ገና ትክክል ነው አይደለም የሚለውን ኢንፎርሜሽኑን ከሰጠው ሰውዬ ጋር ሰውዬውን ወስደን ኮሚቴ አዋቅረን እዛው ቦታ ላይ ደርሰን እውነት መሆኑና አለመሆኑ ይረጋገጣል እንጂ አሁን በኢንፎርሜሽን ደረጃ የወረዳ ካቢኔ፣ የፀጥታ አካል የታገቱት ሞተዋል የሚለውን በወሬ ደረጃ ሰማን እንጂ ትክክለኛ መሆኑን መጨረሻ ላይ አልደረስንም።

የወረዳው አስተዳዳሪዎች፣ እና የፀጥታ ኃይሎች ታግተው መወሰዳቸውን ከታጋቾቹ ውስጥ አምልጦ ከወጣ ሰው አረጋግጠናል።

አጋቹ ያው ኦነግ ሸኔ ወረዳውን ይዞ ነበር አሁን ግን ነፃ ወጥቷል አሁን እኛ ነን እዚህ ያለነው። በእኛ እጅ ነው ወረዳው ያለው። የኛ መዋቅር ወደቦታው ተመልሶ ስራ ውስጥ ገብቷል። ግን ከአንድ ወር ሁለት ወር በላይ በእነሱ እጅ ነበር።

አንድ ሰው ሞቷል ሁለት ሰው ሞቷል ብለን ለመስራት ገና የሚጣራ ጉዳይ ነው። እስከሁን የሞተ ሰው ያየነው የለም።

ጫካ ለጫካ እያሰስን ነው ኦፕሬሽኑ እየተካሄደ ነው ለዚህ ኦፕሬሽን የመጣው ሰራዊት ሰዎቹ መሞታቸው እና መኖራቸውን እስኪያሳውቀን እየጠበቅን ነው፤ እየፈለግን ነው። "

ኢሰመኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦

" ባለው የፀጥታ ችግር አባላቶቻችንን እንኳን ለማሰማራት እና በአካባቢው ምን እየተካሄደ እንዳለ የተጣራ መረጃ ለማግኘት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ነው ያሉት።

የመንግስት ሚዲያ ዘገባዎችን ትክክል ናቸው ስህተት ናቸው የሚለውን ለማረጋገጥ መሬት ላይ ስላለው ሁኔታ ተጨባጭ መረጃ ስለሌለን አሁን ምንም ልንላችሁ አንችልም።

ነገር ግን በአካባቢው ባለው ግጭት የተለያዩ ጉዳቶች እየደረሱ እንደሆነ እኛም እንደ ሌላው ዜጋ ከምንሰማቸው መረጃዎችን የምንረዳው ነገር አለ። specifically ግን እንዲህ ያለ ሰው ላይ እንዲህ ያለ ጉዳት ደርሷል የሚል ነገር ለማስተባበልም ሆነ ለማረጋገጥ የተጨበጠ ነገር የለንም።

ሁኔታዎች እስከፈቀዱ ድረስ ችግሮች ያሉባቸው እና የኛን Mandate የሚመለከት ጉዳዮችን መርምረን ያለውን እውነታ ለማሳወቅ ዝግጁ ነን። ግን መሬት ያለው ሁኔታ መፍቀድ አለበት። "

@tikvahethiopia
#Amhara , #WestGondar 📍

በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ " ዲቢኮ ቀበሌ " የ6 ዓመት ህፃን ያገቱ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ገለፀ።

የወረዳው የፀረሽምቅ ጋንታ አመራር ሃምሳ አለቃ ባየ ደጉ ሰው የማገት መረጃው ከደረሰን በኋላ ከዲቢኮ የጸጥታ አካላት እንዲሁም ከማህበረሰቡ ጋር ቅንጅት በመፍጠር በተደረገው አፕሬሽን የማገት ወንጀሉን የፈፀሙ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን ገልፀዋል።

ሃምሳ አለቃ ባየ ድርጊቱ የሚወገዝ መሆንና ማህበረሰቡ በንቃት አካባቢውንና ቤተሰቡን መጠበቅ ውይይቶችን በማድረግ ችግሮች ሲኖሩ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የጸጥታ ስራ መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ማህበረሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር እና ምላሽ ምስጋና አቅርበዋል።

መረጃውን ያጋራው የመተማ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ሲሆን የፍርድ ሂደቱን በመከታተል ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ኦባሳንጆ ኮምቦልቻ ገብተዋል። የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕከተኛ ኦሊሴንጎን አባሳንጆ ዛሬ ኮምቦልቻ ገብተዋል። በትላንትናው ዕለት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዴኦዬ ፤ የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲቋጭ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን በመግለፅ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ በአማራ እና በአፋር ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ…
#Afar, #Semera📍

ከትላንት በስቲያ ሰኞ በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ ጉብኝት ያደረጉት የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ አፋር ክልል ሰመራ ገብተዋል።

ኦባሳንጆ ሰመራ ሲደርሱ የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አወል አርባ ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች በሰመራ ሱልጣን አሊ ሚራህ ሀንፈሬ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የተመድ ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ ሰመራ መግባታቸውን ከአፋር ክልል ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን አስተዳደር በአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች በኩል፣ በዞኑ ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ተገልጿል።

በዞኑ አስተዳደርና በታጣቂዎች መካካል የሚደረገው ንግግር " ጥሩ ደረጃ " ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ያሏቸውን ጥያቄዎች በሽማግሌዎች በኩል በደብዳቤ አቅርበው ሁለቱም አካላት በተነሱ አጀንዳዎች ላይ መስማማታቸው ታውቋል፡፡

በቅርቡ አዳዲስ አመራሮች የተሾሙለት ካማሺ ዞን፣ አዲሶቹ አመራሮች ያዋቀሯቸው የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ወደ የሚገኙበት ያሶ ወረዳ ሄደው ታጣቂዎቹን ማነጋገራቸው ተገልጿል፡፡

ከዞኑ አስተደዳር የተላኩት እነዚህ ልዑካን ከታጣቂዎች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ፣ በታጣቂዎቹ በኩል የተወከሉ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችን ይዘው ወደ ካማሺ ከተማ መመለሳቸው ተሰምቷል፡፡

በሁለቱም በኩል ያሉ ልዑካን ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ይዘው የመጡትን የውይይት ሪፖርት በተመለከተ፣ ከዞኑ አመራሮች እንዲሁም በዞኑ ከሚገኙና ከክልሉ የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ጻፊዮ ፤ ከውይይቱ በኋላ በሁለቱም ወገን ያሉ ሽማግሌዎች ተመልሰው ወደ ታጣቂዎቹ ዘንድ መሄዳቸውን አስረድተዋል፡፡

በካማሺ በተደረገው ውይይት ላይ ታጣቂዎቹ ለሰላም ፍላጎት እንዳላቸው በሽማግሌዎቹ በኩል መግለጻቸውን የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው፣ ታጣቂዎቹም ሆነ የክልሉ መንግሥት ባሏቸው አጀንዳዎች ላይ መግባባት እንዳለ ገልጸዋል፡፡

የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባን ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-02-09

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍 የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የካማሺ ዞን አስተዳደር በአገር ሽማግሌዎችና በሃይማኖት አባቶች በኩል፣ በዞኑ ከሚገኙ ታጣቂዎች ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ተገልጿል። በዞኑ አስተዳደርና በታጣቂዎች መካካል የሚደረገው ንግግር " ጥሩ ደረጃ " ላይ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፣ ታጣቂዎቹ ያሏቸውን ጥያቄዎች በሽማግሌዎች በኩል በደብዳቤ አቅርበው ሁለቱም አካላት በተነሱ አጀንዳዎች…
#BenishangulGumuz , #Kamashi📍

የካማሺ ዞን ታጣቂዎች ያናሷቸው ጥያቄዎች ምንድናቸው ?

የካማሺ ዞን ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ኮሎኔል ዓለሙ በሽር  ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደተናገሩት ታጣቂዎቹ በእስር ላይ ያሉ አባሎቻቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የዞኑ አስተዳደሮች ይሄ ጥያቄ በዞኑ የሚመለስ እንዳልሆነ አስረድተው፣ በጉዳዩ ላይ ከበላይ አካላት ጋር ንግግር በማድረግ መልስ እንደሚሰጡ አሳውቀዋል።

ሌላው በመተከል ዞን የሚገኙና ከክልሉ ውጪ ያሉ የፀጥታ ኃይሎች እንዲወጡ ታጣቂዎቹ ጠይቀዋል።

ኮሎኔል ዓለሙ በሽር ፥ " የሌሎቹን አላውቅም፤ የፌዴራል ፖሊስ እና መከላከያ ሠራዊትን ግን ማስወጣት አይችሉም፣ ይኼ አይመለስላቸውም እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።

በተጨማሪም ታጣቂዎቹ " በክልሉ ውስጥ ድርሻ ይኑረን " የሚል ጥያቄም አንስተዋል።

የካማሺ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ጻፊዮ ፤ ታጣቂዎቹ ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ በካማሺ ዞን ደረጃ ሚስተናገዱትን እንደሚመለሱ በክልል ወይም በፌዴራል ደረጃ የሚመለሰውን ደግሞ የዞኑ አስተዳደር ለበላይ አካላት እንደሚያስታውቅ ስምምነት ላይ መደረሱን ለጋዜጣው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar, #Semera📍 ከትላንት በስቲያ ሰኞ በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ ጉብኝት ያደረጉት የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ አፋር ክልል ሰመራ ገብተዋል። ኦባሳንጆ ሰመራ ሲደርሱ የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አወል አርባ ፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች በሰመራ ሱልጣን አሊ ሚራህ ሀንፈሬ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል…
#Update

ዛሬ ጥዋት ላይ አፋር የገባው በፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና በተመድ ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድ የተመራው ልዑክ ከአፋር ክልላዊ መንግስት ፕሬዜዳንት አቶ አወል አርባ ጋር ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ፕሬዜዳንት አወል አርባ አሁን ላይ በክልሉ ስላለው ተጨባጭ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በተጨማሪ ልዑኩ በክልሉ ላይ እንደአዲስ በተከፈተው ጦርነት በኪልበቲ ረሱ ዞን በከባድ መሳሪያ ድብደባ ጉዳት የደረሰባቸውን ህፃናት በዱብቲ ሆስፒታል ተገኝቶ ተመልክቷል።

በአፋር ክልል ላይ በተከፈተው አዲስ ጦርነት ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰ መሆኑና በጦርነቱ ከ300 ሺህ በላይ የአፋር ክልል ነዋሪዎች ከገዛ ቄያቸው መፈናቀላቸው ሪፖርት መደረጉ ይታወቃል።

ፎቶ ፦ የአፋር ክልል መንግስት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር) ፦ • የፈተና መሰረቅ ከግለሰብ ይልቅ ተቋማዊ እየሆነ በመምጣቱ ፤ በአጠቃላይ የደረሰብን የሞራል ክስረት ከፍተኛ ነው። • የእኔ ክልል ተማሪዎች ማለፍ አለባቸው በሚል በተቋም ደረጃ የፈተና ወረቀቶችን በመስረቅና መልስ በመስጠት ጭምር ተባባሪ የሆኑ አመራሮች መኖራቸው የትምህርት ሲስተሙ ጥራት ተዓማኒነት ከፍተኛ ጥያቄ ዉስጥ ገብቷል። • ግማሹ ለፍቶ…
የብሄራዊ ፈተና ጉዳይ ?

በትምህርት ሚኒስቴር የዕቅድ እና ሀብት ማፈላለግ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ግርማ ፦

" የአገር አቀፍ ፈተናው በቴክኖሎጂ ተደግፎ በኦንላይን ሥርዓት ታግዞ ካልተሰጠ የምዘናው ሥርዓት አደጋ ውስጥ ነው "

የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ፦

" የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዘና ጉዳይ የሚመለከታቸው ተቋማትን ብቻ ሳይሆን መንግሥትንም የፈተነ ነው።

የፀጥታ ችግር ፈተናውን ለመስጠት አዳጋች ካደረጉት ጉዳዮች ተጠቃሹ ሲሆን፣ ከሰሞኑ በሁለተኛ ዙር በተሰጠው የ2013 ዓ.ም. አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና እንኳን 150 የሚደርሱ ተማሪዎችን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ወስዶ ለመፈተን ከ100 በላይ የፀጥታ ኃይል ባልደረባ እጀባ አስፈልጎ ነበር።

በዚህ የተነሳ አገር አቀፍ ሁለተኛ ደረጃ ፈተናን የመስጠት ሥራ ከኤጀንሲው አቅም በላይ ለመንግሥትም ፈተና ሆኗል።

አገራዊ ፈተናው የሚሰጥበት ዋና ዓላማ፣ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ አንዱ መሣሪያና የብቁ ዜጋ ማፍሪያ መለኪያነቱን ታሳቢ በማድረግ ቢሆንም፣ በዚህ ወቅት ከዚህ ዓላማ ውጪ መስመሩን ስቶ ራሱን የቻለ ትልቅ ፈተና ሆኗል።

በሌላ በኩል ፈተናው ፖለቲካዊ ይዘትን እየተላበሰ መጥቷል። አገርን በሚገነባ ዕሳቤ ሳይሆን፣ " ከእኔ ክልል ይህን ያህል አለፈ " ወደሚል ጤናማ ያልሆነ ውድድር ውስጥ እንደተገባ ነው።

ከኤጀንሲው አቅም በላይ የሆነውን ይህንን ችግር መንግሥት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። በተለይ ከላይ የተነሱትን ችግሮች ለመፍታት ብቸኛው መንገድ፣ ፈተናውን በዲጂታል መንገድ በኦንላይን መስጠት ነው "

[ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተናግሩት - ሪፖርተር ]

@tikvahethiopia
#AnbesaCityBus

አንበሳ የከተማ አውቶብስ እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጀ እንደሚገኝ አስታወቀ።

ድርጅቱ እስከ የለሊት አገልግሎትን ለመስጠት ተገልጋዮች የሚበዙባቸውን የአዲስ አበባ አካባቢዎች የመለየት ስራ እያከናወነ ሲሆን ጥናቱ ሲጠባቀቅ እስከ ምሽት 3 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡት አውቶብሶች እስከ ለሊት 6 ሰዓት ወደ ስራ እንደሚያስገባ ገልጿል።

የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ምስክር ማንደፍሮ፥ " አሁን እስከ 3 ሰዓት ብቻ ነው አገልግሎት የሚሰጡት ከዚህ በኃላ በምንጀምረው አዲስ አገልግሎት እስከ ለሊት አጋማሽ ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ የትኞቹ መስመሮች ለእንደዚህ አይነት ስራ ተጋላጭ ናቸው / የትኞቹ መስመሮች አምሽተው የሚሰሩ በዛ በምናስበው ሰዓት ከስራቸው የሚወጡ ማህበረሰቦች አሉ የሚለውን ጥናት እያደረግን ነው፤ ጥናቱን ከጨረስን በኃላ የተወሰኑ እንደ ዲሞንስትሬሽን የምንጀምረው አሰራር ይኖራል " ብለዋል።

አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት የቀኑን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት የአዲስ አበባ አስተዳደር ይገዛቸዋል የተባሉትን 3 ሺህ አውቶብሶች እየጠበቀ እንደሚገኝ እና አውቶብሶቹን እንደተረከበ በመጠሉ ችግሩን ለማቃለል እንሞክራለን ሲል አሳውቋል።

አሁን ላይ አምበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት 630 አውቶብሶች ያሉት ሲሆን በ125 መስመሮች በቀን ውስጥ እስከ 600 ሺ ያህል ሰዎችን እንደሚያጓጉዝ ገልጿል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

@tikvahethiopia