TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ለሳምንታት ተዘግቶ የቆየው የምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የኢንተርኔት አገልግሎት በዛሬው ዕለት መስራት ጀምሯል።

#አሰበ
#ሀረማያ
#ድሬዳዋ
#ጅግጅጋ
#ሀረር...እንዲሁም በሁሉም የምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል የምትገኙ ቤተሰቦቻችን እንኳን በደህና መጣችሁ! እንኳን በሰላም ተገናኘን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህቺ ከተማ ባለቤት የላትም?⬆️

#ሀረር ዛሬም በየቦታው በተከመሩ ቆሻሻዎች ውበቷ እንደጠፋ ነው። የከተማው አስተዳደር #ፍትሄ አልሰጠውም። ነዋሪዎች ዛሬም ምሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። ሰሚ ግን አልተገኘም!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀረር

የምሥራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የጸጥታ ምክር ቤት የምክክርና የሰላም መድረክ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ የአጎራባች ክልልች ተወካዮችና የጸጥታ አካላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀረር

በሐረር ከተማ #ከአራተኛ እስከ #ሐማሬሳ የጎዳና ላይ ጽዳት ዘመቻ ተካሄደ። በክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪነት በክልሉ የሚገኙ የጸጥታ ሀይሎች የሀገር መከላከያ፣ የክልሉ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የሚኒሻ አባላት፣ የማረሚያ ኮሚሽን፣ ቄሮ፣ ቀሬ፣ የክልሉ ወጣቶች እና የሀይማኖት አባቶች በጋራ በመሆን በዛሬው እለት ከጥዋቱ 12 ጀምሮ ከአራተኛ እስከ ሐማሬሳ የጎዳና ላይ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል። የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ እንደገለጸው ሐረር ከተማ ለነዋሪዎቻ ምቹ ከተማ እንድትሆን ብልሹ አመለካከትና አሰራርን ከክልሉ እናስወገድ በሚል መሪ ቃል የጽዳት ዘመቻው እንደተካሄደ ተገልጿል። ቢሮው እንደገለጸው በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ የጽዳት ዘመቻ እንደሚካሄድ ገልጾ የክልሉ ህብረተሰብ አካባቢውን ማጽዳት እንደሚጠበቅበት ገልጻል።

Via #AD
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሻሸመኔ
#ሀዋሳ
#ነቀምት
#አሰላ
#አዲስአበባ
#ሽሬ
#ደብረብርሃን
#ወላይታሶዶ
#አርባምንጭ
#ጅግጅጋ
#አዳማ
#ድሬዳዋ
#ባህርዳር
#መቐለ
#ሀረር
#ጎንደር

ከሌሎች በርካታ ከተሞች ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች የSAT ውጤት ያልጠበቁት እንደሆነ በመግለፅ ቅሬታቸው እያሰሙ ይገኛሉ። የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዶዶላ #ቢሾፍቱ #ሀረር

በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ትናንት እና ዛሬ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውን ታውቋል። ዛሬ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ትናንት ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር። በአካባቢው ከጠዋት ጀምሮ ሠልፍ እንደነበር የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከሰዓት በኋላ ግን ይህ ሠልፍ መልኩን መቀየሩን ይናገራሉ። ሁኔታው አስፈሪ ስለነበር ለሕይወታቸው የሰጉ ሰዎች በአካባቢው በምትገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው አንደሚገኙ ተናግረዋል። በሐረር ከተማ በትናንትናው ዕለት 3 ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ከነዋሪዎች ሰምቻለሁ ብሎ ዘግቧል። በቢሾፍቱ ከተማ ዛሬም በቀጠለው አለመረጋጋት የሰዎች ህይወት ማለፉን የቢሾፍቱ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ተናገርዋል። ዛሬ ከተማይቱ በተኩስ ስትናጥ እንደዋለች፣ በየቦታው መንገዶች ሲዘጉ እንደነበርና ወታደሮች መንገድ ለማስከፈት ሲንቀሳቀሱ መዋላቸውን ገልፀዋል። አመሻሹን ግን ሁኔታዎች ረገብ ብለዋል።

#BBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀረር

ጥቅምት 17/2012 ዓ/ም

ባለፈው ሳምንት በሐረር ከተማ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ዛሬም በከተማዋ የነበረው እንቅስቃሴ መቀዝቀዙን ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ክፍል ያናገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው የዋሉ ሲሆን ወደ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ተገልጋዮች ስለማይታዩ ጭር እንዳሉና አንዳንድ ሱቆችም ዝግ ሆነው ውለዋል።

በከተማዋ ያሉ መንገዶች እምብዛም ተሽከርካሪዎች ስለማይታዩባቸው ጭር ማለታቸውን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ የጸጥታ አካላትም በከተማዋ እየተዘዋወሩ ጥበቃ እያደረጉ እንደሆነም ተገልጿል።

በተጨማሪም ቀደም ካሉት ቀናት በተለየ የጸጥታ አካላት ስለትም ሆነ ዱላ ይዞ መንቀሳቀስን ከልክለዋል። እነዚህን ቁሶች ይዘው ከሚገኙ ሰዎች ላይ እንደሚቀሙ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሰልፍም ሆነ ግጭት እስካሁኗ ሰዓት ድረስ አለመከሰቱን ለማወቅ ተችሏል።

(BBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia