TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የ10ኛ ክፍል ውጤት⬇️

የ12 ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ እና የ10ኛ ክፍል ዉጤት ከነሐሴ 25 እስከ 30 ባሉት ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገልጿል፡፡

የ12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብን ለመወሰንም የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም መረጃ እያሰባሰቡ መሆኑን ነው የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን ደሳለኝ የገለጹት፡፡

የ10ኛ ክፍል ውጤትም የእርማት ስራው #መጠናቀቁን እና አሁን ላይ ስራውን የማጥራት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ነው ዶክተእ ዘሪሁን የተናገሩት። እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለጻ የ12 ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ እና የ10ኛ ክፍል ዉጤት ከነሐሴ 25 እስከ 30 ባሉት ቀናት ይፋ ይደረጋል፡፡

©አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሀገር አቀፍ ደረጃ በጋምቤላ ክልል የሚከበረውን የአለም የቱሪዝም ቀን ለማስተናገድ የሚደረገው ዝግጅት #መጠናቀቁን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል። በዓሉ “የዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር ለቱሪዝም ልማት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ እንደሚከበርም ተገጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምእራብ ሸዋ ዞን ኢሉ ገላን ወረዳ ‘’የገዳ መጫ” የኢሬቻ በዓልን ለማክበር ዝግጅቱ #መጠናቀቁን የወረዳው  የባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የፊታችን #እሁድ በሚከበረው በዓል ከኦሮሚያ ክልል 10 ዞኖች የተውጣጡ አባገዳዎችና ሌሎች እንግዶች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡ በዓሉ #ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ከወረዳውና ከኢጃጂ ከተማ የተመለመሉ ፎሌዎችና ቄሮዎች ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ተገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትምህርት ሚኒስቴር...

የትምህርት #ፍኖተ_ካርታ መተግበሪያ መርሃግብር ዝግጅት #መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ተማሪዎችን በመልካም ስነ-ምግባር የታነፁ እንዲሆኑ ከማስቻል ባለፈ ተማሪ ተኮር የሆነ የትምህርት ስርዓት ለመዘርጋትና ለመተግበር የተደገፈ የምዘና፣ የፈተና እና አጠቃላይ የጥራት ተገቢነት ማረጋገጫ ስርዓቱ የዜጎችን የዕውቀት፣ የክህሎት የአመለካከት ችሎታን #መመዘን የሚያስችል እንዲሆን ያግዛል፡፡

በቴክኖሎጂ የታገዘ ውጤታማ ስርዓት ለመገንባት ያስችላል የተባለውን የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ለመተግበር ከ9ኙ ክልሎች፣ ዞንና ከተማ
አስተዳደሮች መተግበሪያዎች ተዘጋጅቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የትምህርት ስርዓቱን ለማጠናከር መስራት እንደሚገባውና ለአርብቶ አደር አካባቢዎች ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው የትምህርት ሚኒስቴርን የ2011 በጀት ግምገማ አድርጓል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር 21 ደረሰ‼️

በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኝ ባለ አምስት ኮከቡ ዱሲት ዲ2 ሆቴልና የንግድ ማዕከል ባሳለፍነው ማክሰኞ #በታጠቁ_ኃይሎች በተፈጸመው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 21 ደርሷል።

ጥቃቱ ከተከፈተበት ቅንጡ ሆቴልና የገበያ ማዕከል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳት ሳይደርስባቸው የወጡ ሲሆን 28 ሰዎች ቆስለዋል። የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበር እንዳስታወቀው 19 ሰዎች እስካሁን የገቡበት አልታወቀም።

አልሸባብ እጄ አለበት ያለውን ጥቃት ለመቆጣጠር የፀጥታ ኃይሎች 19 ሰዓታት ወስዶባቸዋል።

የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ትናንት በበብሔራዊ ቴሌቪዥን ባደረጉት ንግግር ጥቃተን የፈፀሙት #አምስት ታጣቂዎችን #በመግደል የኦፕሬሽን ስራው #መጠናቀቁን ተናግረዋል።

ከጥቃቱ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

ኬንያ አልሸባብን ለመዋጋት ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ከላከችበትከፈረንጆቹ 2011 ጥቅምት ጀምሮ የሽብር ቡድኑ የጥቃት ዒላማ ሆናለች።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነው ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው 270 ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ ግንባታ 97 በመቶ #መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 23/2011 ዓ.ም.

ከትራንስፓርት ሚንስቴርና ከሌሎች ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የተወጣጣው የሉኡካን ቡድን የጅቡቲ ወደብን ጎብኝቷል።
.
.
ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በምዕራብ እንዲሁም ምሥራቅ ጉጂ በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች መካከል በታካሄደ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን በርካቶች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተናግረዋል።
.
.
ከአመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀምራው የነበረውን መጠነ ሰፊ የፀረ-ሙስና ዘመቻ እንዳጠናቀቀች አስታውቃለች፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት 100 ቢሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በቁስ መልክ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መሰብሰቡን አስታውቋል።
.
.
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የፀደቀውን #የስደተኞች_አዋጅ በመቃወም ነገ በጋምቤላ ከተማ ሊደረግ ለታሰበው የተቃውሞ ሰልፍ ፈቃድ #ከልክሏል
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ6 ሺህ ነጋዴዎች ግብር ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ ግብር ስረዛው ከ2003 እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከፍተኛ የግብር ተመን ተጥሎባቸው አቤቱታ ሲያቀርቡ የቆዩትን ነጋዴዎች ያካትታል፡፡
.
.
4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል ስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ #ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በጫነው አሸዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
.
.
በቴፒ ከተማ ከትንላንት ጀምሮ ዳግም #ያገረሸው #አለመረጋጋት ዛሬም ቀጥሏል። የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተቋርጦ ውሏል። ከተማዋ በፀጥታ ሃይሎች በከፍተኛ ደረጃ እየተጠበቀች ነው።
.
.
ዛሬ በስራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ዋጋ መጨመር ተከትሎ ምንም አይነት #የትራንስፖርት_ታሪፍ  ጭማሪ #እንደማይኖር የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገልጿል።
.
.
ጅቡቲ በተካሄደው 15ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የኢትዮጵያ ልዑካን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተዋል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች #አዲስ የስራ ምደባ እየካሄደ መሆኑን የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
.
.
#ኮማንድ_ፖስቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ወረዳዎች ላይ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ 528 ተጠርጣሪዎች 440 የሚሆኑትን በነፃ አሰናብቷል።
.
.
የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነው ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው 270 ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ ግንባታ 97 በመቶ #መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ገልጿል።
.
.
በሱማሌ ክልል ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰዓት ዕላፊ ገደብ ተጥሏል፡፡ የአደባባይ ስብሰባም ተከልክሏል፡፡
.
.
#ቴዎድሮስ_አዲሱ(ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ ቢፈቀድለትም #በሙስና_ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።
.
.
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ለሚያልፉ ዐለም ዐቀፍ መንገደኞች #የነጻ ጉብኝት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ዘርፍ ማህበር እና #የሰላም_ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የሰላም ሚዲያ ህብረት ትስሰር ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ዛሬ ማምሻውን አካሂደዋል።
.
.
የሐረሪ ክልል የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ #መሻሻል ማሳየቱን የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ  አስታውቋል።
.
.
#ብሄሬን መሰረት ተደርጎ ጥቃት ተፈፅሞብኛል በሚል በሀሰት የሽንት መሽኛ #ብልቱን በፋሻና ፕላስተር በመጠቅለል ግጭት ለመቀስቀስ የሞከረው ግለስብ ድሬ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ በዳቦ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ አግባብነት የሌለውና ህብረተሰቡን ያላማከለ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
.
.
በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን አንድ #ኢትዮጵያዊ በእስራኤል ፖሊስ መገደሉን በመቃወም ቴላቪቭ ውስጥ ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።
.
.
በአሜሪካ በተከሰተው ከፍተኛ ቅዝቃዜ እስካሁን ቢያንስ ስምንት ሰዎች #መሞታቸው ተገለጸ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በአሜሪካ ሜድ ዌስት የተከሰተው ቅዝቃዜ በአስር አመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ አደገኛ ነው፡፡
.
.
ምንጭ፦ etv፣ የጀርመን ራድዮ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ ዋዜማ ራድዮ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ bbc፣ VOA፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ ዞን ፖሊስ‼️

የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታን #ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ #በተጠናከረ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ምክትል ኮማንደር #ኤፌሶን¥ላካይቶ እንደገለጹት በዞኑ የፀጥታ ሁኔታ ለማረጋገጥ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው፡፡

ባለፉት ሶስት ወራት በተለያዩ የስርቆትና ንጥቂያ ወንጀል የተጠረጠሩና እጅ ከፍንጅ የተያዙ በቁጥር 50 የሚሆኑ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ብለዋል።

በዞኑ ዜጎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ለማድረግና የህግ የበላይነት እንዲከበር ለማስቻል መምሪያው ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰፊ ሥራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ሀገሪቱ በለውጥ ጎዳና ላይ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ለውጡን የማይቀበሉ አንዳንድ አካላት በሚፈጥሩት የፀጥታ መደፍረስ የተለያዩ የስርቆትና ንጥቂያ ወንጀሎች እየተበራከቱ በመሆናቸው ችግሮችን ለመቅረፍ የፀጥታ አካላትን ያሳተፈ ጊዜያዊ ግብረ ኃይል መቋቋሙንም ተናግረዋል፡፡

በዞኑ የሚፈጸሙ #የስርቆትና #የንጥቂያ ወንጀል #በዘላቂነት ለመከላከል በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የማወያየትና በወንጀሉ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በጉኑኖ ከተማ አስተዳደር በህገ ወጥ መንገድ ሌሊት ባለሁለት እግር ሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር ፖሊስ ያደረገውን ጥረት ጥቂት የሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎች ‹‹እኛን መቆጣጠር አትችሉም›› በማለት ሁከት ፈጥረው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ሁከት ፖሊስ ከከተማው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት #በቁጥጥር ስር ለማዋል መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በከተማው ሁከት የፈጠሩ፣ የተሳታፉና የመሩ በቁጥር 30 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ህጋዊ የምርመራ ሂደት መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

በሶዶ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ በቡድን ተደራጅተው #በስርቆት ወንጀል የተሰማሩ 9 ግለሰቦች ለህግ ቀርበው ተገቢ ውሳኔ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በዋዱ አከባቢም በተመሳሳይ ወንጀል ተሰማርተው የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራው #መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በተለይ የባለሁለት እግር ሞተር ብስክለት አሽከርካሪዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ማሽከርከር እንደሌለባቸው ያሳሰቡት ምክትል ኮማንደር ኤፌሶን ሌሊት ማሽከርከር ለተለያዩ አደጋዎች የሚያጋልጥ በመሆኑ ህብረተሰቡ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

በየአካባቢው ህብረተሰቡ ከወትሮው የተለየ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥም ለዞኑ ፖሊስ በ046-551-21-26፣ ለሶዶ ከተማ ፖሊስ 046-551-01-46፣ ለሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ 046-551-00-22 የስልክ ቁጥሮችን በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦Wolaita ZONE Culture,tourisim and Governmental Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትግራይ ዲያስፖራ ፌስቲቫል!

2ኛው ዓለምቀፍ የትግራይ ዲያስፓራ ፌስተቫል ለመካሄድ የሚያስችል ዝግጅት
#መጠናቀቁን የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል፡፡

ፌስቲቫሉ በተለያዩ የዓለም ሃገራት የሚገኙ የትግራይ ዲያስፓራ ማህበረሰብ በክልሉ ብሎም በሃገራቱ እየተከናወኑ ባሉት የሰላም የዴሞክራሲና የልማት ስራዎች ተሳታፊ ለማድረግ ያለው ነው ተብሏል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ልማትና ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር #አብርሃም_ተከስተ ዝግጅቱን አስመልክቶ በሠጡት መግለጫ ፌስቲቫሉ የትግራይ ዲያስፓራ ስለሃገራቸውና ስለ ክልላቸው ተጨባጭ ሁኔታ ተገንዝበው ለትግራይ ህዝብ ሰላምና ደህንነት በተደራጀ መልኩ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማድረግ ነው፡፡

ፌስቲቫሉ ዲያስፓራውን በክልሉ በሚካሄደው የንግድ የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ልማት እንቅስቃሴዎች ተሳታፊ ለማድረግ ነው ያሉት ዶክተር አብርሃም የፐብሊክ ዲኘሎማሲውን በማጠናከር በኢትዮ ኤርትራ የተጀመረውን የሰላም ግንኙነት ተጠናክሮ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ነው፡፡

ዋናው ፌስቲባል ከሃምሌ 24 -ሃምሌ 3ዐ/ 2ዐ11 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ ሲሆን የህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ /ህወሓት/ የተመሰረተበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ከየካቲት 11/2ዐ11 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እንደሚካሄደ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በመጪው ቅዳሜ በጅግጅጋ ከተማ ለሚካሄደው ስምንተኛው ሀገር አቀፍ የከተሞች ፎረም አስፈላጊው ዝግጅት #መጠናቀቁን የፎረሙ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የፎረሙ ተሳታፊዎች በቆይታቸው የሚያርፉበት ስፍራዎችና አንድ ሺህ ሁለት መቶ የእንግዶ ማረፊያ ክፍሎች በከተማው በሚገኙ ሆቴሎች መዘጋጀታቸውም ታውቋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ፓትርያርኩ ጳጉሜን 1 ቀን 2014 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰሜን አሜሪካን የነበራቸውን የሕክምና ክትትል በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ጤናቸውንም በተመለከተ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ ታውቋል። በመሆኑም ቀደም ሲል በተያዘው…
#Update

ቅዱስ ፓትርያርኩ ለህክምና ከሄዱበት አሜሪካ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲገቡ አቀባበል ይደረግላቸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሕክምናቸውን አጠናቀው ነገ ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው ይመለሳሉ።

ቅዱስ ፓትራርኩ ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው መመለሳቸውን ተከትሎ ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ጀምሮ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ታውቋል።

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በጤና ወደ መንበራቸው መመለሳቸው የቤተ ክርስቲያን ደስታ ነው ያለ ሲሆን በዚሁ መጠን ይፋዊ አቀበበል ዝግጅት ተደርጓል ሲል አሳውቋል።

የቅዱስነታቸውን ወደ አገር ቤት መመለስን አስመልክቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የአቀባበል ኮሚቴ ተቋቁሞ ሲሰራ የቆየ ሲሆን አሁን ላይ የአቀባበል ቅድመ ዝግጅቱ #መጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስነታቸው ወደ ሀገራቸውና ወቅዱስ መንበራቸው መመለስን ተከትሎ ነገ ለሚደረገው አቀባበል ሁሉም ሚዲያዎች ጥዋት 1 ሰዓት ላይ ቦሌ ኤርፖርት (VIP) እንዲገኙላት ጥሪ አቅርባለች።

@tikvahethiopia
" ዝግጅቱ ተጠናቋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዝግጅት #መጠናቀቁን አስታወቀ።

ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

በሚኒስቴሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ " የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎችን እውቀትና ብቃት ለመለካት የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ተጠናቋል " ብለዋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የትክክለኛ ተፈታኞችን ቁጥር እንዲያጣራ በማድረግ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 95 ሺህ 755 እንዲሁም ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 74 ሺህ 776 ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎቸ ዲግሪ እንደማይሰጣቸው እና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው የፈተና ጊዜ መሰረት ድጋሚ እንደሚፈተኑ አመልክተዋል።

ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ከተማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የሚባሉ ከ12 እስከ 17 የትምህርት ዓይነቶች ፈተና እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የፈተና ንድፍና የብቃት መመዘኛ መስፈርቶች መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ከግንቦት 15 ጀምሮ ለ211 የትምህርት ፕሮግራሞች የፈተና ጥያቄዎች በማውጣት ለፈተናው ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል።

ፈተናው በኦንላየን የሚሰጥ በመሆኑም አስፈላጊ የቴሌኮም እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ ካሉ 325 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 161 እና ከመንግስት ደግሞ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንደሚያስፈትኑ ጠቅሰዋል።

ዶ/ር እዮብ ፤ " ገበያው የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የመውጫ ፈተናው ከ2015 ጀምሮ በሁሉም የትምህርት መስኮችና መርሐ ግብሮች መስጠት እንዲቻል ስራዎች ከአንድ ዓመት በላይ ሲሰሩ ቆይቷል " ሲሉ አስታውሰዋል።

#ኢዜአ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በዓሉ #በሰላም ተጠናቋል " - ግብረ ኃይሉ

የ2016 የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርአቱን በጠበቀ መልኩ #በሰላም መከበሩን የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

ግብረ ኃይሉ ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ተገኝተውበታል ያለድ የዘንድሮው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብሮ #መጠናቀቁን ገልጿል።

የነገው የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓለም በተመሳሳይ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እና ለፀጥታ ኃይሉ እገዛውን እንዲያጠናክር ተጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU #ETHIOPIA ትላንትና ምሽት ላይ ለ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመጡ መሪዎች በብሄራዊ ቤተመንግስት የእራት ግብዣ ተደርጎላቸው ነበር። ዛሬ የጠ/ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ባሰራጫቸው ምስሎች የኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ፣ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌህን ጨምሮ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በእራት ግብዣው ላይ ተገኝተው የነበረ ሲሆን የጎረቤት ሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን…
#Update #ተጠናቋል

የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ በሰላምና በስኬት #መጠናቀቁን ኢትዮጵያ አስታውቃለች።

የሁሉም ሀገራት መሪዎች እና የጉባኤው ተሳታፊዎች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ ከዚህ ቀደም ከነበረው በደመቀ ሁኔታ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ ክብርን እና ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ አቀባበል እንደተደረገላቸው ፤ በአዲስ አበባ ቆይታቸውም በልዩ እንክብካቤ እንደተያዙ በኢትዮጵያ መንግሥት ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ለዚህ ጉባኤ ስኬት ላለፉት 6 ወራት ስትዘጋጅ መቆየቷን የተገለጸ ሲሆን በተለይም ከሰላምና ደህንነት አንፃር በርካታ ባለድርሻ አካላት ሲሳተፉ መቆየታቸውን ተጠቁሟል።

በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የፀጥታ እና ደህንነት ኃይሎች ተሰማርተው እንደነበረም ተመላክቷል።

ለጉባኤው ስኬታማነት በተለይ በተለይ የአዲስ አበባ ህዝብ ከቅድመ ጉባኤው ዝግጅት አንስቶ ስብሰባው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ የትራፊክ፣ የመንገድ መዘጋጋት እና ሌሎች ጉዳዮችንም ታግሶ ፤ ከፀጥታ ኃይሉም ጋር በመተባበር እንግዶች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲስተናገዱ ልዩ የእግዳ አቀባበል በማድረጉ መንግሥት ምስጋና አቅርቧል።

በተጨማሪ የፀጥታ እና ደህንነት ኃይሎች ፣ የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች፣ የፕሮቶኮል ሰዎች፣ ሆቴሎች ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሃን .. ሌሎችም አስተዋፅኦ ያደረጉ ሁሉ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

@tikvahethiopia