TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ነፃ የጡት ካንሰር ምርመራ "

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ከጥቅምት 15 እስከ ጥቅምት 22 ደረድ ነፃ የጡት ካንሰር ምርመራ እንደሚያካሂድ አሳውቆናል።

ምርመራው ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ከጥዋቱ 3 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ድረስ 5ኛ በር አካባቢ ነው የሚካሄደው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ENDF: የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ተጨማሪ የአየር ጥቃት ፈፅሟል። ጥቃቱ በዚህ ሳምንት ብቻ 4ኛው ነው። የዛሬው የአየር ድብደባ የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) የማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑን በፌዴራል መንግስት ስር ያለው የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገፅ አሳውቋል። ገፁ የአየር ድብደባው የት እንደተፈፀመ በግልፅ ባይጠቅስም " ሌላው የአሸባሪው ቡድን የህወሓት ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ…
" ... በራሳቸው ምክንያት ካልሆነ በስተቀር የአየር ድብደባውና የሰብአዊ እርዳታ ጫኝ አውሮፕላን እንቅስቃሴ አይገናኝም " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

ዛሬ ሮይተርስ 2 የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የተመድን የሰብአዊ እርዳታ የጫነ አውሮፕላን መንግስት በትግራይ ክልል ባካሄደው የአየር ድብድባ ምክንያት መቐለ ማረፍ አልቻለም ብሏል።

ሮይተርስ በዚህ ጉዳይ ሁለት ሰማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰዎችን ማናገሩን ጠቅሷል።

ይህንን ጉዳዩን በተመለከተ ለአል ዐይን ቃላቸውን የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ፥ " በራሳቸው ምክንያት ካልሆነ በስተቀር የአየር ድብደባው እና የሰብአዊ እርዳታ ጫኝ አውሮፕላን እንቅስቃሴ አይገናኝም" ብለዋል።

“አንደኛ ሰዓቱ የተለያየ ነው” ያሉት ዶ/ር ለገሰ፤ “መዳረሻዎችም የተለያዩ ናቸው” ሲሉም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን
Photo : FILE

@tikvahethiopia
#ኢህአፓ : የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ አገራዊ ምክር ቤት አዲስ አበባ በሚገኘው ፅ/ቤቱ ለሶስት ቀናት ስብሰባ አድርጎ ነበር። ም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴው ባቀረበለት አጀንዳ ውይይት ካካሄደ በኃላ ከላይ የተያያዘውን መግለጫ አውጥቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Harari : በሀረሪ ክልል የአዲስ መንግስት ምስረታ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ማካሄድ በጀመረው የመንግስት ምስረታ ጉባኤው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር , የምክር ቤቱን አፈጉባኤ እና ምክትል አፈጉባኤ እንደሚሾም ይጠበቃል። በተጨማሪም ጉባኤው በቆይታው በርዕሰ መስተዳድሩ የሚቀርቡ የምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የካቢኔ አባላትንም እጩዎችን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡ በክልሉ…
#UPDATE

አዲሱ የሀረሪ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያ ጉባኤ አቶ ኦርዲን በድሪ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሹሟል።

አቶ ኦርዲን በድሪ ላለፉት ሶስት አመታት የሀረሪ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት መርተዋል።

በተጨማሪ መረጃ ፦ አቶ ሱልጣን አብዱሰላምን የምክር ቤቱ ዋና አፈጉባኤ ፤ አቶ አሪፍ መሀመድ አዱስ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ በመሆን ተሹመዋል፡፡

ምንጭ፦ የሀረሪ ክልል ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#EHRC : የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቶ እስክንድር ነጋ የሚገኙበትን ሁኔታ ለማጣራት ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማረፊያ በመገኘት፣ አቶ እስክንድር ነጋን፣ ክስተቱ ሲፈጠር በስፍራው የነበሩትን አቶ ስንታየው ቸኮልን፣ ከአቶ እስክንድር ጋር ተጋጩ የተባሉትን እስረኛ፣ እንዲሁም የማረሚያ ቤቱን አስተዳደር አካላት ማነጋገሩን ሳውቋል።

በማጣራቱ ሂደት ለመረዳት እንደተቻለው፣ አቶ እስክንድር የፍርድ ቤት ቀጠሮ በነበራቸው ሐሙስ ጥቀምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠዋት በሚገኙበት ዞን ግቢ ውስጥ የስፖርት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እያሉ፣ ከዚህ ቀደም እርሳቸው ባሉበት ዞን ታስረው የነበሩና ከዞኑ  ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተዘዋውረው ከነበሩ ከሌላ እስረኛ ጋር ሲገናኙ በመካከላቸው የተነሳው የቃላት ልውውጥ ወደ አካላዊ ግጭት ተሸጋገረ።

ክስተቱ እንደተፈጠረ የእስር ቤቱ ጥበቃዎች እና ሌሎች ታራሚዎች እንዳገላገሏቸውና የማረሚያ ቤቱ አስተዳደርም ሌላኛውን እስረኛ ወዲያው ወደ ሌላ ዞን ማዘዋወሩን ለማረጋገጥ ተችሏል።

በአቶ እስክንድር እና በእስረኛው መካከል ከዚህ ቀደም አለመግባባት እንደነበረና እስረኛው ከተዘዋወሩበት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በቅርቡ የተመለሱ መሆኑንም ኮሚሽኑ መገንዘብ ችሏል።  

በሁኔታው አቶ እስክንድር በግራ እግር አውራጣታቸው ላይ እብጠት፣ በሁለቱም ጉልበቶቻቸው ላይ የመላላጥና በቀኝ ቅንድባቸው ላይ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን፣ በማረሚያ ቤቱ ክሊኒክ የተመላላሽ ሕክምና እያገኙ መሆኑንና በአሁኑ ጊዜ በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አረጋግጧል። በሌላኛው እስረኛ ላይም በቀኝ እጅ ጣቶቻቸው ላይ የመፋፋቅ ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማየት ተችሏል።

ያንብቡ : telegra.ph/EHRC-10-22

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በነአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ሂደት ችሎት ታድመው የነበሩ 42 የፓርቲው አባላት ታፍሰው ልደታ ክፍለ ከተማ የፖሊስ መምሪያ ከቆዩ በኋላ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው እንዲታሠሩ እንደተደረጉ ገልጿል። ከታሠሩት ውስጥ አስራ ሁለቱ (12) ሴቶች መሆናቸውን ፓርቲው አረጋግጫለሁ ብሏል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ…
#Balderas : ከታሰሩት የባልደራስ አባላት እና ደጋፊዎች መካከል 2ቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጥረዋል።

የእነ አቶ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጥቅምት 11/2014 የሄዱ 42 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው ዕለት በፓሊስ መታሰራቸው መግለፁ ይታወሳል።

ባልደራስ ፓርቲ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ የታሰሩት ፥ አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ በችሎት ከሰሙ በኃላ እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው ከችሎት ወጥተው በመንገድ ላይ እያኑ ነው ፖሊስ የታሰሩት ብሏል።

ታሳሪዎቹ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ " ችሎት ውስጥ ረብሸዋል፣ ሲወጡ ደግሞ ፍትህ የለም ፣ መንግስት የለም በማለት ሁከት እና ብጥብጥ በመቀስቀስ " ሲንቀሳቀሱ መያዙን ገልጿል።

ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ የምስክሮችን ቃለ ለመቀበል እና ማስረጃቸውን ለማሰባሰብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ቆጠሮ ጠይቋል።

የ42ቱ ተጠርጣሪዎች ጠበቆች ፖሊስ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ ውድቅ እንዲሆን ጠይቀዋል።

"በችሎት ውስጥ ተፈጸመ ለተባለው ድርጊት ፖሊስ የሚመለከተው ሳይሆን በወቅቱ ችሎቱ በራሱ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ነው። ሆኖም ግን ችሎቱ ምንም አይነት ትዕዛዝ ባልሰጠበት ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ተገቢ አይደለም" ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ " ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበት ምክንያት በሕግ ምንም አይነት ድጋፍ " የለውም በማለት የጊዜ ቀጠሮው ውድቅ እንዲሆን በመጠየቅ ከእስር እንዲለቀቁ ለፍ/ቤት ጥያቄ አቅርበዋል ።

ያንብቡ : telegra.ph/BALDERAS-10-22

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 17 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,292 የላብራቶሪ ምርመራ 620 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 512 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
ሻንጋይ ፋርማ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ሊያደርግ ነው።

በቻይና ሀገር 2ኛው ግዙፍ የመድሃኒት አምራች እና አካፋፋይ "ሻንጋይ ፋርማ /Shanghai Pharma/ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ ወስኗል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የአዋጭነት ጥናት ካጠናቀቀ በኋላ ነው ኢንቨስት ለማድረግ ውሳኔ ላይ የደረሰው።

የሻንጋይ ፋርማ ኩባንያ ተወካዮች ከአንድ ሳምንት በፊት በቻይና ከኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

የሻንጋይ ፋርማ ኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጆች በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#Amhara : የአሜሪካ መንግስት ግጭት ባለባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ትላንት በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከአዲሱ የክልሉ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በውይይቱ ወቅት ዶ/ር ይልቃል የትግራይ TPLF በአማራ ክልል በወረራቸው አካባቢዎች እየፈፀመ ነው ያሉትን ሰብዓዊ ቀውስ በዝርዝር እንዳስረዷቸው ተነግሯል።

ከውይይቱ በኃላ መግለጫ የሰጡ ጊታ ፓሲ ሀገራቸው አሜሪካ በአማራ ክልል ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን እንደምትደግፍ ገልፀዋል።

አምባሳደር ጊታ ፓሲ በመግለጫቸው ይህ ብለዋል፦

"ከአዲሱ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ጋር በአማራ ክልል ስላለው ሁኔታ በሰብዓዊ ድጋፍ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።

ሰብዓዊ ሁኔታውን የተመለከተ ግምገማም እንፈልጋለን፤ ከሰብዓዊ ድጋፍ አጋሮቻችን ጋርም ተገናኝተናል፤ በጣም አስፈላጊው ለኔ የማይረሳው በአማራ ክልል ከሚገኙ ተፈናቃዮች ጋር መገናኘት ነው።

ለተፈናቀሉ ወገኖች በሚደረገው ሰብዓዊና በቀጣይ ለማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል።

ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ ሰዎች ሁሉ ስቃይ ላይ ናቸው፤ የግጭቱ አካባቢ የትም ይሁን የትም።

በጦርነት እና በአለመረጋጋት ጊዜ የሚያጋጥም ስቃይ ድንበርን አያውቅም። ከተነጋገርንባቸው ጉዳዮች አንዱም ይሄ ነው።

ስቃዩ እንዲያበቃ ግጭቱ መቆም አለበት፤ ይህ የአሜሪካ መንግስት ብዙ ጊዜ የተናገረው ነው ልደግመው ፈልጋለሁ፤ለችግሩ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም፤ የሆነ አይነት ውይይት፣ ስምምነት እና ተኩስ አቁም እንደሚኖር ተስፋ እናደርጋለን።

ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያውያን የትም ይሁኑ የትም አሜሪካ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ናት"

@tikvahethiopia
#GERD : በህዳሴው ግድብ 2ኛ ዙር የደን ምንጣሮ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ከ40 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸው ተገለጸ።

ይህ የተገለፀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቴክኒክ እና ሙያ ስራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲ የስራ አፈጻጸሙን በክልሉ መዲና አሶሳ በገመገመበት ወቅት ነው።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በሽር አብዱራሂም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆን ጀምሯል ያሉ ሲሆን በ2ኛው ዙር የግድቡ ውሃ ሙሌት ደን ምንጣሮ ስራ በክልሉ የሚገኙ በ149 ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ ከ1 ሺህ 300 በላይ ስራ አጦች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አክለውም ፥ የኢንተርፕራዞቹ አባላት 2 ሺህ 736 ሄክታር መሬት የደን ምንጣሮ ስራ ማካሄዳቸውንና በዚህም ከ40 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጋ ብር በመቆጠብ ወደ ቋሚ ስራ መሸጋገራቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD : በህዳሴው ግድብ 2ኛ ዙር የደን ምንጣሮ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ከ40 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘታቸው ተገለጸ።  ይህ የተገለፀው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቴክኒክ እና ሙያ ስራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲ የስራ አፈጻጸሙን በክልሉ መዲና አሶሳ በገመገመበት ወቅት ነው። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በሽር አብዱራሂም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ…
#ተጨማሪ

ሶስተኛውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት የሚካሄድበት ስፍራ የደን ምንጣሮ ስራ በመጪው ታህሳስ ወር ለማስጀመር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አሻድሊ ሃሰን አሳውቀዋል።

ይህ ያሳወቁት የቴክኒክ እና ሙያ ስራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲ የስራ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ነው።

በመጀመያው እና 2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በተከናወነባቸው አካባቢዎች የተመነጠረው ደን እንዲቃጠል መደረጉን አቶ አሻድሊ አስታውሰዋል፡፡

በተያዘው ዓመት የሚካሄደው የደን ምንጣሮ እንደከዚህ ቀደሙ የገቢ ምንጭ ለማድረግ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የክልሉን ጸጥታ ወደቀደመ ሁኔታ ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት የክልሉ ፕሬዜዳንት ፥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#Tolay : ዛሬ በጦላይ ማሰልጠኛ ማእከል መሰረታዊ የፖሊስ ስልጠና የወሰዱ ምልምል የፌደራል ፖሊስ ሰልጣኞች ተመርቀዋል።

በ20ኛ ዙር የተመረቁት ልዩ የፌደራል ፖሊስ ምልምል ሰልጣኞች በፌደራል ፖሊስ ታሪክ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙና ሃገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር የጠላትን የውስጥና የውጭ ጥቃት ለመመከት በፅንሰ-ሃሳብና በአካላዊ ብቃት በጥራት የሰለጠኑ ናቸው ተብሏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል እና ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው እንደነበር ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia