TIKVAH-ETHIOPIA
#Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በነአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ሂደት ችሎት ታድመው የነበሩ 42 የፓርቲው አባላት ታፍሰው ልደታ ክፍለ ከተማ የፖሊስ መምሪያ ከቆዩ በኋላ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው እንዲታሠሩ እንደተደረጉ ገልጿል። ከታሠሩት ውስጥ አስራ ሁለቱ (12) ሴቶች መሆናቸውን ፓርቲው አረጋግጫለሁ ብሏል። ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ…
#Balderas : ከታሰሩት የባልደራስ አባላት እና ደጋፊዎች መካከል 2ቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጥረዋል።

የእነ አቶ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጥቅምት 11/2014 የሄዱ 42 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው ዕለት በፓሊስ መታሰራቸው መግለፁ ይታወሳል።

ባልደራስ ፓርቲ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ የታሰሩት ፥ አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ በችሎት ከሰሙ በኃላ እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው ከችሎት ወጥተው በመንገድ ላይ እያኑ ነው ፖሊስ የታሰሩት ብሏል።

ታሳሪዎቹ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ " ችሎት ውስጥ ረብሸዋል፣ ሲወጡ ደግሞ ፍትህ የለም ፣ መንግስት የለም በማለት ሁከት እና ብጥብጥ በመቀስቀስ " ሲንቀሳቀሱ መያዙን ገልጿል።

ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ የምስክሮችን ቃለ ለመቀበል እና ማስረጃቸውን ለማሰባሰብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ቆጠሮ ጠይቋል።

የ42ቱ ተጠርጣሪዎች ጠበቆች ፖሊስ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ ውድቅ እንዲሆን ጠይቀዋል።

"በችሎት ውስጥ ተፈጸመ ለተባለው ድርጊት ፖሊስ የሚመለከተው ሳይሆን በወቅቱ ችሎቱ በራሱ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ነው። ሆኖም ግን ችሎቱ ምንም አይነት ትዕዛዝ ባልሰጠበት ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ተገቢ አይደለም" ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ " ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበት ምክንያት በሕግ ምንም አይነት ድጋፍ " የለውም በማለት የጊዜ ቀጠሮው ውድቅ እንዲሆን በመጠየቅ ከእስር እንዲለቀቁ ለፍ/ቤት ጥያቄ አቅርበዋል ።

ያንብቡ : telegra.ph/BALDERAS-10-22

@tikvahethiopia