TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለአካል ጉዳተኞች በአይነቱ ለመጀመርያ ጊዜ በተከታታይ ለሶስት ቀን ሲሰጥ የነበረው የፈጠራ አቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ከጥቅምት 1 እስከ 3/2014 በተከታታይ ለሶስት ቀን ለአካል ጉዳተኞች (PWD) እንደ አገር በፈጠራ ሥራዎች እንዲሰማሩ የሚያግዝ ሁሉን አቀፍ የፈጠራ ፖሊሲ እንዲኖራቸው ለገበያ የሚቀርቡ ክህሎቶችን እና የግል ብራንዲንግን ለፖሊሲ ተሟጋችነት ለማሳደግ የሚያስችል በአይነቱ የመጀመርያ የሆን ስልጠና በሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች (Indigenous Innovation -I2) የበጎ አድራጎት ድርጅት ከCIPE ጋር በመተባበር ተሰጥቷል።

በስልጠናው መጨረሻ ላይ የስልጠና ተሳታፊዎቹ ድርጅቶቹ በስልጠናው ቀጣይነት ላይ እንዲሰሩ እና በኢትዮጵያ የኢኖቬሽን የፖሊሲ ማሻሻያ አካል ጉዳተኞችን ያካተተ እንዲደረግ ለአካል ጉዳተኞች ፍትሃዊ ተሳትፎ በመሟገት አምባሳደር ለመሆን ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA : ከሰዓታት በኃላ የአሜሪካ ፕሬዚዳን ጆ ባይደን የኬንያውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዋይት ሀውስ ተቀብለው ያነጋግራሉ፡፡ ፕሬዝዳንት ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኃባ አንድን የአፍሪካ አገር መሪ ተቀብለው ሲያነጋግሩ ይህ የመጀመሪያቸው ይሆናል፡፡ ጄን ሳኪ (የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ) ሁለቱ መሪዎች “ዴሞክራሲንና የሰብአዊ መብቶችን በመክላከል ሰላምና ደህንነትን ማስከበርና የምጣኔ ሀብት…
ባይዳን እና ኬንያታ ምን ተወያዩ ?

ትላንት ለሊት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የኬንያውን ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታን በዋይት ሐውስ ተቀብለው አነጋግረዋል።

ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በወጣው መረጃ ሁለቱ መሪዎች በአሜሪካ እና በኬንያ መካከል ባለው ጠንካራ የተባለ ወዳጅነት ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ውስጥ ላሉ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሄ መገኘት አለበት በሚለው ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተነጋግረዋል።

ሁለቱ መሪዎች ዲሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እንዲሁም አህጉራዊ ሰላም እና ደኅንነት በማስጠበቅ ዙሪያ ሁለቱ አገራት በጋራ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ዙሪያ ተነጋግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝደንቶቹ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በጋራ ለመግታት የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ለማምረት ሊያደርጉ ስለሚችሉት ትብብሮች ተወያይተዋል።

ፕሬዝደንት ባይደን ለአፍሪካ ሕብረት አገራት የጆንሰን ኤንድ ጆንስን ምርት የሆነው 17 ሚሊዮን ክትባት እንደሚሰጡ አስታውቋል።

Credit : BBC

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከትላንትና በስቲያ በደቡብ አፍሪካ ግዛት በሆነቸው Port Elizabeth በሶማሊያ ዜጎች እና በደቡብ አፍሪካ የPort Elizabeth የታክሲ ባለንብረቶች መካከል ግጭት ተነስቷል።

በተፈጠረው ግጭት እስካሁን በሰው ሕይወት የደረሰ ጉዳት እንዳለ ባይታወቅም በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የግጭቱ መነሻ በአካባቢው ያሉ የታክሲ ባለንብረቶች ከሶማሊያዊ የሱቅ ባለቤት ጋር በተፈጠረው አለመግባባት እንደሆነ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ገልፀዋል።

በዜጋቸው ላይ የደረሰውን በደል የሰሙ በተለያየ ቦታ የሚገኙ የሶማሊያ ተወላጆች ግጭት ወዳለበት ስፍራ እንዳቀኑ እና በቦታው ካሉ የታክሲ ባለንብረቶች ጋር ግጭት ውስጥ እንደገቡ የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ያለው ውጥረት ረገብ እስኪል ድረስ በአካባቢው የምትኖሩት (የTikvah-Ethiopia ቤተሰቦች ) ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እራሳችሁን እንድትጠብቁ እና ጥንቃቄ እንድታደርጉ ለማለት እንወዳለን

Faya (Tikvah-family)
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
#Bahirdar : የባህርዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ መመሪያን ተከትለው ያልሰሩ የግል ትምህርት ቤቶችን አስጠነቀቀ።

መምሪያው በከተማው ላሉ ትምህርት ቤቶች በፃፈው ደብዳቤ ከዚህ ቀደም በትምህርት ቤት ክፍያ ጉዳይ ተከታታይ ውይይት መደረጉን አስታውሷል።

መስከረም 7/2014 ዓ/ም ትምህርት ቤቶቹ የተማሪ ወላጆችን ሰብስበው በክፍያ ዙሪያ ከወላጅ ጋር ተግባብተው በመመሪያው መሰረት ወላጅ ያመነበትን ክፍያ እንዲያስከፍሉና ወላጆችን ያወያዩበት ቃለጉባኤ የተሳታፊዎችን ፊርማ እና በቪድዮ የተደገፈ ማስረጃ ለትምህርት መምሪያው መረጃ አደራጅተው እንዲያሳውቁ በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት ተቋማቱ ዕድሉን እንዳልተጠቀሙበት ትምህርት መምሪያው በደብዳቤው ላይ ገልጿል።

አሁን ላይ ወላጆች የት/ቤት ክፍያ እንደተጨመረባቸው ይህ የተጨመረው ጭማሪም ወላጆች ያላመኑበት መሆን ለመምሪያው ቅሬታ እያቀረቡ እንደሚኙ ገልጿል።

ትምህርት መምሪያው ፥ ትምህርት ቤቶች የጨመሩት ክፍያ ከተማሪ ወላጆች ስምምነት ውጭና ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ከመስከረም 2014 ጀምሮ የተከፈለ ክፍያ ለቀጣይ ወራት ታሳቢ ተደርጎ በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ሲያስከፍሉ የነበረውን ክፍያ እንዲያስከፍሉ አሳስቧል።

ት/ቤቶቹ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ የማያደርጉ ከሆነ በቀጣይ የማስተማር ፍቃዳቸው እንደሚነሳ ፤ ከ2ኛ ሴሚኒስተር በኃላ ምንም አይነት ተማሪ በተቋማቸው የማይማርና ተቋማቱም እንደሚዘጋ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#AGOA : ኢትዮጵያ በ "AGOA" በኩል ያላት ተጠቃሚነት ላይ አሜሪካ በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ ካትሪን ታይ (የንግድ ተወካይ) ተናግረዋል።

ኃላፊዋ በይፋዊ መንገድ እና በግብረሰናይ ድርጅቶች በኩል የሚደርሱን መረጃዎች አበረታች አይደሉም፤ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያ ቢልለኔ ስዩም፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ቢልለኔ፥ " ሰብዓዊ ቀውስ AGOA እድል ከፈጠረላቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሴቶች የስራ እድል በመንጠቅ አይገታም እንደውም ያባብሰዋል" ብለዋል።

ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ አሜሪካ፥ በኢትዮጵያ እየተፈፀሙ ነው ያለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፍትሄ የማያገኙ ከሆነ በAGOA ያለቀረጥ ምርቶቿን ለአሜሪካ ገበያ የማቅረብ እድሏን እንደምታጣ ገልፃ ነበር።

ሮይተርስ ኢትዮጵያ በ2020 (እኤአ) 237 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሸቀጦችን ያለቀረጥ በAGOA በኩል ለአሜሪካ ገበያ ማቅረቧን የሀገሪቱ መንግስት መረጃ ያሳያል ብሏል።

የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ አማካሪ እና የኢትዮጵያ የንግድ ተደራዳሪ የሆኑት ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያን በAGOA በኩል ያላትን እድል ማሳጣት ማለት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞች እንደሚጎዳ ለፎርየን ፖሊሲ በፃፉት የግል አስተያየት ላይ ገልፀዋል።

AGOA ምንድነው?

African Growth and Opportunity Act (AGOA) የግብይት ስርዓት ነው፤ ይህ የግብይት ስርዓት የተወሰኑ የብቃት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ሸቀጦችን ያለቀረጥ ለአሜሪካ ገበያ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ነው። #DW

@tikvahethiopia
አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ መሞቱ ተገለፀ።

የናይጄሪያ ጦር ፤ የምዕራብ አፍሪካ የISIL ከፍተኛ መሪ መሞቱን አስታወቀ።

የናይጄሪያ ጦር ኃይል ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ላኪ ኢራቦር ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ፥ " አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ መሞቱን አረጋግጥላችኃለሁ ፤ ሞቷል እንደ ሞተም ይቀራል" ብለዋል።

ጄኔራሉ ፤ አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ መቼ እና እንዴት እንደሞተ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የምዕራብ አፍሪካ የISIL ከፍተኛ መሪ የሆነው አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ በ2009 የተገደለው የናይጄሪያው ቦኮ ሃራም የታጠቀ ቡድን መስራች መሀመድ የሱፍ ልጅ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Masha በማሻ ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ። በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን የመቅደላ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳውቋል። ገደቡ የተጣለው የሀገሪቱን እና የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ለህዝቡ ደህንነት ሲባል መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስ የእንቅስቃሴ ገደቡን በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ በማሻ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ሞተርና ባጃጅ…
#Kombolcha : በኮምቦልቻ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

ኮምቦልቻ ከተማ አስተደደር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ፥ ለከተማው ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት እና በህወሓት ቡድን ከቤት ቀያቸው ተፈናቅለው በከተማው ለሚገኙ ወገኖች አጠቃላይ ደህንነት ሲባል እንቅስቃሴዎች በሰዓት እንዲገደቡ መወሰኑን አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

1ኛ. ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ ከፀጥታ አስከባሪዎች ውጭ የትኛውም ዓይነት የግለሰቦች እንቅስቃሴ ተከልክሏል።

2ኛ. ለወቅታዊ ሰራ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ተቋማትና የጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጭ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እንቅስቃሴአቸው እንዲገደብ ተወስኗል።

3ኛ. የፋብሪካ ሰርቪስ በመስጠት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች ከሚያገለግሉበት ተቋም የመውጫ እና የመግቢያ ስዓት በተቋሙ ህጋዊ ደብዳቤ ለሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

መላው የኮምቦልቻ ነዋሪዎች ለሁሉን አቀፍ ትብብር እራሳቸውን ዝግጁ እንዲያዲያደርጉ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#Gedo : በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በጨሊያ ወረዳ ጌዶ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝወ የነበረ ከ3 ሺህ 850 በላይ የክላሽ ተተኳስ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ መመሪያ አስታውቋል።

ፖሊስ እንዳሳወቀው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3/59736 የሆነ ተሸከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሸ ከ3 ሺህ 850 በላይ የክለሽ ተተኳስ ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

ጥይቶቱ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ ነው ብለዋል፡፡

የመኪናው አሽከርካሪ እና የንብረቱ ባለቤት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል።

ጥይቱን ለመውሰድ የመጣ ግለሰብም ትላንት በቁጥጥር ስር መዋሉ የከተማው ፖሊስ አክሎ መግለፁ የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን አሳውቋል።

Credit : Oromia Communication

@tikvahethiopia
#Majete : በሰ/ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ወረዳ የማጀቴ ቀጣና አንቃር ኮበኮብና አግላ ማጀቴ ቆላ ባሳለፍነው ዕሮብ ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ የ15 አምስት አርሶ አደሮች በማሳ ላይ እየተሰበሰበ ያለ የጤፍ ሰብል መቃጠሉን የኤፍራታና ግድም ወረዳ አሳውቋል።

ወረዳው ፥ የጤፍ ሰብሉ የተቃጠለው በአጥፊ ኃይሎች ነው ሲል ገልጿል።

ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ፦
- የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ፀጥታ አመራሮች
- የሰ/ሸዋ ዞን የፀጥታ አመራሮች፣
- የኤፍራታና ግድም ወረዳ አመራሮች
- የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ አመራሮች
- የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ - የአገር መከላከያ ሰራዊት
- የፌደራል ፖሊስ አካባቢው የሚገኙ የፀጥታ ሃሎች እና የሰላም ኮሚቴን ጨምሮ የችግሩን ጠንሳሽ ለማጣራት እየሰሩ መሆኑን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተናግረዋል።

ከሁለቱም አጎራባች ወረዳዎች የተውጣጣ የምርመራ ቡድንም ተዋቅሮ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው አስረድተዋል።

የተቃጠለው የጤፍ ሰብል 95 ኩንታል የተገመተ ሲሆን 4 መቶ 27 ሺህ 5 መቶ ብር የተተመነ መሆኑን ገልፀዋል።

የተቋቋመው የምርመራ ቡድን ጉዳዩን አጣርቶ ለአርሶ አደሮቹ ይከፈላልም ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ፥ በተደጋጋሚ ቀጣናው ወደ አልተፈለገ ችግር ውስጥ ለማስገባት የሚሰሩ የፀረ ሰላም ሃሎችን ከዕኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ያሳሰቡ ሲሆን ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን በቅንጅት መስራት አለበት ብለዋል።

Credit : ኤፍራታና ግድም ወረዳ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia