TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara የትግራይ ክልል ጦርነት ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች ከሰፋ በኃላ ህወሓት የተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎችን ፣ በርካታ ህዝብ የሚኖርባቸውን ከተሞች እንደተቆጣጠረ ይገኛል። መንግስት አካባቢዎቹን ከቡድኑ ለማስለቀቅ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ከዚህ ቀደም ሲገልፅ ነበር። ከሰሞኑ የህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ይዘዋቸዋል በተባሉ ቦታዎች ላይ የአየር ድብደባ እየተፈፀመ…
የህወሓት በ #አማራ_ክልል በያዛቸው አካባቢዎች የኢትዮጵያ ጦር ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ "ሙሉ የማጥቃት" እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ዛሬ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘገብ ውሏል።

ህወሓት ዛሬ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ጦር ተከፈተብኝ ያለውን ጥቃት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርቧል።

ህወሓት የኢትዮጵያ ሠራዊት የተቀናጀ ጥቃት ከፍቶብኛል ያለ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማኅረሰብ ይህንን እርምጃ እንዲያወግዝ ጠይቋል።

ህወሓት በኢትዮጵያ ሰራዊት እየተሰነዘረበት ያለው ጥቃት "በከባድ ጦር መሳሪያ፣ በታንክ፣ በሮኬቶች፣ በድሮኖች እና በተዋጊ ጀቶች" የታገዘ እንደሆነ ገልጿል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ጦር በህወሓት ታጣቂዎች በተያዙ ቦታዎች ላይ "ከባድ" የተባለ ጥቃት መፈፀም እንደጀመረ መገለፁ አይዘነጋም።

ካለፉት ቀናት አንስቶ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩ ለነበሩ መረጃዎች ቃሉን ያልሰጠው የመከላከያ ሰራዊት በይፋዊ ገፁ ላይ ዛሬ ምሽር መግለጫ አውጥቷል።

ሰራዊቱ ፥ "ህወሓት ውሸት ቀለቡ ነው ያለ ሲሆን ፤ በአንድ በኩል "ተጠቃሁ" ድረሱልኝ ፤ በሌላ በኩል ደግሞ "የትግራይ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሰራዊት ባለበት ተኮማትሮ እንዲቀመጥ አድርገነዋል" ሲል ይገልጻል ብሏል።

አክሎ ፥ የዛሬው ፈሊጥ ለጋላቢዎቹ "መጠነ ሰፊ ጥቃት" ተሰነዘረብኝ እባካችሁ አድኑኝ እያለ ሲማፀን ለሚጋልባቸው ደግሞ "አኮማትሬያለሁ" እያለ መዘላበድ ሆኗል ብሏል።

መከላከያ ሰራዊት በራሱ ዕቅድ ሙሉ ማጥቃት ከጀመረ " ተጠቃሁ " ብሎ ለመናገር እንኳን ጊዜ ሳያገኝ የሚፈፀም እንደሚሆን መታወቅ አለበት ያለ ሲሆን ህዝቡ በወሬ ሳይደናገር የቁርጥ ቀን ልጆቹ በመንግስት ትዕዛዝ አይቀሬውን ድል እስኪያበስሩ የተለመደውን ድጋፍ እንዲያደርግ ሲል ጠይቋል።

* መግለጫው ከመከላከያ ሰራዊቱ ገፅ ተነስቷል።

@tikvahethiopia
ፌስቡክ ማሻሻያ ሊያደርግ ነው።

ፌስቡክ ማሻሻያ አደርጋለሁ ያለው በሚሰጠው አገልግሎት ላይ “ህጻናትን የሚጎዱ የተለያዩ መድረኮችን ያመቻቻል” በሚል ሰሞኑንን የቀረበበትን ውግዘትና ተጠያቂነት ተከትሎ ነው።

መሠረቱን አሜሪካ ካሊፎኒያ ሚንሎ ፓርክ ያደረገው የፌስቡክ ኩባንያ እንደ ኢንስታግራም ባሉት የምስልና ፎቶዎች መቀባበያ መድረኮቹ፣ ህጻናት በተከታታይ ከሚመለከቷቸው ምስሎች ፋታ እንዲወስዱና እንዲገቱ የሚያደርጉ የተለያዩ ቅንብሮችን መጠቀም እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

በተለይ ህጻናት መመልከት የማይገባቸውን ምስል ደጋግመው እንዳይመለከቱ የሚያግዳቸው መሆኑንም ገልጿል፡፡

ታዳጊዎቹ ወጣቶች ኢንተርኔት ላይ ምን እንደሚያደርጉ ምን እንደሚመለከቱ ማወቅ ለሚፈልጉ ወላጆችና ሞግዚቶቻቸውም በቤተሰቦቻቸው ምርጫ የተለያዩ የመቆጣጠሪያ ስልቶችን እንደሚያበጅ ፌስቡክ አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ እቅዱ የመጣው “ኢንስትግራም ፎር ኪድስ” በሚል ልጆች ላይ ያነጣጠረ ልዩ ፕሮጀክቱን ባላፈው ወር መገባደጃ ላይ ለጊዜው ያቆመው መሆኑን ካስታወቀ በኋላ ነው፡፡

በዚህ የተነሳ ተችዎች ፌስቡክ አደረገዋለሁ ያላቸውን ስለማድረጉ ጥርጥሬ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱም ተችዎቹ እንደሚሉት ስለ እቅዱ “በዝርዝር ያስቀመጠው ምንም ነገር የለም፡፡”

ፌስቡክ ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለአገልግሎት መድረኩ ደህንነት መጠበቂያ 13 ቢሊዮን ዶላር ያወጣ ሲሆን ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግም 40 ሺ ሠራተኞች የተሰማሩበት መሆኑን ማስታወቁን ቪኦኤ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#AU

የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ።

የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።

የሕብረቱ ኮሚሽን የሚያዘጋጀው የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጥቅምት 4 እና 5 ቀን 2014 ዓ.ም በአፍሪካ ሕብረት ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ይካሄዳል።

በስብሰባው ለመሳተፍ የላይቤሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲ-ማክስዌል ሳህ ኬማያ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሕብረቱ 55 አባል አገራት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

የምክር ቤቱ ስብሰባ የአገራት መሪዎች፣ የአፍሪካ ሕብረት ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማኀበረሰብ ተቋማትና በሕብረቱ ስር የሚገኙ ተቋማት የሚያደርጉት በሶስተኛው አጋማሽ ዓመት ለሚያደርጉት ጥምር ውይይት አጀንዳዎች የሚቀርቡበት ነው።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#BORENA

• "... በዝናብ መጥፋት 4164 ከብቶች ከ1916 አባወራዎች ሞተዋል ፤ ከ9 ሺ በላይ የቀንድ ከብቶች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው " - ዶ/ር ቃሲም ጉዮ (የቦረና ዞን የእንስሳት ሀብት ቢሮ ኃላፊ)

• "... የሳር ግዢው በቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ፤ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ለአርብቶ አደሮች ይደርሳል " - ዶ/ር አሚና አብዱራህማን (የክልሉ እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ኤጀንሲ ኃላፊ)

በቦረና ዞን በበልግ እና ክረምት ዝናብ በመጥፋቱ ከአራት ሺህ በላይ ከብቶች መሞታቸዉ ተነግሯል።

በደቡብ ኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በጊዜዉ መዝነብ የነበረበት ዝናብ በመዘግየቱ በላይ የቀንድ ከብቶ መሞታቸውን የዞኑ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ነዋሪዎቹ ይህ ክስተት መታየት ከጀመረ አንድ ወር መሆኑን ተናግረው፣ በዚህም በሺሕዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በተለያዩ የዞኑ አካባቢዎች እንደሞቱ ነው የገለጹት።

እስካሁን ድረስ ለአርብቶ አደሮች በቂ ድጋፍ እንዳልተደረገ ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች አሳውቀዋል።

የቦረና ዞን የእንስሳት ሀብት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ቃሲም ጉዮ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል እስካሁን ከ4 ሺሕ የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን፣ ከዘጠኝ ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በሞት አፋፍ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ኃላፊው ፤ ለሁለት ወቅት መዝነብ የነበረበት ዝናብ መዘግይቱ ለጉዳቱ መንስኤ መሆኑን ገልፀዋል።

ዶ/ር ቃሲም ብዙ የቀንድ ከብት ሞት እየተመዘገበ ያለበትን ወረዳዎች በዝርዝር ገልፀዋል።

1ኛ. ተልተሌ ወረዳ ከ1486 በላይ ከብቶች ሞተዋል።
2ኛ. ድሎ ወረዳ 992 ከብቶች ሞተዋል።
3ኛ. ሚዮ ወረዳ 496 ከብቶች ሞተዋል።
4ኛ. አሬሮ ወረዳ 219 ከብቶች ሞተዋል።
5ኛ. ጉቺ ወረዳ 216 ከብቶች ሞተዋል።
6ኛ. ያቤሎ ወረዳ 116 ከብቶች ሞተዋል።

ያንብቡ 👉 telegra.ph/VOA-10-12

@tikvahethiopia
#Bahirdar : በባህርዳር ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ህገ-ወጥ ሽጉጥ እንዲሁም የብሬን፣ የክላሸና የሽጉጥ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋለ።

በባህር ዳር ከተማ ልዩ ቦታው ዳግማዊ ምንሊክ ክፍለ ከተማ ማርዘነብ ቀበሌ በተባለው ስፍራ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ፦
- 51 ትልቁ ቱርክ ሰራሽ ህገ-ወጥ ሽጉጥ፣
- 2ሺ 1መቶ የብሬን ጥይት፣
- 69 የክላሽ ጥይት እንዲሁም 222 የሽጉጥ ጥይቶች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ አሳውቋል።

የባህር ዳር ፖሊስ ፥ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው የአማራ ክልል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በትብብር መሆኑን ገልጿል።

የባህር ዳር ፖሊስ 9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ንብረቱ ሞት ፥ ህብረተሰቡ ከዚህ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊት እንዲቆጠብ ያሳሰቡ ሲሆን "ህገ-ወጥ ድርጊት ፈፃሚ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በምናውልበት ጊዜ ህዝቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል" ሲሉ ጥሪ አስተላፈዋል።

@tikvahethiopia
#IOM

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) #የኢትዮጵያ ኃላፊ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ "ያልተፈቀደ ቃለ መጠይቆችን" አድርገዋል በሚል የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ መደረጋቸውን AFP ዘገበ።

ኃላፊዋ ማውሪን አቺየንግ ያልተፈቀደ በተባለው ቃለ መጠይቅ ለህወሓት ወገንተኛ ባሏቸው የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ጎን ገሸሽ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

ማውሪን አቺየንግ ምንድነው ያሉት?

ባለፈው ሳምንት ማውሪን አቺየንግናና ሌላ ከፍተኛ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኛ የኢትዮጵያን መንግስት በመደገፍ በርካታ መጣጥፎችን ለሚፅፈው ጄፍ ፒርስ ረዘም ያለ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዋል።

በቃለ መጠይቁ ላይ እንደሚሰማው የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የኢትዮጵያ ኃላፊ ማውሪን ጦርነቱ ከተነሳ በኋላ አዲስ አበባ የገቡ የተባበሩት መንግሥታት የሥራ ባልደረቦቻቸውን በከፍተኛ ሁኔታ በመተቸት መሬት ያሉ የድርጅቱ ተወካዮችን አግልለዋል ብለዋል።

ህወሓትን "ቆሻሻ" እና "ጨካኝ" በማለትም ሲናገሩ ይሰማል።

በአንድ ወቅትም ህወሓት ከሳዑዲ አረቢያ የተባረሩ የትግራይ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ አሲረዋል በማለትም ሲከሱ ይሰማል።

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የነበሩና መውጪያ አጥተው የነበሩ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ ጥያቄ እንደቀረበላቸውና ሩዋንዳም እንዲላኩ የተፈለገው ለሌላ አላማ እንደሆነ ተናግረዋል።

"ወደ ሩዋንዳ እንዲላኩ የተፈለገው የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ ከሩዋንዳ እንዲጀመር" ለማድረግ መሆኑንም ያነሳሉ፤ “እንዲህ ዐይነት ነገር ቆሻሻ ነው” ሲሉ ይደመጣሉ።

ኃላፊዋ በጭራሽ ወደ ትግራይ እንደማይመለሱ ቃል ሲገቡም ይሰማል።

ያንብቡ: https://telegra.ph/AFP-10-12

የመረጃ ባለቤት AFP ነው።

@tikvahethiopia
" ስንት ሰው ሲሞት፣ ስንት ሰው ሲያልቅ ነው የዓለም ማህበረሰብ ወለጋ ላይ ሰው እያለቀ ነው ብሎ ድምፁን የሚያሰማው ? " - የምስራቅ ወለጋ [ሀሮ አዲስ ዓለም] ነዋሪዎች

በምስቅራ ወለጋ [ሀሮ አዲስ ዓለም] በሸኔ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ ሰዎች እየተገደሉ መሆኑን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በምስራቅ ወለጋ ባሉ ወረዳዎች እየተፈፀመ ባለው ጥቃት የትኛውም ኃይል ሊከላከልላቸው እንዳልገባ የሚናገሩት ነዋሪዎች በታቻላቸው አቅም ጥቃቱን ለመቋቋም ቢሞክሩም ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ አስረድተዋል።

የታጣቂዎቹ ጥቃት ከእሁድ ጀምሮ እንደጀመረ የሚገልፁት ነዋሪዎች የፀጥታ ኃይሎች ከአካባቢው ለምን እንደሆነ በማይታወቅ ምክንያት ለቀው እንደወጡ አስረድተዋል፤ የፀጥታ ኃይሎች ከወጡ በኃላ ተኩስ ተከፍቶ ንፁሃን መገደላቸውን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ህዝቡ አሁንም ቶሎ ካልተደረሰለት በቀናት ውስጥ ሁሉንም አንገት የሚያስደፋ ፤ እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ይፈጠራል ሲሉም ሁኔታውን አስረድተዋል።

ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪዎች በኪረሙ የመንግስት መዋቅር ስለመኖሩ በራሱ ያጠራጥራል ያሉ ሲሆን በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ብናደርግም የንፁሃን ሞት መታደግ አልተቻለም ብለዋል።

በአሁን ሰዓት ምስራቅ ወለጋ ሆሮ አዲስ ዓለም ላይ የሰው ሞት ከምንም የማይቆጠርበት ደረጃ ደርሷል፤ አሁንም በችግር ውስጥ ያሉና የቀሩ ዜጎችን መታደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በአሁን ሰዓት በሀሮ ብቻ ከ27 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን በአካባቢው ያለው ህዝብ መንቀሳቀሻም አጥቶ ይገኛል፤ ወደ ጎጃም እንዳይሄድ አጋምሳ ላይ መንገድ ተቆርጧል ፤ ወደ ኪረሙም እንዳይሄድ ኖሌ ላይ መንገድ ተዘግቷል ፤ በዚህ ላይ ህዝቡ ማህበራዊ ቀውሱ በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶታል።

ያንብቡ - telegra.ph/East-Wollega-10-12

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ፦ • ድምፅ ለመስጠት የተመዘገቡ - 1 ሚሊየን 344 ሺህ 622 ዜጎች • ድምፅ የሰጡ ዜጎች - 1 ሚሊየን 262 ሺህ 679 ዜጎች ወይም ከተመዘገቡት 93 ነጥብ 9 በመቶ በዚህ መሰረት ፦ • 1 ሚሊየን 221 ሺህ 92 ዜጎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በሚል የጋራ አንድ ክልል ለመመስረት እደግፋለሁ ሲሉ ወስነዋል። • 24 ሺህ መራጮች በደቡብ ክልል…
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም (በእቅድ ደረጃ ያለ ቀን) መንግስት ለመመስረት ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

ይህን የገለፁት የህዝበ ወሳኔው ማድፈፀሚያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ምትኩ ከድር ናቸው።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት በኩል የሚያልቁ ጉዳዮች አልቀው በጊዜ የደቡብ ክልል መንግስት የስልጣን ርክክብ ማድረግ የሚችል ከሆነ ጥቅምት 29 የክልሉን መንግስት ለመመስረት እቅድ መያዙን ኢ/ር ምትኩ ተናግረዋል።

ኢ/ር ምትኩ ከድር በአሁን ሰዓት ለክልል ምስረታው የሚያስፈልጉ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከሰሞኑን የክልል አደራጅ አብይ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ ስብሰባ አድርጎ የነበረ ሲሆን በፕሮጀክት ፅ/ቤት የተዘጋጀ ረቂቅ ህገ መንግስት ተነልክቶ ለውይይት ወደህዝብ እንዲወርድ መደረጉን አንስተዋል።

በየዞን እና ወረዳው ህዝባዊ ውይይት የሚደረግም ይሆናል።

- የክልሉ ስያሜ
- ክልሉ የስራ ቋንቋ
- ሰንደቅ ዓላማ
- የህዝብ መዝሙር
- አስተዳደራዊ አደረጃጀት የሚመለከቱ ጉዳዮችን የያዘ ሰነድ እና ስምምነት የደረሰባቸው ጉዳዮች በየመዋቅሩ ያሉ የህዝብ ተወካዮች እንዲመክሩበት ወደታች ወርዷል።

የአዲሱ የክልል መንግስት የአስተዳደር መቀመጫን በሚመለከት ከዓለም የፌዴሬሽን መንግሥታት በተወሰዱ ልምዶች ከአንድ በላይ የሆነ የብዝሃ ማዕከላት አካሄድን ለመከተል የሚያስችል ጥናት ቀርቦ ሀሳብ እየተሰጠበት እንደሚገኝ ኢ/ር ምትኩ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሐረሪ፣ የሶማሌ እና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልሎች ላይ አጠቃላይ ምርጫ የተከናወባቸው ምርጫ ክልሎች ውጤት መግለጫ !

@tikvahethiopia
#KENYA #SOMALIA

ኬንያና ሶማሊያን ሲያወዛግብ በቆየው የባሕር ላይ ይዞታ ይገባኛል ጉዳይ ላይ ኔዘርላንድስ ዘ ሔግ የተሰየመው ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍ/ቤት ብይን ሰጠ።

በተፈጥሮ ሀብት የታደለ ነው የተባለውን አወዛጋቢ የውቅያኖስ ላይ ግዛትን ሁለቱ አገራት እንዲካፈሉት ጉዳዩን የተመለከቱት ፍርድ ቤት አስር ለአራት በሆነ ድምጽ ውሳኔ ሰጥቷል።

የባሕር ላይ ይዞታውን በተመለከተ ኬንያ በትይዩ ያለውን ድንበር ከሶማሊያ ጋር ከስምምነት ላይ መድረሷን ያቀረበችውን መከራከሪያ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።

በተጨማሪም በውቅያኖስ ክልሉ ውስጥ ኬንያ የነዳጅ ፍለጋና ቁፋሮ ተግባርን በማከናወን ዓለም አቀፍ ሕጎችን ጥሳለች በማለት ሶማሊያ ያቀረበችውን ክስ ፍርድ ቤቱ ውድቅ በማድረግ የካሳ ጥያቄዋን ሳይቀበለው ቀርቷል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስር የሚገኘው ይህ ፍርድ ቤት የባሕር ጠረፍ ውዝግቡን በተመለከተ የሰጠው ውሳኔ በአብዛኛው የሶማሊያን ፍላጎት የሚያሟላ መሆኑ ተገልጿል።

ቀደም ሲል ኬንያ ዓለም አቀፉን ፍርድ ቤት በወገንተኝነት በመክሰስ የሚሰጠውን ውሳኔ እንደማትቀበለው አሳውቃ ነበር።

ሁለቱ አገራት በይገባኛል የሚወዛገቡበት በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ያለው 100,000 ስኩዌር ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን የውሃ አካል ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ አለበት ተብሎ ይታሰባል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 40 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 40 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 7,126 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 842 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 715 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia