TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሹመታቸው የፀደቀላቸው የካቢኔ አባላት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። አዲስ የተሾሙት ሚኒስትሮች ዝርዝር ፦ 1. አቶ ደመቀ መኮንን - የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር 2. ዶ/ር አብርሃም በላይ - የሃገር መከላከያ ሚኒስትር 3. አቶ አህመድ ሽዴ - የገንዘብ ሚኒስትር 4. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል - የስራና ክህሎት ሚኒስትር 5. አቶ ኡመር…
#DrEngSeleshiBekele

" በቀጣይ አገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል " - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ለአዳዲሶቹ ሚኒስትሮች ለኢ/ር አይሻ መሀመድ እና ለዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢቲፋ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ።

ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ፤ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚ/ር እና ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚ/ር ሆነው በመሾማቸው "እንኳን ደስ አላችሁ" ብለዋል።

አክለው ፤ " ላለፉት 5 አመታት ስመራው የነበረው የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚ/ር ዛሬ በጸደቀው የአስፈጻሚ መ/ቤቶች አደረጃጀት መሰረት በመሾማችሁ በጣም ደስ በሎኛል" ሲሉ ፅፈዋል።

" ሁለቱም ዘርፎች ለአገራችን ማደግ እና መለውጥ ወሳኝ ተቋማት ናቸው " ያሉት ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ ፤ "በውጤታማነት እንደምትመሩ ባለሙሉ እምነት ነኝ፡፡ የበኩሌ ድጋፍም ሁሌም አይለያችሁም" ሲሉ ገልፀዋል።

"ያደረግሁት አስተዋጽኦ በፈታኞቹ ወቅቶችና ሰአታት አገሬን ቀና አድርጓታል ብዬ አምናለሁ፡፡ በቀጣይ አገሬ በምትፈልገኝ አገልግሎት የምሰማራ ይሆናል፤ ለነበረኝ ትልቅ ሃላፊነትና ለተደረገልኝ ትብብር አመሰግናለሁ" ሲሉም ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም ፥ "አገራችን ኢትዮጵያን ፈጣሪ ይጠብቃት፡፡ ኢትዮጵያችን እንደ ገናና ታሪኳ ሁሉ ጸንታ ትኖራለች" ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።

@tikvahethiopia
ኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ የ"ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ" እንዲሆን ተወሠነ።

"ኢትዮጵያ አንድ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ያስፈልጋታል" ከሚለው መነሻ ውሳኔ ላይ መደረሱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ተጠሪነትም ለትምህርት ሚኒስቴር እንዲሆን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ መደንገጉንም ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#SemiraMohammed

ከሰሞኑን በአንድ ቪድዮ ላይ ልጇ ፊት በፖሊስ አባላት ስትደበብ የተመለከትናት ሰሚራ መሐመድ የስራ ዕድል እንደተፈጠረላት ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ተሰምቷል።

ግለሰቧ በልመና ላይ ተሰማርታ በነበረበት ወቅት በፖሊስ አባላት በርካቶችን ያስቆጣ ኢሰብዓዊ ድርጊት ከተፈፀመባት በኃላ የከተማ አስተዳደሩ በከንቲባ አዳነች አቤቤ አማካኝነት ለግለሰቧ የስራ እድል እንደሚመቻች አሳውቆ ነበር።

ዛሬ እንደተሰማው ግለሰቧ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ተስፋ ብርሐን የምገባ ማዕከል የስራ ዕድል ተፈጥሮላት የስራ ቅጥር ውል ፈርማለች።

በርካቶች በከተማ አስተዳደሩ የተወሰደውን እርምጃ ያወደሱት ሲሆን በሌሎችም ዜጎች ላይ መሰል ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ ንቁ ክትትል ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ሰሚራ ላይ የደረሰው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በቪድዮ ተቀርፆ የተሰራጨ በመሆኑ ነው እንጂ በየመንደሩ የሚፈፀሙ ብዙ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ የሚመለከተው አካል በስነምግባር የታነፁ የፖሊስ አባላትን በማፍራቱ ዙሪያ እንዲሁም በህገወጥ ድርጊት የተሰማሩትን አባላት ለይቶ ለህግ የማቅረቡን ስራ አጠናክሮ መስራት ይኖርበታል።

ዜጎች ጥቆማ ከመስጠት ባለፈ የሚመለከቱትን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በእጅ ስልኮቻቸው በመቅረፅና በማሰራጨት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የሚፈፅሙ አካላትን ማጋለጥ አለባቸው።

የሰሚራ መሐመድ ጉዳይ በእጅጉ የማህበራዊ ሚዲያን ኃያልነት ያስመሰከረና ማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎ ነገር ማዋል ከተቻለ ብዙ የሀገር ችግሮች ማስተካከል እንደሚቻል ማሳያ ሆኖ ያለፈ ነው።

@tikvahethiopia
#Facebook

የቀድሞው የፌስቡክ ሠራተኛ ፍራንሲስ ሐውገን የፌስቡክን ሚስጥር አጋልጠዋል።

ፌስቡክ ኢትዮጵያን🇪🇹ጨምሮ በሌሎችም አገራት ሐሰተኛ መረጃና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን እንዳላስቆመ በይፋ ተናግረዋል።

የአሜሪካ ኮንግረስ ፊት ቀርበው ቃላቸውን የሰጡት ፍራንሲስ ሐውገን ፌስቡክ በኢትዮጵያና በምያንማር ግጭት ቀስቃሽ እና ሐሰተኛ መረጃዎችን ሳያስቆም ቀርቷል ብለዋል።

"እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ አሁን ላይ የምናያቸው ጽንፈኛ ድርጊቶች እየተባባሱ ይሄዳሉ ብዬ እፈራለሁ። በኢትዮጵያና በምያንማር ያየናቸው ነገሮች ወደባሰ ደረጃ የሚደርሱ፣ የአስፈሪ ታሪክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ናቸው" ብለዋል።

ፌስቡክ ሐሰተኛ መረጃዎችን፣ ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን እንዲሁም የጥላቻ ንግግሮችን ከመሰራጨት ማስቆም እንዳልቻለ ተናግረዋል።

የ37 ዓመቷ የቀድሞው የፌስቡክ ፕሮዳክት ማናጀር በአሜሪካ ምክር ቤት ተገኝተው ቃላቸውን ሲሰጡ ድርጅቱን በጽኑ ወቅሰዋል።

ፌስቡክ ለሚለጠፉት መልዕክቶች ኃላፊነት እንዲወስድ መደረግ እንዳለበት ለኮሚቴው ባደረጉት ንግግር ጠቁመዋል።

ፌስቡክን ተጠያቂ ማድረግ የሐሰተኛ መረጃ ስርጨትን እንደሚገታ አልፎም ግጭት እንዳይነሳ እንደሚከላከል ተናግረዋል።

ፌስቡክ በአምባገነን እና የሽብር ድርጅት መሪዎች ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ በንግግራቸው አጋልጠዋል። እነዚህ አካሎች እየተጠቀሙበት እንደሆነ ፌስቡክ መረጃው እንዳለውም አክለዋል።

የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይክና ሼር እንዲያደርጉ እንዲሁም አስተያየት እንዲሰጡ የሚያነሳሱ ጽሑፎች በገጹ ወደላይ እንደሚገፉ ተናግረዋል።

"እነዚህ መልዕክቶች እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በብሔር ክፍፍል የሚናጡ አገሮች ውስጥ ግጭት እያስነሱ ነው" ሲሉ አብራርተዋል።

ፌስቡክ ክሱን ውድቅ አድርጓል።

ያንብቡ : telegra.ph/BBC-10-06

@tikvahethiopi
#UNSC

ዛሬ ተመድ ፥ "Peace and Security in Africa" በሚል የውይይት አጀንዳ ስር በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው ሁኔታ ለውይይት እንደሚቀመጥ ቢቢሲ ዘግቧል።

በዚህ ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካዮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ክፍት ስብሰባም እንደሚሆን ተነግሯል።

ውይይቱ እንዲካሄድ የጠየቁት አሜሪካ፣ ዩኬ፣ ኖርዌይ፣ ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ እና አየርላንድ ናቸው።

በዛሬው ስብሰባ የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ንግግራቸው 7ቱ የድርጅታቸው ሠራተኞች ከኢትዮጵያ መውጣታቸውን በተመለከተ እና በሰብአዊ ቀውስ ጉዳይ ነው ተብሎ የሚጠበቀው።

ተመድ የትግራይ ክልል ጦርነት ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ሲቀመጥ ይኸኛው ለ10 ጊዜው ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 32 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 32 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 9,216 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 1,134 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 765 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ የተናገሩትን ንግግር አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ዛሬ በተካሄደው 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱልቃድርን ለአዲስ አበባ ም/ቤት የካቢኔ አባልነት ተጠይቀው ፓርቲያቸው እንዳልፈቀደ ተናግረው ነበር።

ይህን ተከትሎ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ብልፅግና ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ያለውን ፍላጎት አድንቆ ለሀገሪቱ ፖለቲካ ጠቃሚ በመሆኑ ደግፋለሁኝ ብሏል።

ፓርቲው በአዲስ አበባ ካቢኔ ውስጥ ለመሳተፍ ስምምነቱን የገለፀ ሲሆን ከአፈፃፀም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ከብልፅግና ጋር ውይይት ማድረጉን አሳውቋል።

በተደረገው ውይይትም በአ/አ ካቢኔ ውስጥ እንዲሳተፉ የተጠየቁት የፓርቲው ሊቀመንበር ምትክ ሌላ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር እንዲሳተፉ ከብልፅግና ጋር ስምምነት መደረሱን አስታውሶ ፓርቲውን ወክለው በአ/አ ካቢኔ አባል እንዲሆኑ የተመረጡት የነእፓ አመራር ለብልፅግና እንዳሳወቀ በመገለጫው ጠቅሷል።

ይሁን እንጂ ነእፓ መርጦ የላካቸው የፓርቲው ተወካይ በካቢኔው ሳይካተቱ መቅረታቸውን ገልጿል፤ይህንንም በተመለከተ ከብልፅግና የተሰጠው ማብራሪያ እንደሌለም አሳውቋል።

ፓርቲው ሀገርን በጋራ ለማገልገል ተፎካካሪዎች በመንግስት ስልጣን እንዲሳተፉ በብልፅግና የተሰጠው እድልን አድንቆ በሀገሪቱ የመንግስት ታሪክ አዲስ አሰራር በመሆኑ ከገዢው ፓርቲ ጋር አብሮ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት አረጋግጧል።

ነገር ይህ አዲስ አሰራር ተግባራዊ ሲደረግ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሂደቱ በግልፅ እንዲሳተፉ ማድረግ በሀገር ደረጃ ለታሰበው አዲስ የፖለቲካ ባህል ውጤታማነት አስፈላጊ ነው ብሏል።

@tikvahethiopia
" አዲሱ መንግስት የስም ብቻ ሳይሆን የግብርም አዲስነት እንዲያሳይ ሕዝብ ይጠብቃል " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ ፤ አዲሱ መንግስት የስም ብቻ ሳይሆን የግብርም አዲስነት ተለንሶ ሀገሪቱን ከተጋረጡባት ችግሮች እንዲያወጣ አሳሰበ።

እናት ፓርቲ ይህን ያለው ከአዲስ መንግስት ምስረታ ጋር በተያያዘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ነው።

ፓርቲው በመግለጫው ፥ በአዲስ መለክ የተዋቀረው መንግስት የስም ብቻ ሳይሆን የግብር አዲስነትን ተላብሶ ኢትዮጵያን ከተጋረጡባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዲያወጣ ያሳሰበ ሲሆን " መንግሥት ይህን ለማድረግ ትንሽዋን ቀናነት ሲያሳይ የሕዝብ የጎላ ድጋፍ እንደሚቸረው እምነታችን ነው" ብሏል።

ሕዝቡ መንግሥት ለሚያደርገው በጎ ተግባር ሙሉ ድጋፉን እንዲሰጥ፤ ባለማወቅ ለሚፈጽማቸው ስህተቶች ገንቢ የእርምት አስተያየቶችን፣ በማን አለብኝነት ለሚሠራው ጥፋት ደግሞ በድፍረት ይህ አይደረግም/አይሆንም እንዲል እናት ፓርቲ መልዕክት አስተላልፏል።

ፓርቲው በየደረጃው በአገልጋይነት የተሾሙትን ሁሉ " እንኳን ደስ አላችሁ " ያለ ሲሆን ለተሻሚዎች በሙሉ መልካም የአገልግሎት ዘመን እንዲሆን ምኞቱን ገልጿል።

* የእናት ፓርቲ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያው ከፍተኛ ባለስልጣን #ፌስቡክ መረጃዬን አሳልፎ ሰጠብኝ አሉ።

ዛሬ ምሽት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋ/ዳሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ''ሀክ ተደረጉ'' ከሚል ጹሑፍ ጋር ተንቀሳቃሽ ምስሎች ተለጥፈው ነበር።

ይህ ከሆነ ከደቂቃዎች በኃላ ዳሬክተሩ፥ ''ለግንዛቤያችሁ'' ብለው ባሰፈሩት መልዕከት ይፋዊ የፌስቡክ አካውንታቸው ''በውጭ አካላት ሃክ አልተደረገም'' ብለዋል።

የተለቀቀው ቪዲዮም ከ1 ዓመት በፊት ፌስቡክ የመልዕክት መላኪያ መተግበሪያ (Messenger) አማካኝነት ከጓደኞቻቸው ጋር ያወሩት እንደሆነ ገልጸዋል።

ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ''ፌስቡክ መዝግቦ ያስቀመጠውን መረጃ (Password, Username) እንዴት አሳልፎ እንደሰጠና በዚህም ግለሰብንና ሀገርን ለማሳጣት የተደረገውን የቴክኖሎጂ ውንብድና በህግ አግባብ እንሄድበታለን'' ሲሉ በጹሑፋቸው ገልጸዋል።

በገጻቸው ላይ ለተለጠፈው ተንቀሳቃሽ ምስልም ፌስቡክን መረጃዬን አሳልፎ በመስጠቱ ነው ሲሉም አስረድተዋል።

''የኛ Username እና password እነርሱ ጋር ስለሚገኝ ይህንን ማድረግ ተገቢ አይደለም። ጠላትነታችን እዚህ የደረሰ አልመሠለኝም ነበር'' ይላል አጭር ያሰፈሩት ጹሑፍ።

ተንቀሳቃሽ ምስሉ ዳይሬክተሩ ለጓደኞቻቸው በፊት ለፊት ካሜራ ቀርጸው የላኩት ''አታስቀኑኝ በርሬ መጣለው'' የሚል መልዕክት የያዘ ሲሆን በገጻቸው ላይ በተደጋጋሚ ''ሹመቴ ግዛው ሀክ ተደረገ'' የሚል የሥላቅ መልዕክት ታክሎበት በገጹ ለደቂቃዎች ተለጥፎ ነበር።

አሁን ተንቀሳቃሽ ምስሎቹ ከገጹ የጠፉ ሲሆን ሂደቱን በህግ እንደሚከታተሉም ዶ/ር ሹመቴ አስታውቀዋል።

ዶ/ር ሹመቴ ከ2012 ጀምሮ የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ በመካሄድ ላይ ሲሆን በተመድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ለምክር ቤቱ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። የዛሬው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ክፍት ሲሆን በተመድ (UN) ይፋዊ የ #YouTube ቻናል መከታተል ይቻላል : https://youtu.be/cX2tXnUL-cY @tikvahethiopia
የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን አለ ?

የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ሲቀመጥ ሁለት (2) ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ይኸኛው ለአራተኛ (4) ጊዜ (በዝግና በክፍት) ነው።

ይኸኛው ስብሰባው ለምን ተጠራ ?

- ኢትዮጵያ 7 የተመድ ሰራተኞችን ከሀገር በማስወጣቷ።
- የሰሜን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየት።

ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት፦ አሜሪካ ፣ ዩኬ (UK)፣ ኖርዌይ ፣ ኢስቶኒያ ፣ ፈረንሳይ እና አየርላንድ ናቸው።

በስብሰባው ላይ የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ንግግር አድርገዋል።

የምክር ቤቱ አባል ሀገራት የተለያዩ ሀሳቦችን ሰንዝረዋል።

ሙሉ ውይይቱን (ክፍት ውይይት ስለሆነ) በተመድ የYouTube ቻናል ማግኘት እንደምትችሉ እየጠቆምን የተነሱ ዋና ሃሳቦችን ግን በአጭሩ እንዳስሳለን።

ይህን ተጭነው ያንብቡ (Instant View)👇
https://telegra.ph/UNSC-10-07
TIKVAH-ETHIOPIA
የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን አለ ? የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ሲቀመጥ ሁለት (2) ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ይኸኛው ለአራተኛ (4) ጊዜ (በዝግና በክፍት) ነው። ይኸኛው ስብሰባው ለምን ተጠራ ? - ኢትዮጵያ 7 የተመድ ሰራተኞችን ከሀገር በማስወጣቷ። - የሰሜን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየት። ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት፦ አሜሪካ ፣ ዩኬ (UK)፣…
#UNSC

ትላንት በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያ በተመድ ሰራተኞች ላይ ስለወሰደውች እርምጃ ማብራሪያ የሰጡት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ፥ በዓለም አቀፍ ህግ ሀገራት መብቶቻቸውን መጠቀም ይችላሉ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለውሳኔውም ምንም አይነት ማብራሪያ የማቅረብ ግዴታ የለበትም ብለዋል።

ሀገራት የተለያዩ የተመድ ሰራተኞችን እና የሀገራት ዲፕሎማቶችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከሀገራቸው ማስወጣታቸውን እናውቃለን፤ ሆኖም ግን ተመድ በእነሱ ላይ ስብሰባ አድርጎ ያውቅ ይሆን ? ሲሉ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እርምጃውን ስለ መውሰዱ ለማንኛውም አካል ማብራሪያ የመስጠት ግዴታ የለበትም ሲሉ ተናግረዋል።

የተመድ ሰራተኞች የገለልተኝነት መርሆችን በጣሰ መልኩ ለህወሓት የሚወግኑ መሆናቸውን ገልፀዋል። 

የተመድ ሰራተኞች ያልሞቱ ሰዎችን በረሃብ ሞተዋል በሚል የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨት፤ የመገናኛ መሣሪያዎችን ለህወሓት ወገን ማድረስ፤ ህወሃት መቐለ ሲገባ ከቡድኑ ጋር ደስታቸውን መግለጽ ፤ ከሳዑዲ የትግራይ ተወላጆችን ወደ ሶስተኛ ሀገር በማምጣት ለቡድኑ እንዲዋጉ ስልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸትና ህወሓትን የሚደግፉ ጹሑፎችን ማዘገጀት ላይ ተጠምደው ነበር ብለዋል።

ማን ይገባል፤ ማን ይወጣል ፣ ማን ይቆያል የሚለውን የሀገር መሰረታዊ ሉዓላዊ መብት ነው ብለዋል።

የመረጃ ግብአ አልዓይን ፣ ቪኦኤ፣ የUN ገፅ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን አለ ? የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ሲቀመጥ ሁለት (2) ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ይኸኛው ለአራተኛ (4) ጊዜ (በዝግና በክፍት) ነው። ይኸኛው ስብሰባው ለምን ተጠራ ? - ኢትዮጵያ 7 የተመድ ሰራተኞችን ከሀገር በማስወጣቷ። - የሰሜን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየት። ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት፦ አሜሪካ ፣ ዩኬ (UK)፣…
በትላንቱ ስብሰባ ...

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፦

ከኢትዮጵያ ጋር የተዋጣ ግንኙነት እንዲኖር ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አሁንም እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

እንደውም ለኢትዮጵያ መንግስት ታደላለህ በሚል ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲወቅሱኝ ቆይተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ለአምባሳደር ታዬ ባቀረቡት ጥያቄም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን ድረስ ለተመድ የገባ ደብዳቤ የለም፤ ከተባረሩት 7 የተመድ ሰራተኞች በአንዱም ላይ ቢሆን አንድም ደብዳቤ ካለ ያቅርቡልኝ ፤ የማውቀው ነገር የለም ስለሚባለው ክስ ብለዋል።

ገተሬዝ በግልፅ ፥ የተመድ ባለስጣናት እና ሰራተኞቹን ኢትዮጵያ የማባረር መብት የላትም ያሉ ሲሆን ግለሰቦቹን በማባረር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ህግ ጥሳለች ብለዋል።

ማንኛውም የተመድ አባል ከስነ ምግባር ውጭ ያደረገው ምንም አድራጎት ካለ እንድናውቅ እንፈልጋለን ሲሉም ተደምጠዋል።

አጀንዳችን አንድ ብቻ ነው እሱም "የኢትዮጵያ ህዝብ መከራ እንዲያበቃ እንፈልጋለን" ይህ ነው አጀንዳችን ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ፦

ንግግሮች መደረግ ያለባቸው በኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መካከል እንዲሆን ጠይቀው አፋጠነው ማስረጃውን ለማቅረብ እንደሚሰሩ ገልፀዋል። እንዲሁም ሀሳብዎት እና ልቦናዎት ከኛ ጋር በመሆኑ እናደንቃለን ብለዋል።

የመረጃ ግብአት ቪኦኤና የUN ገፅ።

@tikvahethiopia