TIKVAH-ETHIOPIA
የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን አለ ? የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ስብሰባ ሲቀመጥ ሁለት (2) ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ይኸኛው ለአራተኛ (4) ጊዜ (በዝግና በክፍት) ነው። ይኸኛው ስብሰባው ለምን ተጠራ ? - ኢትዮጵያ 7 የተመድ ሰራተኞችን ከሀገር በማስወጣቷ። - የሰሜን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየት። ስብሰባው እንዲካሄድ የጠየቁት፦ አሜሪካ ፣ ዩኬ (UK)፣…
በትላንቱ ስብሰባ ...

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፦

ከኢትዮጵያ ጋር የተዋጣ ግንኙነት እንዲኖር ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን አሁንም እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

እንደውም ለኢትዮጵያ መንግስት ታደላለህ በሚል ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሲወቅሱኝ ቆይተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ለአምባሳደር ታዬ ባቀረቡት ጥያቄም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እስካሁን ድረስ ለተመድ የገባ ደብዳቤ የለም፤ ከተባረሩት 7 የተመድ ሰራተኞች በአንዱም ላይ ቢሆን አንድም ደብዳቤ ካለ ያቅርቡልኝ ፤ የማውቀው ነገር የለም ስለሚባለው ክስ ብለዋል።

ገተሬዝ በግልፅ ፥ የተመድ ባለስጣናት እና ሰራተኞቹን ኢትዮጵያ የማባረር መብት የላትም ያሉ ሲሆን ግለሰቦቹን በማባረር ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ህግ ጥሳለች ብለዋል።

ማንኛውም የተመድ አባል ከስነ ምግባር ውጭ ያደረገው ምንም አድራጎት ካለ እንድናውቅ እንፈልጋለን ሲሉም ተደምጠዋል።

አጀንዳችን አንድ ብቻ ነው እሱም "የኢትዮጵያ ህዝብ መከራ እንዲያበቃ እንፈልጋለን" ይህ ነው አጀንዳችን ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ፦

ንግግሮች መደረግ ያለባቸው በኢትዮጵያ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መካከል እንዲሆን ጠይቀው አፋጠነው ማስረጃውን ለማቅረብ እንደሚሰሩ ገልፀዋል። እንዲሁም ሀሳብዎት እና ልቦናዎት ከኛ ጋር በመሆኑ እናደንቃለን ብለዋል።

የመረጃ ግብአት ቪኦኤና የUN ገፅ።

@tikvahethiopia