#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ የተናገሩትን ንግግር አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ዛሬ በተካሄደው 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብዱልቃድርን ለአዲስ አበባ ም/ቤት የካቢኔ አባልነት ተጠይቀው ፓርቲያቸው እንዳልፈቀደ ተናግረው ነበር።

ይህን ተከትሎ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ብልፅግና ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ያለውን ፍላጎት አድንቆ ለሀገሪቱ ፖለቲካ ጠቃሚ በመሆኑ ደግፋለሁኝ ብሏል።

ፓርቲው በአዲስ አበባ ካቢኔ ውስጥ ለመሳተፍ ስምምነቱን የገለፀ ሲሆን ከአፈፃፀም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ከብልፅግና ጋር ውይይት ማድረጉን አሳውቋል።

በተደረገው ውይይትም በአ/አ ካቢኔ ውስጥ እንዲሳተፉ የተጠየቁት የፓርቲው ሊቀመንበር ምትክ ሌላ የፓርቲው ከፍተኛ አመራር እንዲሳተፉ ከብልፅግና ጋር ስምምነት መደረሱን አስታውሶ ፓርቲውን ወክለው በአ/አ ካቢኔ አባል እንዲሆኑ የተመረጡት የነእፓ አመራር ለብልፅግና እንዳሳወቀ በመገለጫው ጠቅሷል።

ይሁን እንጂ ነእፓ መርጦ የላካቸው የፓርቲው ተወካይ በካቢኔው ሳይካተቱ መቅረታቸውን ገልጿል፤ይህንንም በተመለከተ ከብልፅግና የተሰጠው ማብራሪያ እንደሌለም አሳውቋል።

ፓርቲው ሀገርን በጋራ ለማገልገል ተፎካካሪዎች በመንግስት ስልጣን እንዲሳተፉ በብልፅግና የተሰጠው እድልን አድንቆ በሀገሪቱ የመንግስት ታሪክ አዲስ አሰራር በመሆኑ ከገዢው ፓርቲ ጋር አብሮ ለመስራት ያለውን ዝግጁነት አረጋግጧል።

ነገር ይህ አዲስ አሰራር ተግባራዊ ሲደረግ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሂደቱ በግልፅ እንዲሳተፉ ማድረግ በሀገር ደረጃ ለታሰበው አዲስ የፖለቲካ ባህል ውጤታማነት አስፈላጊ ነው ብሏል።

@tikvahethiopia