TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WFP

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት የተናጠል ተኩስ ካቆመበትና መከላከያ ሰራዊቱን ከትግራይ ካስወጣበት ጊዜ ጀምሮ የአለም የምግብ ፕሮጋራም (WFP) አውሮፕላን ለሁለተኛ ጊዜ የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረስ ከቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መቐለ ዛሬ በረራ ያደርጋል።

በዚህ በረራም ከ30 በላይ ግለሰቦችና የተራድኦ ድርጅቱ ሰራተኞች ጉዞ ያደርጋሉ፡፡

@tikvahethiopia
#WFP #Tigray

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌይ ፥ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ትግራይ ውስጥ የሚያደርሰው የምግብ ድጋፍ አቅርቦት በዚህ አርብ እንደሚያልቅበት ገለፁ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በትግራይ ውስጥ ሊመግብ ላሰባቸው ሰዎች ሁሉ ለመድረስ በቀን 100 የጭነት ተሽከርካሪዎች እንደሚያስፈልገው አንስተዋል።

ባስሌይ ፥ "ለትግራይ ምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶች የያዙ 170 ተሽከርካሪዎች በአሁን ሰዓት አፋር ይገኛሉ፤ መንቀሳቀስም አልቻሉም ፤ አሁኑኑ እነዚህ ተሽከርካሪዎች እንዲንቀሳቀሱ መፈቀድ አለበት ፤ ሰዎች እየተራቡ ነው" ብለዋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#WFP : የዓለም ምግብ ፕሮግራም /WFP/ ባለፉት ጥቂት ቀናት 61 ተሽከርካሪዎች ከትግራይ ክልል መመለሳቸውን አሳውቋል ፤ በቀጣዮቹ ቀናት/ሳምንታት ተጨማሪ ተሽከርካሪዎች ይመለሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።

ድርጅቱ ፥ ተሽከርካሪዎቹ ጉዟቸውን መቀጠላቸውን ለማረጋገጥ ፣ የሰብአዊ ዕርዳታ አቅርቦትን ለማመቻቸት ማንኛውም የሎጅስቲክስ ችግር ለመቅረፍ ከአጓጓዦች ጋር መስራቱን እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ባለፉት 3 ሳምንታት 6,150 ሜትሪክ ቶን ምግብ የጫኑ 5 ኮንቮዮች - 171 የጭነት ተሽከርካሪዎች ትግራይ መግባታቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም የገለፀ ሲሆን ለአንድ ወር 350,000 ሰዎችን ለመመገብ በቂ መሆኑን ጠቅሷል።

አክሎም ፥ " ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ለማድረስ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ነፃ የእርዳታ ፍሰት መኖሩ አስፈላጊ ነው" ብሏል።

@tikvahethiopia
#WFP : በአፋር እና አማራ ክልሎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች፤ የመጀመርያ ዙር የምግብ እርዳታ ማዳረሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አሳውቋል።

ድርጅቱ በግጭት ምክንያት እርዳታዎችን ማዳረስ ያልተቻለባቸው ቦታዎች ቢኖሩም 2,200 ሜትሪክ ቶን የሚገመት የምግብ እርዳታ ወደ ዋግኸምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች ሊያድርስ መቻሉን ገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር የእርዳታ ስርጭት 210 ሺ ሰዎች ለመርዳት እንደተቻለ ድርጅቱ አሳውቋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፥ በአፋር ክልል 80 ሺ ሰዎች እርዳታ ማግኘታቸውን ገልፆ ካለው የችግሩ መጠን አንጻር በቀጣይ ዙር የሚረዱ ዜጎች ቁጥር ወደ 500 ሺ ሊያሻቅብ እንደሚችል ጠቁሟል።

እአአ ከነሃሴ 15 ወዲህ በአማራና አፋር ክልሎች ለሚገኙ 300 ሺ ተፈናቃዮች የሰብዓዊ እርዳታ መዳረሱንም ገልጿል።

ለትግራይ ክልል የሚደረገው እርዳታ በተመለከተ “በተለያዩ እንቅፋቶች፤ የሰብዓዊ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች እንደፈለጉ መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ምክንያት ወደ ኋላ ቀርቷል” ብሏል።

ከግንቦት 27 ወዲህ ከሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ ትግራይ ተፈናቅለው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች እርዳታ ማዳረሱን ገልጿል፡፡

“እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 200 ሺ ህጻናት እና እድሜያቸው ከ39 እስከ 71 የሆኑ ነፍሰጡር እና አጥቢ እናቶች” የተመጣጠነ የምግብ እርዳታን ካገኙ የትግራይ ተፈናቃዮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

የድርጅቱ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚካኤል ዱንፎርድ ፥ “ሪፖርቶች እንደሚያመክቱት ከሆነ ፤ባለው ሁኔታ በርካታ ቤተሰቦች ከቤታቸው እየሸሹ በመሆናቸው በሶስቱም ክልሎች ያለው የምግብ እጥረት ሁኔታ እየጨመረ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

Credit : www.wfp.org / አል ዓይን

@tikvahethiopia
#WFP #USAID

USAID በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አቁሞ ከአገሪቱ ሊወጣ ነው የተባለ ሐሰት ነው ሲል አስታወቀ።

ድርጅቱ ይህን ያሳወቀው ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ነው።

USAID እየተካሄደ ባለው ጦርነት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ለሚገኙ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ አቅርቦቶችን ማቅረብ መቀጠሉን አስታውቋል።

የተቋሙ ቃል አቀባይ ሬቤካ ክሊፍ ፥ " የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሠራተኞቻችን ከአገሪቱ ቢወጡም፤ በሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ላይ ከሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ጋር በቅርበት እየሰራን እንገኛለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፦የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር በሚገኘው ኮምቦልቻ ውስጥ ያሉት የሰብዓዊ እርዳታ ማከማቻ መጋዘኖቹ መዘረፋቸውን ዛሬ ገልጿል።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ቶምሰን ፊሪ ፥ ባለፈው ሳምንት የዓለም ምግብ ድርጅት በአማራ ክልል ኮምቦልቻ የሰብዓዊ እርዳቃ እንዲያቀርብ ፍቃድ አግኝቷል ብለዋል።

ድርጅቱ ባደረገው ቅድመ ግምገማ መሠረት በርካታ ንብረቶቹ መውደማቸውን እና መጋዘኖች ውስጥ የነበረ እህልም መዘረፉን አሳይቷል ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
#WFP

በትላንትናው ዕለት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (የዓለም ምግብ ፕሮግራም) ቃል አቀባይ ቶመሰን ፉሪ በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

• ከጦርነት ጋር በተያያዘ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 9.4 ሚሊዮን ደርሷል።

• የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች ወስጥ የሚገኙ 9.4 ሚሊዮን ሰዎች አስከፊ ሕይወት እየገፉ ነው።

• 7.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በጦርነቱ ምክንያት ሰብአዊ እርዳታ ማድረስ አዳጋች የሆኑባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ሰዎች ናቸው።

• የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ለውጥ የታየበት #በአማራ_ክልል ነው። በአሁኑ ጊዜ በአማራ ክልል ብቻ 3.7 ሚሊዮን ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

• ከትግራይ፣ ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች የተሰበሰቡ መረጃዎች እንዳመለከቱት በሦስቱ ክልሎች ከሚገኙ ሕጻናት መካከል ከ16 እስከ 18 በመቶ የሚሆኑት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል። ነፍሰጡር ከሆኑ እና ከሚያጠቡት እናቶች መካከል 50 በመቶ ያህሉ በተመሳሳይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አጋጥሟቸዋል።

• UN የምግብ አቅርቦት የጫኑ ተሸከርካሪዎች ከኮምቦልቻ ወደ ደቡባዊ ትግራይ እየላከ ነው። በቀጣይ ቀናት 2200 ሜትሪክ ቶን ሕይወት አደን ምግብ መቐለ ይደርሳል።

WFP በትግራይ 2.5 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር መድረስ ሲኖርበት እስካሁን መድረስ የቻለው 180 ሺህ የሚሆኑትን ብቻ ነው።

ምንጭ፦ https://www.wfp.org/news/millions-more-need-food-assistance-direct-result-conflict-northern-ethiopia-says-wfp

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በሰሜን ኢትዮጵያ ሰብአዊ ድጋፍ ፍላጎቶች እየጨመሩ መሆኑን ገልጿል።

በአፋር ክልል ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ከ30% በላይ መሆኑንም አመልክቷል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ከሚገኙ ማህበረሰቦች፣ ከክልሉ ባለሥልጣናት እና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ወሳኝ የሆነ የምግብ ድጋፍ ለማድረስ በቅርበት እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" እርዳታ የጫኑ ከ150 በላይ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደርሰዋል " - ስቴፋን ዱጃሪች

እርዳታ የጫኑ ከ150 በላይ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቐለ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ትናንት በሰጡት መግለጫቸው ፥ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ከ5 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ የሚፈልገውን መጠነ ሰፊ እርዳታ በየእለቱ እየላከ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በአካባቢው ባለ ግጭት ወደ አንድ ወር ለተጠጋ ጊዜ ወደ ትግራይ የሚያስገባው መንገድ ተዘግቶ የቆየ መሆኑን ያስታወሱት ቃል አቀባዩ ወደ በአማራ ክልልም በደሴ እና በኮምቦልቻ ለሚገኙ 100 ሺህ ተፈናቆዮች ባላፈው ሳምንት የምግብ እርዳታ መከፋፈሉን ተናግረዋል፡፡

በእነዚህ ከተሞችም እርዳታ ሲሰጥ በ1 ወር በተቃረበ ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው ነው ብለዋል፡፡

በሚቀጥሉት ሳምንታት የWFP እና አጋሮቹ ወደ 450 ሺ ለሚደርሱ ሰዎች የምግብ እርዳታ የሚያቀርቡ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

በአካባቢው ላይ ባለ አለመረጋጋት የተነሳ በኢትዮጵያ ሰአብአዊ ምላሽ ለመስጠት አሁንም ችግር እንደሆነ መቀለጡን ዋና ጸሀፊው አመልክተዋል፡፡

WFP በ1,700 ተሽካርካሪዎችን ሊጫን የሚችል ከ67 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆን እህል በሰሜን ኢትዮጵያ ያከማቸ መሆኑን ስቴፋን ዱጃሪች አስታውቀዋል፡፡

ይህ ወደ 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብን ለሁለት ወራት መመገብ የሚችል መሆኑን ገልጸው፣ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የገንዘብና የነዳጅ እጥረት መኖሩን ማሳወቃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

#WFP #UN

@tikvahethiopia
#WFP

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከመደበኛ እርዳታ ውጪ ለ62,900 አባዋራዎች የምግብ እርዳታ አቀርባለሁ ብሏል።

ከቀናት በፊት የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

ውይይቱ በሶማሊ ክልል ውስጥ በአንድ አንድ ቦታዎች የተከሰተዉን ድርቅ ለመቋቋም ያለመ ነው።

በዉይይቱ ላይ አቶ ሙስጠፋ ፥ በተለይ ዳዋ ዞን ከፍተኛ የድርቅ አደጋ የተከሰተባቸዉ ቦታዎች አንዱ መሆኑን በመግለፅ በአሁኑ ወቅት የዓለም ምግብ ፕሮግራሙ ከሚሰጠው መደበኛ እርዳታ ዉጪ አስቸኳይ እርዳታ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸዉ የሚመሰገን ስራ ነዉ ብለዋል።

በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር ስቲቨን ዌር ኦማሞ ከክልሉ መንግሥት ጋር በድርቁ ሁኔታ ዙሪያ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው የሶማሊ ክልል መንግስት ድርቁን ለመቋቋም ላደረገው ቁርጠኝነትና 200 ሚሊዮን ብር በመመደብ የሰራዉን ስራ ምስጋና በማቅረብ ድርሻቸዉን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ኃላፊው በዳዋ ዞን ውስጥ ለሚገኙ የድርቁ ተጎጂዎች ለሆኑ 62,900 አባዋራዎች በአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያደርሱ ተናግረዋል።

#SomaliRegionCommunication

@tikvahethiopia
#WFP

በትላንትናው ዕለት የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በትላንትናው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በደሴ እና በኮምቦልቻ ከተሞች የነበሩት መጋዘኖቹ በህወሓት ኃይሎች በመዘረፋቸው የምግብ እርዳታ ማቋረጡን አስታውቋል።

ቃል አቀባዩ ፥ የእርዳታ ምግብ ተከማችተውባቸው የነበሩት መጋዘኖቹ በህወሓት ኃይል በተዘረፉበት ወቅት በስፍራው በነበሩ ሠራተኞቹ መሳሪያ ተደግኖባቸው እንደነበረ አመልክተዋል።

በመጋዘኖቹ ላይ በህወሓት በተፈጸመው ዝርፊያ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህጻናት የሚቀርቡ አልሚ ምግቦችን ጨምሮ ከፍተኛ መጠን ያለው የምግብ አቅርቦት ክምችት ከሁለቱ ከተሞች ተወስደውበታል።

በስፍራዎቹ የነበሩ ሠራተኞቹም በጦር መሳሪያ ጭምር ጫናና ማስፈራሪያ ስለተደረሰባቸው ይህንን ዝርፊያ ለመከላከል ሳይችሉ መቅረታቸው ተገልጿል።

ይህ ዝርፊያ በአሁኑ ወቅት ከ9 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በምግብ እርዳታ ላይ ጥገኛ በሆነበት በሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የምግብ ዋስትና ችግርና የተመጣጠነ ምግብ እጦትን የበለጠ እንደሚያባብሰው ድርጅቱ ተናግሯል።

በሌላ በኩል በአማራ ክልል ለሰብአዊ አገልግሎት የሚውሉ ሶስት የWFP መኪኖች በዚህ ሳምንት በወታደሮች ታዝዘው ለራሳቸው ዓላማ መዋላቸውን ዱጃሪች ተናግረው ድርጊቱን አውግዘዋል ሁሉም አካላት የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎችን እንዲያከብሩና እንዲጠብቁ ጠይቀዋል።

ለአንድ ወር ያህል በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር የቆዩት የደሴና የኮምቦልቻ ከተሞች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተመራው የኢትዮጵያ ጥምር የፀጥታ ኃይሎች በዚህ ሳምንት ነፃ መውጣታቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ያቋረጠውን ድጋፍ ከቀናት በኃላ እንደሚጀመር አሳውቋል።

ድርጅቱ በአማራ ክልል የነፍስ አድን ምግብ እርዳታ ማድረግ መቀጠሉን ገልጿል።

በሰ/ጎንደር 470,000 ሰዎች በደሴ/ኮምቦልቻ 172,000 ሰዎች በJEOP በኩል መድረሱን አሳውቋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ በዘረፋ እና በደህንነት ማጣት ምክንያት ባለፈው ሳምንት አቋርጦት የነበረውን ድጋፍ በሚቀጥሉት ቀናት ለመቀጠል ተስፋ እንደሚያድረግ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 21 የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በአፋር ክልል " አብኣላ " መንገድ ወደ ትግራይ ክልል መጓዝ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ከሰዓት አስታውቋል። ተሽከርካሪዎቹ የእህል እርዳታ የጫኑ ሲሆን በዓለም ምግብ ድርጅት (WFP) አማካኝነት ነው በአፋር አብዓላ በኩል በየብስ ወደ ትግራይ እየሄዱ የሚገኙት። መንግስት የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ…
#Tigray #Afar #WFP

ወደ ትግራይ ጉዞ እንደጀመሩ የተገለፀላቸው የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት መጀመራቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) አስታውቋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ ኢሬብቲ ደርሰው ወደ ትግራይ ማቋረጥ መጀመራቸውን የገለጸው ድርጅቱ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ መቐለ ይገባሉ ብሏል፡፡

ከ500 ሜትሪክ ቶን በላይ የተመጣጠነ ምግብ በርሃብ አፋፍ ላይ ለሚገኙ የእርዳታው ፈላጊዎች ይከፋፈላል ተብሏል።

በተጨማሪ ፤ ከ1000 ሜትሪክ ቶን በላይ የተመጣጠነ ምግብ የጫኑ ሌሎች የእርዳታ ተሽከርካሪዎች ዛሬ ከሰዓት ሰሜናዊ አፋር መድረሳቸውንም የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል፡፡

የሰብዓዊ እርዳታው ፦
👉 ዳሎል፣
👉 በራህሌ
👉 ኮነባ አካባቢዎች ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚደርስ ገልጿል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሽከርካሪዎቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲያልፉ የአፋር ክልላዊ መንግስት እና ህዝብ ትልቅ ድጋፍ እንዳደረገ ገልጿል።

መረጃው የዓለም ምግብ ፕሮግራም የትዊተር ገፅ ነው።

ፎቶ ፦ ወደ ትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ ጭነው እየተጓዙ የነበሩት ተሽከርካሪዎች (ከአፋር ክልል ቲክቫህ አባላት)

@tikvahethiopia