TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
PHOTO : ለትምህርት ብለው ልጆቻቸውን ትግራይ ውስጥ ወደሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የላኩ ወላጆች እና ቤተሰቦች በተመድ (UN) ቢሮ ፊት ለፊት ልጆቻቸው እንዲመለሱላቸው ጥያቄ እያቀረቡ ነው።

ከላይ የተያያዙት ፎቶዎች በፎቶግራፍ ባለሞያውና የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ (AFP) ባልደረባ በሆነው አማኑኤል ስለሺ የተነሱ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Save_the_Children Save the Children የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የተኩስ አቁም ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ ለክልሉ የሚደረገውን ድጋፍ በጸጥታ ስጋት ምክንያት በጊዜያዊነት እንዳቆመ አስታወቀ። ይህን ያሳወቁት በኢትዮጲያ የ Save the Childern ቃል አቀባይ የሆኑት ወ/ሮ ህይወት እምሻዉ ለአሀዱ 94.3 ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ነው። ወ/ሮ ህይወት ከተናጠል ተኩስ አቁሙ አስቀድሞ…
#Save_the_Children

"ከቀድሞ ጋር ሲነፃፀር በመጠን ቢያንስም አሁንም ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረግን ነው" - ወ/ሮ ህይወት እምሻው

የሕፃናት አድን ድርጅት አሁንም በትግራይ ክልል ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

በኢትዮጵያ የ Save the Children ቃል አቀባይ ወይዘሮ ህይወት እምሻው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት " አሁናዊ መረጃ እና ማረሚያ " ድርጅቱ በትግራይ ከቀድሞው ጋር ሲነፃፀር በመጠን ቢያንስም፣ አሁንም ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ድጋፎቹ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በውሃ አቅርቦት እንዲሁም የምግብ እርዳታ ላይ ያተኮሩ እንደሆኑም ገልፀዋል።

Save the Childern በመቐለ፣ በአክሱም እና በዓዲግራት ውስን ሰራተኞችን በመጠቀም ስራውን እያከናወነ ይገኛል።

@tikvahethiopia
ዐቃቤ ሕግ በእነ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል መዝገብ በ62 ሰዎች ላይ ክስ መሰረተ፡፡

ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ፦

- የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ውሳኔ በመስጠት ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው የህውሀት መዓከላዊ ኮሚቴ አባላት

- የክልል መንግስቱ ካቢኔ አባላት

- በትጥቅ ጥቃት ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው የኢፈርት ድርጅቶች፣

- የግልና የመንግስት ድርጅት አመራሮች፣

- የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን አመራር አባላት፣

- በትግራይ በተካሄደው ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ምርጫ ላይ ተሳትፎ ያደረጉት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሊቃነ-መናብርት

- የቀድሞ የህውሀት ከፍተኛ አመራር የነበሩ ታዋቂ ግለሰቦች ናቸድ።

ክሱ የተመሰረተው በሁለት የወንጀል አንቀጽ ስር ነው። እነዚህም ፦

• በሀይል በዛቻ በአድማና ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ኢ-ሕገመንግስታዊ ምርጫ በማካሄድ በሕገ-መንግስት የተቋቋመና እውቅና ያለው የክልል መንግስት መለወጥ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 238 ስር የተደነገገውን በመተላለፍ

• የፌዴራሉን መንግስት በሀይል ለመለወጥ በማሰብ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የፌዴራል መንግስትን በመሳሪያ ጥቃት መለወጥ የሚችል የትግራይ ወታደራዊ ኮማንድ የተባለ የጦር ሀይል በማደራጀት የፌዴራል መንግስት የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት በማድረስ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ አዋጅ ቁጥር 1176/2011 አንቀጽ 3/1እና 3/2 በመተላለፍ ወንጀል ነው።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለክሱ አስረጅነት 510 የሰው ምስክሮችን እና እና 5,329 ገጽ የሰነድ ማስረጃዎችን በማያያዝ ለፍርድ ቤቱ ቅርቧል፡፡

ያንብቡ : telegra.ph/Attorney-General-07-23

@tikvahethiopia
#Tokyo2020

የቶኪዮ ኦሎምፒክ መክፈቻ ስነስርዓት መካሄድ ጀመረ።

መላው ዓለም በጉጉት የሚጠበቅው የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ውድድር የመክፈቻ ስነ ስርዓት መካሄድ ጀምሯል።

በጃፓን ባለው የኮቪድ ወረርሽኝ መባባስ የተነሳ የ መክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ታዳሚ እንዲገባ አልተደረገም።

በባዶ ስታዲየም ውስጥ ነው የመክፈቻ ትርኢት እየተየ የሚገኘው።

የኦሎምፒክ ማህበረሰቡ በአስከፊው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተጎዱትን ሁሉ አስቧል።

በነገራችን ላይ ፦ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በ130 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ውድድሩ እንዲራዘም ምክንያት ሆኗል ፤ ይህ ውድድር ባለፈው ዓመት መካሄድ እንደነበረበት ይታወቃል።

Photo Credit : Reuters

@tikvahethiopia
PHOTO : በኮቪድ -19 ምክንያት ለአንድ ዓመት ተራዝሞ የነበረው የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ዛሬ አነስ ባለ ነገር ግን በደማቅ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ተጀምሯል።

በየ4 ዓመቱ የሚካሄደው ኦሎምፒክ በዓለም አቀፍ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት እንዲዘገይ ሆኗል።

በዛሬው በቶኪዮ ኦሊምፒክ ስቴዲየም የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ለኮቪድ-19 ጥንቃቄ ሲባል ወደ 900 የሚሆኑ ተጋባዥ እንግዶች እና ባለሥልጣናት ብቻ በታደሙበት ነው መክፈቻው የተካሄደው።

#ቪኦኤ

Photo Credit : AP

@tikvahethiopoa
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 5,543 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 128 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሁለት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 58 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
ሩሲያ ከ2ኛው ዙር የግድቡ ሙሌት በኃላ ምን አለች ?

ሩሲያ ትላንት ሀሙስ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣችው መግለጫ በግድቡ ዙሪያ ያለው አለመግባባት በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ውስጥ በሚደረግ ድርድር እንዲፈታ አሳስባለች።

ሩሲያ ከህዳሴ ግድቡን ጋር በተያያዘ ያለውን ሁኔታ እየተከታተለች እንደምትገኝ ገልፃ ጉዳዩ ለግብፅ ፣ ለሱዳን ፣ እና ለኢትዮጵያ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እገነዘባለሁ ብላለች ሲል 'Egypt Independent' አስነብቧል።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለው አለመግባባት የትም ቦታ ሳይሄድ እዚሁ በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ መፈታት እንዳለበት ደጋግማ እየገለፀች መሆኑ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#Tokyo2020 #Taekwondo

ሰለሞን ቱፋ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፏል ?

እጅግ ተጠባቂው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር ትላንት ተጀምሯል።

ኢትዮጵያ ሀገራችን በውድድሩ ከምትካፈልበት የውድድር ዘርፎች አንዱ የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ነው።

ኢትዮጵያ በውድድሩ በሰለሞን ቱፋ የተወከለች ሲሆን ከሰዓታት በፊት በተደረገው ውድድር የሀገራችን ልጅ ሰለሞን ቱፋ የጃፓኑን ተጋጣሚው ሰርጅዮ ሱዙኪ በመርታት ወደ ሩብ ፍፃሜው ማለፍ ችሎ ነበር።

ነገር ግን በቱኒዚያው ተፎካካሪው ተሸንፏል። ቱኒዚያዊው ሞሀመድ ካሊል 32 ለ 9 በሆነ የነጥብ ልዩነት ሰለሞን ቱፋን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜው አልፏል ።

ሰለሞን ቱፋ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦሎምፒክ #ኢትዮጵያ በተሳተፈችበት የ58ኪሎ የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ላይ ወደ ሩብ ፍፃሜው ቢያልፍም ፥ በቱኒዝያዊው መሐመድ ካሊል በነጥብ ተሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፍ አልቻለም።

ስፖርታዊ ጉዳዮች : @tikvahethsport
ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

የደ/ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ13ኛው ዙር የ2013 ዓ/ም ተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት እያከናወነ ነው።

ዛሬ የመጀመሪያው ዙር ምርቃት (በዋናው ግቢ) ሲሆን ነገ ደግሞ በቡሬ ካምፓስ ተማሪዎች ይመረቃሉ።

በአጠቃላይ ምን ያህል ተማሪዎች ይመረቃሉ ?

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን በመደበኛው፣ በማታና በክረምት
• ሴት 1193
• ወንድ 2122 በድምሩ ከ3,315 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ

በሁለተኛ ዲግሪ ፦
• 143 ሴቶችና
• 254 ወንዶች በድምሩ 397 ተማሪዎችን በአጠቃላይ 3712 ምሩቃንን በዋናው ግቢ ሃዲስ አለማየሁ የጉባዔ አዳራሽ እና ሃምሌ 18/2013 ዓ/ም በቡሬ ካምፓስ ይመረቃሉ።

ከዩኒቨርሲቲው በተገኘው መረጃ በዋናው ግቢ 2,905 ተማሪዎች ናቸው የሚመረቁት።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን : @tikvahuniversity
ቻይና በአሜሪካ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ነው።

ቻይና በርከት ባሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት እና ተቋማት ላይ ማዕቀብ እየጣለች ትገኛለች። ሀገሪቱ ማዕቀብ እየጣለች የምትገኘው አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ለመጣሏ የመልስ ምት ነው።

አሜሪካ በሆንግ ኮንግ ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ ጥላ የነበረው በዜጎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በሚወስዱት እርምጃ እጃቸው አለበት በሚል ነበር።

አሁን ቻይና ማዕቀብ ከጣለችባቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት መካከል የቀድሞው የንግድ ዘርፍ ጸሐፊ ዊልበር ሮስ በዋ ዋንኝነት ይጠቀሳሉ።

ከዊልበር ሮስ በተጨማሪ የመብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዋች የቻይና ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ሶፊ ሪቻርድሰን ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል።

የቻይና እና አሜሪካ የምጣኔ ሀብትና ደኅንነት ኮሚሽን ኃላፊ ካሮሊን ባርቶሎሜው፣ የዓለም አቀፉ የሪፐብሊካን ተቋም አመራር አዳም ኪንግ ላይም ማዕቀብ ተጥሏል።

የአሁኑ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዌንዲ ሸርማን በጥቂት ቀናት ውስጥ ቻይናን ይጎበኛሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው ፥ በዚህ ወቅት ነው እንግዲ ቻይና በአሜሪካ ባለስጣናት ላይ ማዕቀብ መጣል የጀመረችው።

የዋይት ሐውስ ቃል አቀባይ የሆኑት ጄን ሳኪ አሜሪካ በቻይና ማዕቀብ "አትበገርም" ብለዋል።

NB : ቻይና ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስተር ማይክ ፖምፕዮን ጨምሮ 27 የትራምፕ ዘመን አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።

መረጃው ከቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia