TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የቤንች ሸኮ ዞን ም/ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ዛሬ ያካሂዳል። ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 8ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነው የሚያካሂደው። በወጣው መርሃ ግብር መሰረትም የዞኑ ወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ላይ እና የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በተመለከተ ምክር ቤቱ መክሮበት አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። መረጃው የዞን ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው። @tikvahethiopia
የቤንች ሸኮ ዞን ም/ቤት አስቸኳይ ጉባኤ እንዴት ተጠናቀቀ ?

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶፍቅሬ አማን የዞኑን ወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ላይ እንዲሁም የህብረተሠቡ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የተደረገበት የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በተመለከተ ለምክር ቤቱ አጠቃላይ ሁኔታን የሚያሳይ ሪፖርት አቅርበው ነበር።

የም/ቤቱ አባላት ውይይት ካደረጉ በኃላ ባለ9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባኤው ተጠናቋል።

ም/ቤቱ በአቋም መግለጫው፦

- የተፈጠረው የፀጥታ ችግር መዋቅርን መነሻ ያደረገ ነው ዛሬ ላይ ግን መልኩን ቀይሮ የትኛውንም ብሄረሰብ ሊወክሉ በማይችሉ የ 'ፀረ-ሰላም ሀይሎች' እየተፈጸመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት የንጹሀን ዜጎች ሞት ፣ አካል ጉዳት ፣ ንብረት መውደምና መፈናቀል አጥብቀን እናወግዛለን ብሏል።

- የፀጥታ ሀይሉ ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት መስዋዕትነት በታላቅ አክብሮትና ጀግንነት እያደነቅን ከህብረተሰቡ ውስጥ ሆኖ ለ 'ፀረ-ሰላም ሀይሉና ሽፍታዎች መረጃ ፣ ስንቅ ፣ትጥቅና አቅጣጫ በመስጠት የጸጥታ ሀይሉን ተልዕኮ የሚያደናቅፉ አካላትን አጥብቀን እንቃወማለን ብሏል።

- የህዝብ ም/ቤት አባላት የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት መሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ከፍሎች የጸጥታ መዋቅሩ ለሚያደርጋቸው ህጋዊ እንቅስቃሴዎች እውቅና ከመስጠት በተጨማሪ አስፈላጊው ድጋፍ እናድረጋለን ብለዋል።

- የም/ቤት አባላቱ እና የጉባኤ ተሳታፊዎች በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችንና ቀጥተኛ ተጎጂ ቤተሰቦችን መልሶ ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረት ከአስፈጻሚው ጎን በመሆን በስነ-ልቦና የቁሳቁስና አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ መልሶ እንዲቋቋሙና የተረጋጋ ህይወት እንዲመሩ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

ያንብቡ: telegra.ph/መግለጫ-05-25-2
የሚዛን አማን ኤርፖርት ጉዳይ :

የቤንች ሸኮ ዞን ም/ቤት በአስቸኳይ ጉባኤው ባወጣው ባለ9 ነጥብ የአቋም መግለጫ ስለሚዛን አማን ኤርፖርት ይህን ብሏል ፦

"የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ከ2009 ዓ.ም በጀት ዓመት ጀምሮ ይገነባል ተብሎ ህብረተሰቡን በማስተባበር ከ21.9 ሚሊዬን ብር ተሰባስቦ ካሳ በመክፈልና ቦታውን ከይገባኛል ነጻ በማድረግ ሰዎችን መልሶ የማስፈር ስራ መሰራቱ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ መሰረት የኤርፖርቶች ድርጅት ጥናት በማስጠናት እና ዲዛይን በመስራት እውቅና አግኝቶ በፓርላማ በጀት ተመድቦ ወደ ጫረታ መገባቱ የሚታወስና በተለያዩ ሚዲያዎች የተገለጸ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ ግንባታው በመዘግየቱ ምክንያት ቅሬታ ውስጥ ባለንበት ወቅት ህብረተሰባችንንና ያለንን ዕምቅ አቅም በማይመጥን መንገድ ተለዋጭ ቦታ እንዲዘጋጅ መጠየቁ ተገቢነት የሌለውና ህዝባችንን አሳንሶ ማየት ስለሆነ ይህንን ስህተት የሰራው አካል ህዝባችንን ይቅርታ እንዲጠይቅ እና ግንባታው በፍጥነት እንዲጀመር አበክረን እንጠይቃለን።"

@tikvahethiopia
የማሊ ጦር የሀገሪቱን ፕሬዝደንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር በቁጥጥር ስር አዋለ !

የማሊ የሽግግር ፕሬዝዳንት እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ትናንት ሰኞ ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ፕሬዜዳንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሀገሪቱ ጦር / ወታደራዊ መኮንኖች ነው።

የሀገሪቱ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ባህ ንዳው እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሞክታር ኦዋን ከበርካታ ሰራተኞች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነሐሴ 2020 ከተፈጸመው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በኋላ ማሊ ወደ ሲቪል አስተዳደር መመለሷን የሚከታተለው የሀገሪቱ የሽግግር ተቆጣጣሪ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ይህ ኮሚቴ የአፍሪካ ህብረት ፣ በማሊ የተመድ ተልዕኮን እና የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ማህበረሰብን የሚያካትት ነው፡፡

ኮሚቴው ፈረንሳይ፣ አሜሪካ ፣ እንግሊዝ ፣ ጀርመንና የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሽግግሩ ፕሬዝደንት ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በስራቸው የሚገኙ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡

ኮሚቴው እንዳለው ከሆነ በእስር ላይ ሚገኙት ባለሥልጣናት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በፍጥነት እንዲለቀቁ እና እነርሱን በቁጥጥር ስር ያዋሉ ወታደራዊ አባላት ተጠያቂ እንዲሆኑም ተጠይቋል፡፡

ፕሬዝደንቱ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የታሰሩት ፕሬዝደንት ንዋድ ከፍተኛ የሚኒስትርነት ቦታዎች ላይ በተከታታይ እጩዎችን ይፋ ካደረጉ ብዙም ሳይቆይ ነው፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia
"...የአገር ነፃነት በገንዘብ አይለወጥም" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው አሜሪካ ስላሳለፈችው እገዳ አንስተዋል።

የአሜሪካ እገዳ የ2ቱን አገራት ግንኙነት ቢጎዳም ቀዩ መስመር ግን የኢትዮጵያ ነፃነት በገንዘብ ሊቀየር የሚችል አለመሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ፥ የአገር ነፃነት በገንዘብ አይለወጥም ብለዋል።

አምባሳደር ዲና ፥ "ወቅታዊዉ የአሜሪካ ውሳኔ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ቢያደርስም ፣ ነገር ግን ለገንዘብ ተብሎ ኢትዮጵያ ነፃነቷን አሳልፋ አትሰጥም ፤ ይሄ ቀይ መስመር ነው" ብለዋል።

መንግስት ከአለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለሚያገኘው ገንዘብ ብሎ ልደራደር ቢል እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን በገንዘብ የሚቀይር አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል።

የአሜሪካ እገዳ የ2ቱን አገራት ግንኙነት የሚጎዳ ብቻ ሳይሆን፣ ቀጠናውና ሌሎች አገራት ላይም ተፅዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ አሜሪካ ውሳኔዋን ደግማ ልታስብበት ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የአሜሪካ ውሳኔ በኢትዮጵያ ላይ የኢኮኖሚ ተፅዕኖ ቢኖረውም የኢትዮጵያ ሉአላዊነት ግን ለሚደራደር የሚቀርብ አይሆንም ሲሉ አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
የጆ ባይደን እና የአል ሲ ሲ የስልክ ውይይት :

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ትናንት ሰኞ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ዙሪያ መወያየታቸውን ከሁለቱም ወገን የወጣ መግለጫ አመልክቷል።

ሁለቱ መሪዎቹ በውይይታቸው ግብጽ ከ #ኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ውስጥ ስለገባችበት ስለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አንስተው መወያየታቸውን ከፕሬዝዳንት ባይደን ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አልሲሲ ከሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት ጋዛ ውስጥ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለማስቆም በግብጽ አሸማጋይነት ስለተደረሰው ተኩስ አቁምም ተወያይተዋል ተብሏል።

ከዋይት ሐውስ የወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በስልክ በተደረገው ውይይት ላይ "ፕሬዝዳንት ባይደን የአባይን ውሃ በተመለከተ ግብጽ ያላትን ስጋት እንደሚረዱ ገልጸዋል" ብሏል።

በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ባይደን በጉዳዩ ዙሪያ "የግብጽን፣ የሱዳንን እና የኢትዮጵያን ሕጋዊ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እንዲገኝ የአሜሪካ ፍላጎት መሆኑን ገልልፀዋል ተብሏል።

በሁለቱ መሪዎች መካከል ስለተደረገው ውይይት የግብጽ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ፥ ባይደን እና አልሲሲ "የሁሉንም ወገኖች የውሃ እና የልማት መብቶችን የሚያስከብር ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚያስችል የተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለማድረግ ተስማምተዋል" ብሏል።

#BBC #Reuters

@tikvahethiopia
#AddisAbabaPoliceCommission

የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገ- ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ228 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና ከ85 ሺህ በላይ ብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ገለፀ።

ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት አደረኩት ባለው ክትትል ነው ገንዘቡን በቁጥጥር ስር ያዋለው።

ገንዘቡን በቁጥጥር ስር የዋለው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በተለምዶ ላምበረት ተብሎ በሚጠራው "መናኸሪያ ግቢ" ውስጥ ነው።

ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ 2 ግለሰቦች ከአዲስ አበባ ለመውጣት ሲዘጋጁ ግንቦት 10/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 3 ሠዓት ገደማ በያዙት ሻንጣ ላይ በተደረገ ብርበራ በላስቲክ ተጠቅልሎ የተቀመጠ 205 ሺህ 512 የአሜሪካ ዶላር ተይዟል።

በተጨማሪ የተለያዩ የባንክ ሰነዶችና ፓስፖርት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በሌላ መረጃ ፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥናት ላይ ተመስርቼ አከናወንኩት ባለው ተግባር ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ኦሎምፒያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ግንቦት 11/2013 ዓ/ም በግምት 9 ሰዓት ገደማ ለህገ ወጥ ዝውውር የተዘጋጀ 23 ሺ 300 የአሜሪካ ዶላር ፣ 85 ሺ 600 የኢትዮጵያ ብር እንዲሁም 17 የተለያዩ የኤ.ቲ.ኤም ካርዶች እና 29 የተለያዩ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር እንደያዘ ሪፖርት አድሯል።

በአጠቃላይ በተያዙት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራ ነው።

@tikvahethiopia
#Moderna

ሞደርና የኮቪድ-19 ክትባቱ እድሜያቸው ከ12 እስከ 17 ባሉ ታዳጊዎች ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በጣም ውጤታማ ነው ሲል በዛሬው ዕለት ሪፖርት አድርጓል።

ሞደርና ከ3,700 በላይ በሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ12 - 17 ባሉ ታዳጊዎች ላይ ጥናት ማድረጉን ገልጿል።

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የደረሰበትን የጥናት ውጤት ለአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር እና ለሌሎች የዓለም ተቆጣጣሪዎች በሚቀጥለው ወር መጀመሪያ ላይ አቀርባለሁ ብሏል።

@tikvahethiopia
የአሜሪካ መንግስት በትግራይ ክልል ድጋፍ አደረገ።

የአሜሪካ ተርአዶ ድርጅት (USAID) 33 የቢሮ መኪኖችን እና 10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ ድጋፍ ማድረጉን ኢብኮ ዘግቧል።

የUASID ተወካዮች በጤና ቢሮ በመገኘት ከቢሮ ኃላፊዎቹ ጋር የቁልፍ እና የቁሳቁስ ርክክብ አድርገዋል።

መኪናዎቹ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በጤና ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ እና በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

ድጋፉ በክልሉ ያጋጠመውን የመኪና እጥረት በማቃለል ረገድ አስተዋፆ አለው ተብሏል።

USAID በትግራይ በጤናው ዘርፍ ያጋጠመውን ጉዳት ለመለስ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

የትግራይ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ፋሲካ አምደስላሴ ፥" በትግራይ ብዙ መኪናዎች ጠፍተዋል፣ ተጎድተዋል። እንደ ምሳሌ ከ270 አምቡላንስ 50 አምቡላንስ ብቻ ነው እየሰራ ያለው። ከወረዳ ወረዳ ፣ ከወረዳ ሆስፒታል ከሆስፒታል ሆስፒታል የእናቶች ፣ የልጆች ሪፈራል አገልግሎት ተስተጓጉሏል፤ ከደረሰው ጥፋትና ጉዳት አንፃር ድጋፉ ትንሽ ነው፤ በጣም ብዙ ነው የሚያስፈልገው ፤ ነገር ግን ይሄም ትልቅ ውጤት ይኖረዋል ፤ በክልሉ ከነበረው የጤና ስርዓት አንፃር ስንመለከተው የጎደለው ብዙ ነው" ብለዋል።

ዶ/ር ፋሲካ በUSAID ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በክልሉ የአምቡላንሶች አለመኖር በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑን ገልፀዋል።

አቅም ያላቸው አጋር ድርጅቶች ፣ ያገባኛል የሚሉ አካላት ፣ ግለሰቦች ፣ ባለሃብቶች የክልሉን የጤና ስርዓት ለማስተካከል ከመድሃኒት ጀምሮ ሌሎች ትልልቅ እገዛዎችን በአቅማቸው እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
ቻይና ለትግራይ ክልል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

ቻይና ለትግራይ የኮሮና ቫይረስ መከላከል እና ለሌሎች የህክምና አገልግሎት የሚውል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

ድጋፉን የቻይና ኤምባሲ የኢኮኖሚና የንግድ ካውንስለር ሊ ዩ ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ አስረክበዋል።

ድጋፉ ፦

- ሰባት (7) የመተንፈሻ እገዛ የሚሰጡ መሳሪያዎች (ቬንትሌተሮች)፣
- 36 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ)
- 1 ሺህ 500 የህክምና አልባሳትን
- የህክምና እርዳታ ለመስጠት የሚያስችሉ የህክምና መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ያካተተ ነው።

ድጋፉ ከቻይና መንግሥትና ከቻይና ኩባንያዎች የተሰባሰበ ነው። #ENA

@tikvahethiopia
#Shire

የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ወታደሮች ሰኞ ምሽት በትግራይ ሽረ ከተማ ተፈናቃዮች ከሚገኙበት አራት ካምፖች ከ500 በላይ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በግዳጅ ይዘው መወሰዳቸውን 3 የእርዳታ ሰራተኞች እና አንድ ዶ/ር እንደነገሩት ሮይተርስ አስነብቧል።

የእርዳታ ሰራተኞቹና ዶክተሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኪናዎች ላይ ተጭነው ተወስደዋል ሲሉ ፤ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ተናግረዋል።

ከእርዳታ ሠራተኞች መካከል አንዱ ፥ በርካታ ወንዶች ተደብድበዋል ፣ ስልካቸው እና ገንዘባቸው ተወስዷል ብለዋል።

በአንዱ ካምፕ ውስጥ የሚኖር ክስተቱ በተፈፀመበት ወቅት የተደበቀ አንድ ግለሠብ ወታደሮች ሰብረው ገብተው ሰዎችን በዱላ መደብደባቸው ተናግሯል።

ይኸው ስሙ በሚስጥር እንዲያዝ የጠየቀው ግለሰብ ፥ ወታደሮች በምሽት መጥተው ካምፑን በመክበብ ዋናውን በር በመስበር ያገኙትን ሁሉ በዱላ መደብደብ እንደጀመሩ ገልጾ በወቅቱ የ70 ዓመት አዛውንት መደብደባቸውን እና አንድ አይነስውር አፍነው መውሰዳቸውን ተናግሯል።

እሱ ካለበት ፀሃዬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ 400 ሰዎች መወሰዳቸውን አስረድቷል።

የመከላከያ ቃል አቀባይ፣ የትግራይ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡበት መልዕክት ቢቀመጥላቸውም ምላሽ አልሰጡም ብሏል ሮይተርስ።

የሰሜን ምዕራብ ዞን ጊዜያዊ ኃላፊ ቴዎድሮስ አረጋይ ፥ ጥቂት መረጃ እንዳላቸው ነገር ግን በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ክሱን የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፕሮፖጋንዳ ነው ሲሉ አጣጥለውታል።

ያንብቡ : telegra.ph/Shire-05-25

@tikvahethiopia
4G LTE በምስራቅ ኢትዮጵያ !

ኢትዮ ቴሌኮም ምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች የሞባይል ኢንተርኔት በተሻለ ፍጥነት ማስጠቀም የሚችለውን 4G LTE Advanced የኢንተርኔት አገልግሎት አስጀመረ።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ፦ ድሬዳዋ ፣ አይሻ እና ጭሮ ከተሞች እንደሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ÷ በምስራቅ አካባቢ ለሚገኙ ከ330 ሺህ በላይ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት ይፋ ማድረጉን ገልጸዋል።

ይህም የላቀ የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት መጠቀም የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በሶስት (3) ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ መሠረት እስካሁን በ103 ከተሞች የ4G ኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቧል ብለዋል ወ/ሪት ፍሬህይወት።

የሞባይል አገልግሎት አካታች በመሆኑና ከድህነት ለመውጣትና ለተሻለ ኑሮ አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ድርጅቱ ከታሪፍ አንፃር ከሦስተኛው ትውልድ የአገልግሎት ታሪፍ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ሪጅን ከ1.3 ሚሊየን በላይ ደንበኞች አሉት።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA🇪🇹

የግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ መግለጫ👆

"ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ" የተሰኘው የኩባንያዎች ጥምረት ኢትዮጵያ ውስጥ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት እድሉን በማግኘቱ ደስ እንደተሰኝ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ጥምረቱ፥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት በሌሎች አገራት ያስመዘገበው ለውጥ በማምጣት ለባለአክሲዮኖች ቀጣይነት ያለው የኢንቨስትመንት ትርፍ እንደሚያስገኝ እምነት እንዳለው ገልጿል።

የሳፋሪኮም ፣ የቮዳኮም ግሩፕ ፣ የቮዳፎን ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የሱሚቶሞ ም/ፕሬዜዳንትና CDC አፍሪካ ኃላፊ ያስተላለፉት መልዕክት በመግለጫው ላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia