የጆ ባይደን እና የአል ሲ ሲ የስልክ ውይይት :

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ትናንት ሰኞ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ዙሪያ መወያየታቸውን ከሁለቱም ወገን የወጣ መግለጫ አመልክቷል።

ሁለቱ መሪዎቹ በውይይታቸው ግብጽ ከ #ኢትዮጵያ ጋር አለመግባባት ውስጥ ስለገባችበት ስለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አንስተው መወያየታቸውን ከፕሬዝዳንት ባይደን ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና አልሲሲ ከሕዳሴው ግድብ ጉዳይ በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት ጋዛ ውስጥ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለማስቆም በግብጽ አሸማጋይነት ስለተደረሰው ተኩስ አቁምም ተወያይተዋል ተብሏል።

ከዋይት ሐውስ የወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በስልክ በተደረገው ውይይት ላይ "ፕሬዝዳንት ባይደን የአባይን ውሃ በተመለከተ ግብጽ ያላትን ስጋት እንደሚረዱ ገልጸዋል" ብሏል።

በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ባይደን በጉዳዩ ዙሪያ "የግብጽን፣ የሱዳንን እና የኢትዮጵያን ሕጋዊ ፍላጎቶችን የሚያሟላ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ እንዲገኝ የአሜሪካ ፍላጎት መሆኑን ገልልፀዋል ተብሏል።

በሁለቱ መሪዎች መካከል ስለተደረገው ውይይት የግብጽ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ፥ ባይደን እና አልሲሲ "የሁሉንም ወገኖች የውሃ እና የልማት መብቶችን የሚያስከብር ስምምነት ላይ እንዲደረስ የሚያስችል የተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ለማድረግ ተስማምተዋል" ብሏል።

#BBC #Reuters

@tikvahethiopia