TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦ - ትግራይ ነባር እና አዳዲስ ፖሊሶችን እያሰለጠነች ነው። ከፌዴራል ፖሊስ የሄዱ #ተጋሩ የፖሊስ አባላት ተደራጅተው በ6 ዞኖች መደበኛ 15 መሃል ወረዳዎች በመምረጥ ተመድበው የሚሰሩበት ሁኔታም እየተመቻቸ ነው። - ለትግራይ አዳዲስና ነባር ፖሊሶች ወንጀል ለመከላከል የሚሆን አስፈላጊ ትጥቅ መፈቀዱ። - የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል…
#BREAKING

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ #በትግራይ ጉዳይ ያለ ምንም ስምምነት መጠናቀቁን ዲፕሎማቶች መግለፃቸውን AFP ዘግቧል።

ሩስያ ፣ ቻይና እና ህንድ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት አስፈላጊ አይደለም የሚል አቋም ይዘዋል ፤ በዚህም የተ.መ.ድ. የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ያለ ስምምነት ተጠናቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት ጥልቃ ከመግባት ትቆጠብ" - ሩስያ

አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ሩሲያ ጥሪ አቀረበች፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቡድን በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ጥረት ተቃውመዋል፡፡

ቡድኑ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆምም ጠይቀዋል።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቡድኑ የአጋሮችን ፍላጎት ከግምት ሳያስገባ እና ሳያከብር የሚወስነው ውሳኔ ተገቢ አለመሆኑን ነው ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የገለጹት።

twitter.com/mfa_russia/status/1367516464102723590?s=19

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MinistryOfHealth

ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባቷን እሁድ ወደ አገር ውስጥ እንደምታስገባ ጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘገቧል።

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የኮቪድ - 19 ለመከላከል የሚውል የመጀመሪያው ዙር ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ የፊታችን እሁድ በ28/06/213 ዓ.ም ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል።

በክትባቱ ርክክብ ላይ የመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ሚንስቴሩ ገልጿል።

ይሁንና ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የክትባት መጠን አልተገለጸም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2ኛው ዙር የእጩዎች ምዝገባ ጊዜ ተራዘመ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ በመጀመሪያ ዙር እጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልልሎች/የከተማ መስተዳድሮች ፦
- በአዲስ አበባ
- በድሬዳዋ
- በኦሮሚያ
- በሃረሪ
- በጋምቤላ
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ
የእጩዎች ምዝገባ በትላንትናው እለት መጠናቀቁን አሳውቋል።

የእጩዎች ምዝገባን ዘግይተው በጀመሩ ክልልሎች እና ቦታዎች ፦
- በአማራ
- በሶማሌ
- በአፋር
- በምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞን ኦሮሚያ፣
- በደ/ብ/ብ/ህ
- በሲዳማ በመርሃ ግብሩ መሰረት ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ሊጠናቀቅ እንደሚገባው አስታውሷል።

ነገር ግን በቢሮዎች መከፈት መዘግየት የተነሳ ፣ እንዲሁም የትራንስፓርት እና ሌሎች እክሎችን እና የፓርቲዎች አቤቱታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለተኛ ዙር የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን አሳውቋል።

ፓርቲዎች በተሰጡት ተጨማሪ ቀናት ውስጥ ምዝገባቸውን አንዲያጠናቅቁም ቦርዱ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት ጥልቃ ከመግባት ትቆጠብ" - ሩስያ አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ሩሲያ ጥሪ አቀረበች፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቡድን በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ጥረት ተቃውመዋል፡፡ ቡድኑ በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት…
በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ በይፋዊ ትዊተር ገፁ ይህን አስፍሯል ፦

"🇪🇹 🇷🇺 አሜሪካ በሉአላዊ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንድትቆጠብ ሩሲያ ጥሪ አቀረበች፡፡ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ አሜሪካ በሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ጥረት ተቃውመዋል፡፡"

@tikvahethiopiaBOT @tikvhaethiopia
ተማሪ የደበደበው መምህር በ4 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ ዕስራት ተቀጣ።

በመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ በኩቢት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚያስተምረው መምህር አነፀ ፍርዴን የ13 ዓመት ተማሪ ደብድቦ 2 የፊት ጥርስ በማውለቁ በአቃቢ ህግ ከሳሽነት በቀን 25/06/2013 ዓ.ም የመ/ላ/ም/ወ ፍ/ቤት በዋለው ችሎት በ4 ዓመት ከ4 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ታውቋል።

@tikvahethiopia
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ።

እንደ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ ዘገባ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመጭው ምርጫ #በግል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ይወዳደራሉ።

ለዚህም ምዝገባ የሚያስፈልገውን የ2,500 ሰው ድጋፍ በማሰባሰብ በእጩነት መመዝገባቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል፦

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ የዘገበ ሲሆን በዘገባው ላይ ኡስታዝ አቡበክር በግል ይሁን በፓርቲ በምርጫው እንደሚወዳደሩ የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥበቃ ያልተመደበላቸው የምርጫ ክልል ቢሮዎች በአስቸኳይ ጥበቃ እንዲመደብላቸው አሳሰበ !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ 673 የምርጫ ክልሎችን በመክፈት የእጩዎች ምዝገባን እያከናወነ ነው።

የምርጫ ክልሎች ደህንነታቸውን የማስጠበቅ ሃላፊነት የክልል እና የከተማ መስተዳድሮች ነው።

ቦርዱ በተለያየ ጊዜ የምርጫውን ደህንነት ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶች እና ንግግሮቸን እያደረገ የቆየ ሲሆን በዚህም መሰረት አብዛኛው የምርጫ ክልሎች ጥበቃ ሊሟላላቸው እንደቻለ ገልጿል።

ነገር ግን አሁንም ፦

• በኦሮሚያ ክልል- 21 የምርጫ ክልሎች
• በሶማሌ ክልል- 31 የምርጫ ክልሎች
• አማራ ክልል- 40 የምርጫ ክልሎች
• በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል- 6 የምርጫ ክልሎች ጥበቃ እንዳልተመደበላቸው ገልጿል። በመሆኑም አስፈላጊውን የደህንነት ከለላ ከክልል መንግስታቱ እያገኙ አይደለም ብሏል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ክልሎች በአስቸኳይ ለቀሪ የምርጫ ክልል ቢሮዎች የጥበቃ ምደባ እንዲያከናውኑ ያሳሰበ ሲሆን ይህ ሳይሆን ቀርቶ በጥበቃ ችግር ሊፈጠሩ የሚችሉ የምርጫ አፈጻጸም ችግሮች ክልል መስተዳድሮችና የጸጥታ አካላት ሃላፊነቱን ይወስዳሉ ሲል አስገንዝቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ለተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተርነት በአፍሪካ ህብረት በእጩነት ቀረቡ !

ዶክተር አርከበ ዕቁባይ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲወዳደሩ በሙሉ ድምጽ መምረጡን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አስታወቀ።

ህብረቱ ዶክተር አርከበ ብቸኛው አፍሪካዊ እጩ በማድረግ ማቅረቡን ነው ያመለከተው።

የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት 38ተኛ መደበኛ ስብሰባ በየካቲት 24 እና የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ/ም ባደረገበት ወቅት ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ወክለው እንዲወዳደሩ ውሳኔ አሳልፏል።

ዶክተር አርከበ ባለፉት ሰላሳ አመታት ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ልማትና ቀጣይነት ላለው ሁሉን አቀፍ መዋቅራዊ ሽግግር የሚያግዙ ፖሊሲዎችን በማውጣትና በማስተግበር ስኬታማ እንደሆኑ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ ላይ ማስታወቁን ኤፍ ቢ ሲ (FBC) ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDessalegnChanie

የቀድሞ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ /አብን/ ሊቀመንበር የነበሩት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያቸው ባሰራጩት መልዕክት ባህር ዳር ከተማን ፣ የባህር ዳርንና የአማራ ህዝብን ወክለው በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አቅራቢነት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በእጩነት ለመወዳደር መመዝገባቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ። እንደ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ ዘገባ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመጭው ምርጫ #በግል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ይወዳደራሉ። ለዚህም ምዝገባ የሚያስፈልገውን የ2,500 ሰው ድጋፍ በማሰባሰብ በእጩነት መመዝገባቸው ታውቋል። በሌላ በኩል፦ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሀሩን ሚዲያ…
ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ።

የህግ ምሩቅ የሆኑት ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በምርጫ 2013 #በግል ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሃሩን ሚዲያ /Harun Media/ ማረጋገጡን አሳውቋል።

ቀደም ብሎ በወጣው መረጃ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በዘንድሮው ምርጫ 2013 ላይ ለ ፓርላማ እንደሚወዳደሩ መገለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኦነግ በምርጫ 2013 ይሳተፋል ?

ትላንት በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የእጩዎች ምዝገባ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አንድም እጩ አላስመዘገበም።

የኦነግ ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ፥ ኦነግ ምንም የእጩ ምዝገባ አለማድረጉ በምርጫው ላለመሳተፉ ጉልህ ማሳያ ነው ብለዋል።

አቶ በቴ፥ "... በእኛ በኩል በተደጋጋሚ ስንገልፅ እንደነበረው ቢሮዎቻችን ፣ ዋና ፅ/ቤቶቻችን ጨምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኑ ፣ ነፃ እንቅስቃሴ እንደድርጅት መታገዱ ፣ አመራርና አባሎቻችን ያለህግ አግባብ መታሰራቸው ምርጫ ላይ በምናደርገው ተሳትፎ ላይ ትልቅ ተፅእኖ አላቸውና እነዚህ ችግሮች ሳይፈቱ መሳተፍ እንደማንችል ስንገልፅ ነበር ፤ በዚህ ሁኔታ እጩ ማስመዝገብ አልቻልንም ስለዚህ በምርጫ ሂደቱ ተሳታፊ አይደለንም" ብለዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እስከ ቀጣዩ ጠቅላላ ጉባኤ ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ከዚህ ቀደም የተነገረላቸው አቶ ቀጄላ መርዳሳ (የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) በበኩላቸው ፓርቲው ለ7 እና 8 ወር ችግር ላይ ስለነበር እጩ ለማቅረብ አስቸጋሪ እንደበር ገልፀዋል።

አቶ ቀጄላ ፥ ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤ የውስጥ ችግሮቹን ፈቶ በወጥ አመራር በምርጫ 2013 ለመሳተፍ እጬዎችን ለማስመዝገብ በተለየ ሁኔታ ጊዜ እንዲራዘምለት ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑን አሳውቀዋል።

#EthiopiaElection2013 #DW #OLF
https://telegra.ph/Oromo-Liberation-FrontABO-03-05
#ማሳሰቢያ

በጢስ አባይ 2 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በሚካሄደው ጥገና ምክንያት የጢስ አባይ ፏፏቴ ውሃ ከነገ የካቲት 27/2013 ዓ/ም ጀምሮ መጠኑ ጨምሮ ስለሚለቀቅ ከፏፏቴው ግርጌ በሚገኙ አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተብሏል።

#መልዕክቱን_ለሌሎች_ያድረሱ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Alert😷

ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ዛሬ ሪፖርት ተደርጓል።

427 ሰዎች በፅኑ ታመው ህክምና ላይ ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 7,211 የኮቪድ - 19 ላብራቶሪ ምርመራ 1,119 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በዚሁ በ24 ሰዓት ውስጥ 10 ሰዎች ሞተዋል ፤ 228 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MinistryOfHealth ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባቷን እሁድ ወደ አገር ውስጥ እንደምታስገባ ጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘገቧል። የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የኮቪድ - 19 ለመከላከል የሚውል የመጀመሪያው ዙር ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ የፊታችን እሁድ በ28/06/213 ዓ.ም ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል። በክትባቱ ርክክብ ላይ የመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት…
"ኢትዮጵያ እሁድ የምትረከበው 2.2 ሚሊዮን ክትባት ነው"

ኢትዮጵያ የፊታችን እሁድ የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ/ም የካቪድ-19 ክትባት እንደምታስገባ መገለፁ ይታወቃል።

ማምሻውን የጤና ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ እሁድ ኢትዮጵያ የምትረከበው 2.2 ሚሊዮን ክትባት ሲሆን "ኮቫክስ" ከተሰኘው አለምአቀፍ ጥምረት ነው።

የጤና ሚኒስቴር ክትባቱ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።

የክትባት ፕሮግራሙ በቀጣዮቹ ሳምንታት ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ጠራ።

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2013 ተመራቂ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎቹን መጋቢት 5-6 ወደ ግቢ እንዲገቡ ጥሪ አቅርቧል።

በ2013 ተመራቂ ያልሆኑ መደበኛ ተማሪዎቹን ደግሞ ከመጋቢት 15 -16 ወደ ግቢ እንዲገቡ ነው ጥሪውን ያቀረበው።

የ2013 ተመራቂ ተማሪዎች የሆናችሁና በሽረና በዋናው ግቢ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ሪፓርት የምታደርጉት በዋናው ግቢ ሲሆን የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በነበራችሁበት ሪፓርት እንድታደርጉ ተብላችኋል።

መረጃውን የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት የሆነው ጎይቶም ኃይሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በስልክ አድርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ዝርዝር ፦

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከዛራ የካቲት 27 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ/ም የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

በዚሁ መሰረት የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።

- ቤንዚን በሊትር 25 ብር ከ 86 ሳንቲም፥

- ኤታኖል ድብልቅ ቤንዚን በሊትር 25 ብር ከ 36 ሳንቲም፥

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 23 ብር ከ18 ሳንቲም፥

- ኬሮሲን በሊትር 23 ብር ከ18 ሳንቲም፥

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 20 ብር ከ27 ሳንቲም፥

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 19 ብር ከ78 ሳንቲም፥

- የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 38 ብር ከ65 ሳንቲም ይሆናል ብሏል ሚኒስቴሩ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ በተመለከተ በዝርዝሩ የተካተቱ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫን ለማሳወቅ የህዝብ ማስታወቂያ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።

በዚሁ መሰረት #በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ተግባራዊ ይደረጋል ብሏል። #FBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሱዳን እና ግብፅ ነገር ...? የግብፅ ጦር አዛዥ ካርቱም ፤ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካይሮ ናቸው። ካርቱም ላይ ፦ ሰኞ ወደ ካርቱም ያመሩት የግብፅ ጦር አዛዥ ሌ/ጀ ሞሀመድ ፋሪድ ከሱዳን አቻቸው ሌ/ጀ ሞሀመድ አል ሁሴን ጋር የተለያዩ ወታደራዊ ስምምነቶችን ፈፅመዋል። የግብፁ ጦር አዛዥ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ግብፅ እና ሱዳን ተመሳሳይ ብሄራዊ የደህንነት ስጋት ተደቅኖባቸዋል ፤ በጋራ መስራት…
ስለሱዳን እና ግብፅ ወታደራዊ ስምምነት ኢትዮጵያ ምን ትላለች ?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሰሞኑ ሱዳን እና ግብጽ ሰሞኑን ባደረጉት ወታደራዊ ስምምነት ዙሪየ ተጠይቀው ለኢፕድ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሱዳንም ሆነ ግብጽ ልአላዊ አገር ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የፈለጉትን አይነት ስምምነት የማድረግ መብት እንዳላቸው እና ኢትዮጵያም እንደማይመለከታት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፀዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ "... ልአላዊ አገራት የሚያደርጉት ስምምነት እኛ ምንም አይመለከተንም። የሱዳን እና የግብጽ ስምምንት ኢትዮጵያ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ከሆነ ግን ለሁለቱም አገራት የሚጠቅም አይሆንም" ሲሉ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር በኩል ያለው ግጭት ምንም ለውጥ እንዳላሳየ የገለፁ ሲሆን ፤ ሱዳን ቀድሞ ወደነበረችበት ስፍራ ስትመለስ ኢትዮጵያ ወደ ድርድር ለመመለስ ዝግጁ መሆኗን ዳግም አረጋግጠዋል።

በህዳሴው ግድብ ጉዳይ በተመለከተ የአዲሷ አደራዳሪ አገር ኮንጎ ሪፐብሊክ ልኡካን በካርቱም፣ ካይሮ እና አዲስ አበባ ላይ የየአገራቱን ስሜት ለመረዳት እና መረጃ ለማሰባበስ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ብለዋል።

በቀጣይ ሳምንታት የተቋረጠው የሦስትዮሽ የህዳሴ ግድብ ድርድር ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

የተ.መ.ድ. የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባን በተመለከተም ተጠየቀው ምላሽ ሰጥተዋል : telegra.ph/Ambassador-Dina-Mufti-03-06 (EPA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፁ ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ ሱዳንን ሊጎበኙ ነው። የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርየም ሳዲቅ ኣልመሃዲ የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ከከፍተኛ የሀገሪቱ ልዕካን ጋር በመጪዎቹ ቀናት ሱዳንን እንደሚጎበኙ አሳውቀዋል። በጉብኝቱ አል ሲ ሲ ከአብድል ፈታህ አልቡርሃን ጋርም ይመክራሉ ተብሏል። ምክክር የሚያደርጉትም ስለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ፣ ስለ አካባቢ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንደሆነ…
የግብፁ ፕሬዜዳንት ሱዳን ገቡ።

የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ዛሬ ሱዳን ካርቱም ገብተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ሱዳን የገቡት ከከፍተኛ የሀገሪቱ ልዑክ ጋር ነው።

አልሲሲ ካርቱም ሲደርሱ የሱዳን ሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ተቀብለዋቸዋል።

የአንድ ቀን ቆይታ በሱዳን ይኖራቸዋል የተባለው ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ምክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

ሁለቱ ሀገራት ከቀናት በፊት በጦር ኢታማዦር ሹሞቻቸው አማካኝነት ካርቱም ላይ ወታደራዊ ስምምነት መፈራረማቸው ፤ ካይሮ ላይ ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኩል ውይይት ማድረጋቸው / በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይም አቋማቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰት ነው" - ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

ከቅርብ ቀናት ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሴቶች በከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም ከውጭ ሀገር የገንዘብ ድጋፍ ይደርጋል በሚል የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ በሚል እየተሠራጨ ያለው መረጃ ሀሰት መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

ወ/ሮ አዳነች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

የአ/አ ነዋሪዎች በዚህ የተሳሳተ መረጃ ከመጭበርበር ራሳቸውን እንዲጠብቁ እና ይህንን የተሳሳተ መረጀ የሚያሰራጩ አካላትን ለህግ አስከባሪ አካላት እንዲጠቁሙ ጥሪ ቀርቧል።

@Tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት የተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል ፦

#DireDawaUniversity

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ12ኛ ጊዜ በመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸው 2 ሺህ 93 ተማሪዎችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል ከ700 በላይ ሴቶች መሆናቸ ተገልጿል።

#Yekatit12_Hospital_Medical_College

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ4ኛ እና በ5ኛ ዙር በተለያዩ የህክምና ዘርፍ ያስተማራቸውን 127 ዶክተሮች አስመርቋል።

#AddisAbabaUniversity

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጥቁር አንበሳ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 484 የሕክምና ባለሙያዎችን አስመርቋል። ከምሩቃኑ 209 በስፔሻሊስት፣ ሁለት በዶክትሬት እና 273 በ2ተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ የሕክምና ባለሙያዎች ናቸው።

#MetuUniversity

የመቱ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ ትምህርት ዘርፎ ያሰለጠናቸው 252 ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ አስመርቋል።

ከሰለጠኑባቸው የትምህርት መስኮች ውስጥ ነርሲንግ፣ ፋርማሲ፣ ህብረተሰብ ጤና እና አዋላጅ ነርሲንግ ይገኙበታል።

ከመካከላቸው 93 ሴቶች ናቸው።

#CateringandTourismTrainingCenter

የሆቴልና ቱሪዝም ስራ ማሰልጠኛ ማዕከል (CTTC) በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 425 ተማሪዎችን አስመርቋል።

በዘንድሮ መርሀ ግብር በሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ በድግሪ 16 ተመራቂዎች ፣ በደረጃ 3 በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ 202 ተመራቂዎች ፣ በደረጃ 4 በሆቴል እና ቱሪዝም 157 ተመራቂዎች እንዲሁም በደረጃ 5 በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ 53 ተማሪዎች ነው የተመረቁት።

@tikvahethiopia