TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopiaElection2013 እንደብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከዛሬ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ የምረጡኝ ቅስቀሳ/የምርጫ ዘመቻ የሚደረግበት ጊዜ ነው። በዚሁ በምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ ከግንቦት 24 - ግንቦት 27 ቀን 2013 ዓ/ም የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ የማይቻልበት የጥሞና ጊዜ ነው። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013

ዛሬ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ /የምርጫ ዘመቻ የሚጀምርበት ቀን ነው።

ፖርቲዎች እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴ ደውለን ጠይቀናል።

• ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ህብር ኢትዮጵያ) ፦

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለህብር ኢትዮጵያ ፓርቲ የደወለ ሲሆን አመራሮቹ ዛሬ የምርጫ ቅስቀሳ እንዳልጀመሩ ገልፀዋል።

ነገር ግን ፓርቲው ምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ለመጀመር ሰፋ ያለ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቆናል።

በዚህ ሳምንት የምርጫ ቅስቀሳ እንደሚጀምር ተገልጾልናል።

• የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) ፦

የፓርቲውን አመራሮች በስልክ አግኘተን ያነጋገርናቸው ሲሆን ኢህአፓ ለምርጫ ቅስቀሳ ዛሬ እንዳልጀመረ ገልፀውልናል።

ነገር ግን ኢህአፓ ለምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን ቅድመ ሁኔታዎችን የማመቻቸት እንዲሁም ሌሎች ሰፊ ዝግጅቶችን እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቆናል።

በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥም ወደቅስቀሳ ይገባል።

• የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲት ፓርቲ (ኢሶዴፓ)፦

በቅርቡ ከመድረክ በይፋ ለተለያየው ኢሶዴፓ የምርጫ ቅስቀሳውን በተመለከተ ጥያቄ አቅርበን ነበር ዛሬ ምርጫ ቅስቀሳ እንዳልጀመር ገልጾልናል።

ፓርቲው ወደፊት ቀስ ብሎ የምርጫ ቅስቀሳውን እንደሚጀምር አሳውቆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ፣ በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ፓርቲው በአዲስ አበባ አብሮ ለመስራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) በጋራ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብሩን ለሚመለከተው የመንግስት አካል በደብዳቤ ማሳወቁንም ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013

በምርጫ 2013 ክልሎች የሚኖራቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) የውክልና መቀመጫ፦

- የሲዳማ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኖረው መቀመጫ 19 

- የደቡብ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና 104  ደቡብ ክልል ላለፉት 26 ዓመታት ገደማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው ውክልና ወይም መቀመጫ 123 ነበር፤ ሲዳማ ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን ከቻለ በኃላ ፣ ደቡብ የሚኖረው መቀመጫ ብዛት 104 ሆኗል።

- ኦሮሚያ ክልል በነበረበት 178፣ 

- አማራ ክልል በነበረበት 138፣

- ሶማሌ ክልል በነበረበት 23፣ 

- አዲስ አበባ ከተማ በነበረበት 23፣

- ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በነበረበት 9፣ 

- አፋር ክልል በነበረበት 8፣ 

- ጋምቤላ ክልል በነበረበት 3፣

- ሐረሪ ክልል በነበረበት 2 እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ በነበረበት 2 ሆነው ይቀጥላሉ።

6ኛው አጠቃላይ ምርጫ በትግራይ ክልል እንደማይከናወን ምርጫ ቦርድ ቀድሞ ያስታወቀ ሲሆን፣ ከሰሞኑ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው የክልሎች የፓርላማ ውክልና ድርሻ ውስጥም የትግራይ ክልል አልተገለጸም። 

ይሁን እንጂ ላለፉት አሥርት ዓመታት የትግራይ ክልል የፓርላማ ውክልና 38 እንደሆነ ይታወቃል።

ይህንን ከግምት በማስገባት ሥሌት ሲደረግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጠቃላይ መቀመጫ ብዛት ከነበረበት 547 አልተለወጠም።

(ከሪፖርተር ጋዜጣ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EthiopiaElection2013 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ፣ በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል። ፓርቲው በአዲስ አበባ አብሮ ለመስራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) በጋራ…
#EthiopiaElection2013🗳

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ አካሂዷል።

አብን ከአ/አ ከተማ በተጨማሪ በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ፣ ደብረብርሃን ከተሞች የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻውን ዛሬ በይፋ እያስጀመረ ይገኛል።

አብን በአዲስ አበባው የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ ከዋና ጽህፈት ቤቱ በመነሳት መድረሻውን መስቀል አደባይ ያደረገ መርሃ ግብር አካሂዷል።

ይህ መርሃ ግብር አብን በአዲስ አበባ አብሯቸው ለመስራት ስምምነት ካደረገባቸው ፓርቲዎች ጋር በመሆን ያከናወነው ነው።

በመስቀል አደባባይ ንግግር ያደረጉት የአብን ሊቀመንነር ረ/ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ አብን ከእህት ድርጅቶች ጋር በመሆን የሕዝብን አመኔታና ይሁንታ ወደ ፖለቲካ ውክልና የሚቀይርበትን ትልም ነድፎ ወደስራ ገብቷል ብለዋል።

ማንኛውም ዜጋ በሰላም እና በደኅንነት ወጥቶ የሚገባባት ፤ የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ፣ ሰብአዊ መብቶች ፣ ፍትህ እና ርትዕ የተከበረባት፣ ያለልዩነትና መድልኦ በነፃነት መንቀሳቀስ፣ መኖርና ሰርቶ መበልፀግ የሚቻልባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ቆርጦ ተነስቷል ሲሉም ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013

በመተከል ዞን በሁሉም ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያዎች መከፈታቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።

የፀጥታ ችግር በነበረበት የቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን ላይ በሁሉም ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ መክፈቱን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

በመተከል ዞን በሚገኙት 7 ወረዳዎች የምርጫ ጣቢያ መከፈቱን ያስታወቁት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ናቸው፡፡

ምርጫ ቦርድ በዛሬው እለት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚሁ ውይይት ላይም በስድስት ክልልሎች ላይ የእጩ ምዝገባ መጀመሩን ዋና ሰብሳቢ አስታውቀዋል።

የእጩ ምዝገባው የተጀመረባቸው ቦታዎች አዲስ አበባ ፣ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሲሆኑ በተቀሩት ክልሎች ደግሞ ከዛሬው እለት ጀምሮ የእጩ ምዝገባ ሂደቱን ይጀምራሉ ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢዜማ አባላቶቼ ተደበደቡብኝና ታሰሩብኝ ክስ የመንግስት ምላሽ ፦

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ከአስራ አንድ በላይ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውና ለቀናት መታሰራቸው በኃላም ከእስር መፈታታቸውንአስታውቋል።

ኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ፥ "ባለን መረጃ የካቲት 4 የመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ይደረግ ነበር በኃላም ይህ ሰልፍ ተሰርዞ ምርጫ ቅስቀሳ እንዲደረግ በተያዘለት ጊዜ ሲደረግ ኢዜማ የምርጫ ቅስቀሳ ከማድረግ ተቆጥቦ ሰልፉ ከተካሄደ በኃላ ነው ወደ ቅስቀሳ የገቡት ከዚህ በኃላ ነው እስርና ድብደባው በአባላቶቻችን ላይ የደረሰው" ብለዋል።

የፓርቲው አባላት ሲታሰሩ የኢዜማን አርማ መያዛቸውን፣ የፓርቲውን የምርጫ ምልክት ያለበት ቲሸርትም ለብሰው እንደነበር በኮንሶ ዞን የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር ገልፀዋል።

ምክትል ሊቀመንበሩ ፥ የአካባቢው ፀጥታ አካላት የኢዜማን ቲሸርት የለበሱ አካላትን እየቀጠቀጡ እና እየደበደቡ ነበር ብለዋል ፤ አንደኛው የኢዜማን ቲሸርት የለበሰ ሃኪምም በሳንጃ ሁሉ ተወግቷል ሲሉ ገልፀዋል።

መንግስት በኢዜማ አባላት ላይ በማህበራዊ ኑሮ ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ጫና እያዳደረ መሆኑንም አብራርተዋል። ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑ አሳውቀዋል።

"እነሱ በየአዳራሹ ቅስቀሳ ያደርጋሉ ፣ ቀበሌዎች ላይም በመንግስት ሃብት (ሞተር እና መኪና) እንደልባቸው እየተንቀሳቀሱ ቅስቀሳ ያደርጋሉ እኛ ግን በራሳችን ፅ/ቤታችን እንኳን እንዳንሰበሰብ ሊያደርጉን ነው" ብለዋል።

የታሰሩት የኢዜማ አባላት ማክሰኞ እለት ተፈተዋል።

የኮንሶ ዞን የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሃሰን ወላሎ ፥ በኢዜማ ምርጫ ቅስቀሳ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ብለዋል። ነገር ግን መንግስት ፈርሷል እያሉ ኢ-ህገመንግስታዊ የሆነ ሰንደቅ ዓላማ በመያዝ በአደባባይ ሲያውጁ/ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ ሲጥሩ የነበሩ ግለሰቦች እንደነበሩ ገልፀዋል።

#EthiopiaElection2013

https://telegra.ph/EZEMA-02-25
የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ እንቅስቃሴ ፦

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳውን ማካሄድ መጀመሩን የፓርቲው ሊቀመንበር አብዱልቃድር አደም ገልፀውልናል።

ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ የጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን በጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ አድርጓል።

በቀጣይ በስፋት በሀገር አቀፍ ደረጀ ወደ ምርጫ ቀስቀሳ እንደሚገባ ዶ/ር አብዱልቃድር አሳውቀውናል።

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አሁን ላይ የእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ነው። በየክልሉ ያሉት የፓርቲው አደረጃጀቶችን ሰፊ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ የሚገኙት በዚሁ በእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ ነው።

ጎን ለጎን እንዲሁም ምዝገባው እንዳለቀ ነፃነት እና እኩብነት ፓርቲ በሰፊው የምርጫ ቅስቀሳ ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የአዲስ አባባ ቅስቀሳ እንዴት ነበር ?

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በጀመረበት አዲስ አበባ ይሄ ነው ተብሎ የሚገልፅ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠመው አሳውቆናል።

ቅስቀሳው በሁሉም ክ/ከተማ በሰላማዊ እና በተሳካ ሁኔታ ነው የተካሄደው።

ነገር ግን ፓርቲው ከወዲሁ ወደክልል በሚወርድበት ጊዜ ችግር ይገጥመኛል የሚል ስጋት አለው ይህም የመነጫው አሁን ላይ ሌሎች ፓርቲዎች ችግር እየገጠመን ነው በማለት ሪፖርት እያደረጉ በመሆኑ ነው።

በሌላ በኩል ፦

በርከት ያሉ የቲክቫህ አባላት ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ለምንድነው በስፋት በሚዲያዎች ላይ የማናገኘው ? የሚል ጥያቄ አንስተው ጥያቄ አቅርበዋል ፤ ለዚህም የፓርቲውን ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድርን ምላሽ እንዲሰጡን ጠይቀናል።

ዶክተር አብዱልቃድር፥ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ባሉት የሚዲያ አማራጮች እንደሚንቀሳቀስ ገልፀዋል ፤ ነገር ግን የፖለቲካ ጉዳይ ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ ፓርቲው በሚዲያ ወጥቶ ወደህዝብ የሚያስተላልፈው መልዕክት በህዝብ ላይ ችግር የሚፈጥር እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።

#EthiopiaElection2013 #TikvahEthiopia

https://telegra.ph/Freedom--Equality-Party-02-25
#EthiopiaElection2013

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሀይማኖት መምህርነታቸውና በሚሰጧቸው ማህበራዊ ሂሶች የሚታወቁት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመጪው 6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በግላቸው እንደሚወዳደሩ አሳውቁ።

ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለኢትዮጵየ ቼክ ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ "...በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እወዳደራለሁ" ብለዋል።

"ሀሳብ ከመስጠት ባለፈ በሂደቱ ተሳታፊ መሆን ይገባል ብዬ ስላመንኩ በምርጫው ለመሳተፍ ወስኛለሁ" የሚሉት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 12/13 ምርጫ ክልል በግል ተወዳዳሪነት ዕጩ ሆነው አስረድተዋል።

ለምን በግል ለመወዳደር ፈለጉ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፥ "...ከፓርቲ ፖለቲካ ይልቅ ግላዊ ፖለቲካ የተሻለ ነው ብየ ስለማምን ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ www.ethiopiacheck.org
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013

አብን በተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማደረጉን ገለፀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለምርጫ 2013 የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

አብን በም/ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ግንደወይን ከተማ እና በማቻከል ወረዳ ደጋሰኝና ደብረቀለም ታዳጊ ከተሞች ፣ እና በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት «ታሪክ እየጠበቅን ታሪክ ለመስራት ድምጻችንን ለአብን እንስጥ!» በሚል መሪ ቃል የካቲት 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ እንዳካሄደ አሳውቋል።

አብን ከየካቲት 14/2013 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013

"...የእጩ ተወዳዳሪዬ ቤት በጥይት ተደብድቧል" - የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜ ሰሌዳ እንደሚያሳየው ዛሬ የእጩዎች ምዝገባ ተጠናቋል።

መኢአድ በዘንድሮው ምርጫ በፌዴራል ደረጃ መንግስት ለመስረት በሚስችል የምክር ቤት ወንበር ቁጥር እንደሚወዳደር እና እጩዎችንም በዚህ ደረጃ ማስመዝገቡን አሳውቋል።

መኢአድ በእጩ ማስመዝገብ ሂደቱ በጎንደር የአንድ እጩ ተወዳዳሪው ቤት በጥይት መደብደቡ የገጠመው ከፍተኛው ችግር እንደሆነ ገልጿል።

በሌላ በኩል ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ላይ እጩ ተወዳዳሪው ማስፈራሪያና ዛቻ እንደደረሰበት አሳውቋል።

ምንም እንኳን ችግሮች ቢኖሩም ሂደቱ ጥሩ የሚባል እንደነበር ገልጿል።

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ትናንት እንዳስታወቀዉ እስከ ትናንት ድረስ በምርጫዉ ለመወዳደር ምልክት ከፀደቀላቸው 53 የፖለቲካ ድርጅቶች ዕጩ ያስመዘገቡት 15ቱ ብቻ ናቸው።

መረጃው የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦነግ በምርጫ 2013 ይሳተፋል ?

ትላንት በተጠናቀቀው የመጀመሪያው ዙር የእጩዎች ምዝገባ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አንድም እጩ አላስመዘገበም።

የኦነግ ጊዜያዊ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ፥ ኦነግ ምንም የእጩ ምዝገባ አለማድረጉ በምርጫው ላለመሳተፉ ጉልህ ማሳያ ነው ብለዋል።

አቶ በቴ፥ "... በእኛ በኩል በተደጋጋሚ ስንገልፅ እንደነበረው ቢሮዎቻችን ፣ ዋና ፅ/ቤቶቻችን ጨምሮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኑ ፣ ነፃ እንቅስቃሴ እንደድርጅት መታገዱ ፣ አመራርና አባሎቻችን ያለህግ አግባብ መታሰራቸው ምርጫ ላይ በምናደርገው ተሳትፎ ላይ ትልቅ ተፅእኖ አላቸውና እነዚህ ችግሮች ሳይፈቱ መሳተፍ እንደማንችል ስንገልፅ ነበር ፤ በዚህ ሁኔታ እጩ ማስመዝገብ አልቻልንም ስለዚህ በምርጫ ሂደቱ ተሳታፊ አይደለንም" ብለዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እስከ ቀጣዩ ጠቅላላ ጉባኤ ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ከዚህ ቀደም የተነገረላቸው አቶ ቀጄላ መርዳሳ (የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ) በበኩላቸው ፓርቲው ለ7 እና 8 ወር ችግር ላይ ስለነበር እጩ ለማቅረብ አስቸጋሪ እንደበር ገልፀዋል።

አቶ ቀጄላ ፥ ፓርቲው በጠቅላላ ጉባኤ የውስጥ ችግሮቹን ፈቶ በወጥ አመራር በምርጫ 2013 ለመሳተፍ እጬዎችን ለማስመዝገብ በተለየ ሁኔታ ጊዜ እንዲራዘምለት ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑን አሳውቀዋል።

#EthiopiaElection2013 #DW #OLF
https://telegra.ph/Oromo-Liberation-FrontABO-03-05
#EthiopiaElection2013

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በምርጫ እለት ድንገተኛ አደጋዎች ቢያጋጥሙ እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችን ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ቢሮው ፥ ከምርጫ አስቀድሞ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ከምርጫ በኋላ ለሚፈጠሩ ችግሮች ዝግጁ በመሆን እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮው የጤና ምርምር ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ዳይሬክተርና የኮቪድ-19 ማስተባበሪያ መዕከል ምክትል አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ዳምጠው ፥ በምርጫ ወቅት ኮቪድ-19 እንዳይስፋፋ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች የሚሰጡና ድንገተኛ አደጋዎች ቢያጋጥሙ ወይም ግጭቶች ቢኖሩ እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ በትምህርት ቤቶች ላይና በመገናኛ ብዙኃን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ይሰራል ብለዋል።

አቶ ዳንኤል ፥ በምርጫ ወቅት ድንገተኛ አደጋዎች ቢያጋጥሙም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሰው ኃይልን በማደራጀት፤ የጎደሉ ህክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶችን የሟሟማላት ስራ እንደተጀመረና ቀጣይነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያዎች ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ዳንኤል ከምርጫው በኋላም የኮሮና ቫይረስ ሊስፋፋ ስለሚችል ሌላ ተጨማሪ 5 መቶ የጽኑ ህሙማን አልጋዎች ዝግጁ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌሎች የጤና ስጋቶችም ካሉ በአቅራቢያ የሚገኙ 20 የጤና ተቋማትና እንዲሁም ሌሎች የግል የጤና ተቋማትን ዝግጁ በማድረግ ቢሮው መስራቱን ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ አሐዱ 94.3

@tikvahethiopia