የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ እንቅስቃሴ ፦

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳውን ማካሄድ መጀመሩን የፓርቲው ሊቀመንበር አብዱልቃድር አደም ገልፀውልናል።

ፓርቲው የምርጫ ቅስቀሳ የጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን በጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ አድርጓል።

በቀጣይ በስፋት በሀገር አቀፍ ደረጀ ወደ ምርጫ ቀስቀሳ እንደሚገባ ዶ/ር አብዱልቃድር አሳውቀውናል።

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አሁን ላይ የእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ በትኩረት እየሰራ ነው። በየክልሉ ያሉት የፓርቲው አደረጃጀቶችን ሰፊ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ የሚገኙት በዚሁ በእጩ የማስመዝገብ ስራ ላይ ነው።

ጎን ለጎን እንዲሁም ምዝገባው እንዳለቀ ነፃነት እና እኩብነት ፓርቲ በሰፊው የምርጫ ቅስቀሳ ለመስራት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የአዲስ አባባ ቅስቀሳ እንዴት ነበር ?

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በጀመረበት አዲስ አበባ ይሄ ነው ተብሎ የሚገልፅ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠመው አሳውቆናል።

ቅስቀሳው በሁሉም ክ/ከተማ በሰላማዊ እና በተሳካ ሁኔታ ነው የተካሄደው።

ነገር ግን ፓርቲው ከወዲሁ ወደክልል በሚወርድበት ጊዜ ችግር ይገጥመኛል የሚል ስጋት አለው ይህም የመነጫው አሁን ላይ ሌሎች ፓርቲዎች ችግር እየገጠመን ነው በማለት ሪፖርት እያደረጉ በመሆኑ ነው።

በሌላ በኩል ፦

በርከት ያሉ የቲክቫህ አባላት ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ለምንድነው በስፋት በሚዲያዎች ላይ የማናገኘው ? የሚል ጥያቄ አንስተው ጥያቄ አቅርበዋል ፤ ለዚህም የፓርቲውን ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድርን ምላሽ እንዲሰጡን ጠይቀናል።

ዶክተር አብዱልቃድር፥ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ባሉት የሚዲያ አማራጮች እንደሚንቀሳቀስ ገልፀዋል ፤ ነገር ግን የፖለቲካ ጉዳይ ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ ፓርቲው በሚዲያ ወጥቶ ወደህዝብ የሚያስተላልፈው መልዕክት በህዝብ ላይ ችግር የሚፈጥር እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።

#EthiopiaElection2013 #TikvahEthiopia

https://telegra.ph/Freedom--Equality-Party-02-25