TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Emirates

ኤሚሬትስ አዲሱን የዓለም አቀፍ "ይህ ቅጣት ነው" የተሰኘው ዘመቻ አካል የሆነ "ሕገወጥ ሰዎች ዝውውር ምንድነው?" የተሰኘ ፊልም ከታዋቂው አይርላንዳዊ ፊልም አክተር ሊያም ኒሰን ጋር በትብብር ያዘጋጀውን አጭር ፊልም ይፋ አድርጓል።

አዲሱ አጭር ፊልም በዓለም ዙሪያ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ብዝበዛ ዙሪያ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለመቀየር እና ማስተማር አላማ ያለው ነው።

ከጥቅምት ወር ጀምሮ በሁሉም በረራዎች ውስጥ ከሚኖሩት የመዝናኛ ቪዲዮች አንዱ አካል በማድረግ ይህን ልዩ መልእክት በማስተላለፍ ኤሚሬትስ ስለዚህ ዓለም አቀፍ ችግር ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ብሎም በረካታ ስለ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ምንነት የተሻለ መረጃ ያስጨብጣል ብሎ ተስፋ አድርጓል።

ይህ አንቅስቃሴም ከፍተኛ ግንዛቤ በመፍጠር ብዙ ህገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪ ተጠርጣሪዎች ተለይተው ሪፖርት ስለሚያስችል ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑትን ከአደጋ ለመከላከል ያስችላል ተብሎ ይታመናል።

#251communication

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባህር ዳር ደም ባንክ ተሸለመ !

በኢትዮጵያ ካሉት 40 የደም ባንክ አገልግሎት የባህርዳር ደም ባንክ የ2012 ዓመት ምርጥ 1ኛ በመሆን ተሸለመ።

ትላንት ጥቅምት 6/2013 ዓ/ም በጎንደር ሀይሌ ሪዞርት የተዘጋጀውን የእውቅና የዋንጫ እና ምስክር ወረቀት ተቀብሏል።

የባህር ዳር ደም ባንክ የተሸለመው ፦

- በክልሉ በደም እጥረት እንዳይኖር በማድረግ
- አውቶማቲክ እና በኢትዮጵያ ብቸኛ ሶፍትዌር በመስራት
- አለማቀፋዊ ጥናታዊ ጹሁፍ በማሳተም
- ሌሎችን ደም ባንኮች በማገዝ ነው።

የደም ባንኩ ከሽልማቱ በኃላ አብረውት ለነበሩ በጎ ሰዎች፣ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች፣ የባህር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ፣ የደም ባንክ ክበባት እና ሰራተኞች ፣ ደም ልገሳ አስተባባሪዎች፣ ደም ለተጠቃሚዎቹ ፣ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር እና ነዋሪዎች ፣ ለማህበራዊ ድረ ገጽ ጸሀፊዋች ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በአርሜኒያ እና አዛርባጃን መካከል ተደርጎ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ከአንድ ቀን በላይ መዝለቅ አልቻለም። አዛርባጃን በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀችው የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ከአንድ ቀን በኋላ ለዛሬ እሁድ አጥቢያ የአርሜኒያ ኃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት 7 ሰዎች ተገድለዋል። ጥቃቱ የተሰነዘረው በአዛርባጃንዋ የጋንጃ ከተማ የመኖርያ መንደሮች ላይ ነው ተብሏል። በጥቃቱ…
#UPDATE

የአዘርባጃን ባለስልጣናት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቁት በጋንጃ ከተማ ላይ በኤርሜንያ በተፈፀመ የሚሳኤል ጥቃት 12 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል።

ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

በአርሜኒያ እና አዘርባጃን መካከል በሩሲያ የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ከተጣሰ በኃላ በ2ቱ ሀገራት መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ መቀጠሉ እየተገለፀ ይገኛል። በጦርነቱ እስካሁን በርካቶች አልቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#LIVE

የሴቶች ማራቶን መካሄድ ጀምሯል !

#ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በጉጉት የሚጠበቁበት የግማሽ ማራቶን ውድድር ከ ጀመረ ጥቂት ደቂቃዎችን ተቆጠርዋል።

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን!

@tikvahethsport
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሴቶች ማራቶን ተጠናቋል !

ኬንያዊቷ ጄፕንችሩ ውድድሩን በበላይነት አጠናቃለች ።

ጀርመናዊቷ ኬጄይታ ሁለተኛ በመውጣት አጠናቃለች።

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት የለምዘርፍ የኋላው ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ዘይነባ ይመር እና አባብል የሻነህ አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል ።

@tikvahethsport
#UPDATE

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በ11 ቀበሌዎች የተከሰተዉና በሰብል ላይ ወድመት እያደረሰ ያለዉን የአንበጣ መንጋን ለመቆጣጠር ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በአንድ ኤሊኮፕተር የኬሚካል መርጨት ስራ እየተሰራ ነዉ፡፡

በተለይም በአዳማ ቀበሌ ልዩ ስሙ "ሲዳ" በሚባል አካባቢ የአንበጣ መንጋዉ በስፋት ሰፍሮ በሚገኝበት ቦታ የኬሚካል ርጭቱ የተከናወነ ሲሆን ከኬሚካል ርጭቱ ጎን ለጎን ሰብሎችን በማጨድ የማንሳት ስራም እየተከናወነ ይገኛል።

የሰብል ማሰባሰብ ስራው እየተሰራ የሚገኘው ፦
- በወረዳውና በከተማ አስተዳደር ህዝብ ፣
- በአማራ ክልል ልዩ ሀይል አባላት ፣
- ከሀገረ ማሪያም፣ በረኸትና አንጎለላና ጠራ ወረዳዎች በመጡ ሰዎች ጭምር ነው።

#MenjarShenkoraWerda
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የጥንቃቄ_መልዕክት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞቹ ከሀሰተኛ የብር ኖቶች እንዲጠነቀቁ መልዕክት አስተላልፏል።

አዲሶቹን የብር ኖቶች አስመስሎ በማተም ሀሰተኛ ገንዘብ የማሰራጨት ህገ-ወጥ ተግባር በአንዳንድ አካባቢዎች እየታየ መሆኑን ባንኩ ገልጿል።

አዲስ የታተሙት የብር ኖቶች በአካላቸው ላይ የሚገኙ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ያሉባቸው እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የደህንነት መጠበቂያ ያላሟሉ ወይም ተመሳስለው የተዘጋጁ ገንዘቦቸን የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ግለሰቦች ካጋጠሟችሁ ወዲያውኑ በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ/የጸጥታ አካል አሳውቁ ተብሏል።

ህብረተሰቡ ሀሰተኛውን የብር ኖት ከእውነተኛው ለመለየት ያስችለው ዘንድ የአዲሶቹን የብር ኖቶች የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION📣

በዚህ ሰዓት የባቲ ወረዳ አዋሬ ቀበሌ "ከታሪ ጎጥ" በከፍተኛ ሁኔታ በበረሀ የአንበጣ መንጋ ተወሯል።

Awwaara obomboleettin kaase kan fakkaatu kun hoomaa awwaannisaa ganda Awwaaree gooxii Kataariitti weeraree argamudha. (ባቲ ወረዳ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION📣

ሀረሪ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ ተከስቷል።

የአንበጣ መንጋው በክልሉ ከተከሰተ ጀምሮ ከክልሉ ህዝብና ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው።

በአጎራባች አካባቢዎች በአውሮፕላን የታገዘ ርጭት መደረጉን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ከፍተኛ መጠን ያለው የአንበጣ መንጋ እየታየ ይገኛል።

በክልሉ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋን ለመከላከል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንዲረባረብ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጣና ሐይቅን ከእንቦጭ የመታደግ ዘመቻ !

እንቦጨን ከጣና ሃይቅ የማስወገድ ዘመቻን የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 9፣ 2013 ዓ.ም በይፋ ለማስጀመር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ዘመቻው የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የሚጀመረው።

በዚህ ጉዳይ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተከታዩን መረጃ ሰጥተዋል ፦

- አረሙን ከውሃው ለማስወገድ ፣ መንቀል ፤ በአንድ ቦታ አከማችቶ ማቃጠል ወይንም መቅበር በዘመቻው የሚሰራ ስራ ነው ፤ ለዚህ አስፈላጊ የሆኑ ገልባጭ ተሸከርካሪዎች ፤ ማጨጃ መሳሪያዎች ሞተር ሳይክሎች እና ጀልባዎች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች የሚቀርቡበት መንገድ ተመቻችቷል፡፡

- ለዘመቻው 95 ሚሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን ክልሎች ፤ ከተማ አስተዳደሮች ፤ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የገንዘብ ድጋፉን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአሁኑ ሰአትም ለዘመቻው የሚያስፈልገውን ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ ተጀምሯል፡፡

- እንቦጭ የተንሰራፋበትን የጣና የውሃ አካል ሁሉም ክልሎች ፤ ከተማ አስተዳደሮች እና የፌደራል እና የክልል ተቋማት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት በመከፋፈል በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ የሚስወግዱት ይሆናል፡፡

በነገራችን ላይ በአሁኑ ሰአት የእንቦጭ አረም ጣና ሃይቅን በሚያዋስኑ 9 ወረዳዎች በሚገኙ ሰላሳ (30) ቀበሌዎች ላይ ተንሰራፍቶ ይገኛል።

Via Ministry Of Water, Irrigation & Energy
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ትኩረት

ምዕራብ ሀረርጌ ፣ ጉባ ቆርቻ ወረዳ ላይ የአንበጣ መጋው ባደረሰው ጉዳት ምንም የተረፈ ሰብል የለም።

የሰው ህይወት በረሃብ እንዳይጠፋ መረባረብ ይኖርብናል።

Goodina Haarargee lixaa, Aanaa Gubbaa Qorichaatti hubaatii Awwaannisni geessiseen midhaan tokko akka hin hafin adda baafachuu danda'eera.

Lubbuun ummataa akka beelaan hin dhumne baraaruu qabna!

እዮብ ወንዱ
ጥቅምት 7/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ትኩረት_ለጉባቆርቻ_ወረዳ

ከወረዳው አመራሮች ተከታዩ መረጃ ተሰጥቶል፦

- አንበጣ መንጋው በወረዳው ባሉት 24 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ውድመት አድርሷል።

- የአካባቢው አርሶ አደር የሚያመርተው ተመሳሳይ ምርት ነው ማሽላ፣ በቆሎና ሽኩርት ወድሟል/ዜሮ ሆኗል።

- ይሄ የሚመረተው ምርት ከዚህ ቀደምም ከአመት አመት የሚያደርሰው አልነበረም እንኳን ይሄ ተጨምሮበት።

- የመንግስት መሰሪያ ቤቶች ሳይቀር ተዘግተው ለመከላከል ጥረት ቢደረግም ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ መንጋው ውድመት አድርሷል።

- አርሶ አደሩ ተስፋ ቆርጧል፣ ሞራሉም ተነክቷል።

- ሚዲያዎችም ትኩረት ሰጥተው ወደአከባቢው መጥተው በአካል አገኝተው አይተው ለህዝብ ማድረስ አለባቸው።

- አካባቢው የመንግስትን የድርጅቶችን፣ የሁሉንም አካል እገዛ ይፈልጋል።

የአርሶ አደሩን ህይወት መታደግ የራስን ህይወት መታደግ ነው !

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,548
• በቫይረሱ የተያዙ - 600
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 471

በአጠቃላይ በሀገራችን 88,434 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,346 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 42,099 ከበሽታው አገግመዋል።

299 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SHARE #ሼር

አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ ለራያ ቆቦና ቆቦ ከተማ አርሶ አደሮች !

(ለሚመለከተው ሁሉ)

በራያ ቆቦ ወረዳ ከመስከረም ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የአንበጣ መንጋ መከሰቱን እና ሰብል ማውደሙ ይታወቃል።

እስከዛሬ ተከስቶ ከነበረው የከፋ በብዛቱም እንዲሁም ሰብልን በማውደም አደገኛ የሆነ የአንበጣ መንጋ በአዲስአለም ፣ በአቧሬ ፣ በገደመዩ አካባቢ ተከስቷል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ወደነዚህ አካባቢ በመሄድ የተለመደውን ቀናነቱን ያሳይ።

ይህን መልዕክት የሚያይ የዞን የክልል የፌደራል እና ሌሎች አጋራ አካላት በአስቸኳይ የአውሮፕላን ርጭት እንዲካሄድ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መንገሻ አሸብር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia