TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

አዲሱ የብር ኖት መሰራጨት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንክ ቅርንጫፎች መሰራጨቱ ተገልጿል !

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ ፦

- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብሔራዊ ባንክን በመወከል አዲሱን የብር ኖት ለግል ባንኮች ጭምር በማሰራጨት ላይ ነው።

- አዲሱን የብር ኖት ማሰራጨት ከተጀመረ ከመስከረም 6/2013 ዓ ም ጀምሮ አስካሁን ባለው ጊዜ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የግል ባንክ ቅርንጫፎች ተሰራጭቷል። ከዚህ ውስጥ 28 ቢሊዮን ብር ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ተሰራጭቷል።

- 22 ቢሊዮን አሮጌው የብር ኖት ወደ ማዕክል ገቢ ተደርጓል።

- 5 ሺ ብር እና ከዛ በላይ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብር ለመለወጥ የሚመጡ ደንበኞች የብሔራዊ ባንክ መመሪያ በሚያዘው መሠረት በቁጥር 63 ሺ ደንበኞች አዲስ የባንክ አካውንት ከፍተዋል፤ ከ 6.4 ቢሊዮን ብር በላይ ተቆጥቧል።

- በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ 3,700 ኤቲኤም ማሽኖች በሙሉ ማለት በሚያስችል ደረጃ አዲሱን የብር ኖት እንዲከፍሉ የማድረግ ሥራ ተሰርቷል።

- ከመቶ ሽ ብር በላይ ብር ለሚቀይሩ ደንበኞች ዛሬ (ጥቅምት 1, 2013) ጨምሮ በቀሩት 5 ቀናት ውስጥ ሰንበትን ጨምሮ በመስራት ላይ ወዳሉት የኢትዮጰጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች በመምጣት በቀነ ገደቡ ሊጠቀሙ ይገባል። (CBE)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ አንዳንድ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለማስጀመር እንደሚቸገሩ እየገለፁ ይገኛሉ።

የካ አባዶ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሀዲስ አለማየሁ ለአዲስ ዘመን ከገለፁት፦

- በኮሮና ምክንያት ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲልም ያለው የተማሪ ብዛት ለማስተማር አስቸጋሪ ነበር።

- አሁንም የክፍል እጥረቱ ሳይፈታ ተማሪዎችን እየመዘገብን ነው። ችግሩን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አውቆ ተጨማሪ 70 ክፍሎችን ለመስራት ቦታ የተለየና ከሞላ ጎደል እቃዎች ያቀረበ ቢሆንም እስካሁን በተግባር የተሰራ ነገር የለም።

- ወቅቱ አስቸጋሪ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በቀጥታ ወደ ትምህርት ገበታ ማስገባት ይከብዳል።

- 70 ክፍሎች ተሰርተው ለአገልግሎት ከዋሉ በ2 ፈረቃ ተማሪዎችን ማስተማር ይቻላል። ሆኖም እስከ መስከረም 29 ድረስ 6 ሺህ 500 ተማሪዎች የተመዘገቡ ቢሆንም ከ8 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደሚኖሩ ይገመታል። በዚህም ትልቅ ችግር ይገጥመናል።

- 76 ሺህ ሊትር የሚይዝ የውሃ ታንከር ተዘጋጅቷል ፤ ይህ ከተማሪዎች ብዛት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ በመሆኑም ቆራጥ ውሳኔ ያስፈልገዋል።

- የተማሪዎች የመመገቢያ አዳራሽ ጭራሽ አለመሰራቱ ሌላው ሥጋት በመሆኑ ትምህርት ለማስጀመር እንቸገራለን።

ፈለገ ዮርዳኖስ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ፈንታሁን ሞላ ለአዲስ ዘመን ከገለፁት ፦

• ትምህርት ለመጀመር የኬሚካል ርጭት ከማካሄድ ውጭ እስካሁን መሬት ላይ የወረደ ሥራ የለም።

• አካባቢው የውሃ እጥረት ያለበት በመሆኑ ከዚህ በፊትም ትልቅ ችግር አስከትሏል። ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገርን ቢሆንም እስካሁን መፍትሄ አልተገኘም።

• የውሃ ችግሩ በፍጥነት መፈታት ካልቻለ ትምህርት ለማስጀመር ይከብደናል።

@tikvahethiopiaBoT
#ATTENTION📣

"የአንበጣ መንጋ እህሉ አልበቃ ሲለው በፎቶው እንደምታዪት በዛፎች ላይ እያረፈ ይገኛል። የአርሶ አደሮችን አመታዊ ሰብል አውድሞ የከብቶች መኖ እና ሌሎች ደኖችን በከፍተኛ ሁኔታ እያወደመ ነው።" - መርሳ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ኬሚካል የሚረጩ 5 ተጨማሪ አውሮፕላኖችን ከውጪ ለማስገባት ጥረት እያደረገ መሆኑ ግብርና ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ከተናገሩት ፦

- የአንበጣ መንጋ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ፣ አማራ ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተከስቷል።

- የመከላከል ሥራው በአውሮፕላን ኬሚካል ርጭት ጭምር በመከናወን ላይ ነው። ችግሩ እየሰፋ በመምጣቱ እና ሥራው ላይ ከነበሩት አውሮፕላኖች ሁለቱ በመከስከሳቸው እስከ ረቡዕ ድረስ ተጨማሪ 5 አውሮፕላኖች ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሠራ ነው።

- መንጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች በስፋት እንዳይዛመት ለማድረግ የመከላከል ሥራውን በጥንቃቄ ለመሥራት ጥረት እየተደረገ ነው።

- በአንበጣው ጉዳት የደረሰባቸውን አርሶ አደሮች ለመደገፍ የመለየት ሥራ በመከናወን ላይ ነው።

- የግል ባለሀብቱ የአንበጣ መከላከል ሥራውን እንዲያግዝ ጥሪ ቀርቧል። (etv)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሳወት የ15,000 ብር እገዛ አደርገ !

በትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሰው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) በክልሉ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ የ15,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ለአርሶ_አደሩ_እንድረስለት !

በወረባቦ ወረዳ ውስጥ የተከተሰው የአንበጣ መንጋ አርሶ አደሩ ደክሞ ለፍቶ ያፈራውን ሰብል ወደ ጎተራው ሳያስገባ አንበጣ መንጋው እያወደበት ይገኛል።

ይህንን የሰብል ጉዳትም ለመቀነስ በሰው ሃይል የኬሚካል ርጭት ፣ በባህላዊ መንገድ የመባረር እና በሂሊኮፍተር ኬሚካል ርጭት ቢደረግም የአንበጣ መንጋውን መቆጣጠር አልተቻለም።

በመሆኑም የሲቪክ ማህበራት የመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በአንበጣ መንጋው ሰብላቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች እንዲደግፉ የወረባቦ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች 2.8 ሚሊዮን ማስክ ይከፋፈላል" - ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (Face Mask) ስርጭትን በተመለከተ ክልሎች ለተማሪዎቻቸው ተረክበው እንዲያሰራጩ የሚገልጽ እና ድልድሉንም አስመልክቶ የጊዜ እና የመጠን ዝርዝር ያለው ደብዳቤ ለክልል ትምህርት ቢሮዎች ጽፏል፡፡

በዚህ ደብዳቤ ውስጥ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አልተካተተም፡፡ ይህም በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ ፈጥሯል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠይቀን ተከታዩ መረጃ ተሰጥቶናል ፦

- የተደረገው ድልድል የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ጭምር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያገኙ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

- በደብዳቤው ላይ ማካተት ያልተቻለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቅርቡ ባሳለፈው ውሳኔ ምክንያት ነው፡፡

- አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ ላሉ 26 ሚሊዮን ተማሪዎች የማስክ አቅርቦት እንዲሟላ እየተሰራ ይገኛል፡፡

- ለትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎችም ይህንን ሥርጭት ለማድረስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከወረዳዎች እና ከዞኖች ጋር ግንኙነት ጀምሯል፡፡ ሥርጭቱም በዚያው በኩል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

- አጠቃላይ ወደ 50 ሚሊዮን ማስክ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ 2.8 ሚሊዮን የሚሆነው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የሚከፋፈል ይሆናል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጥቅምት 1/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 104 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 39 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,154 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 99 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ99ኙ መካከል 64 ከምዕ/ጎጃም ዞን ፣ 16 ከባህር ዳር ከተማ ይገኙበታል።

#DireDawa

በድሬዳዋ 142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 47 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 468 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 19 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 471 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 169 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 3,913 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 365 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#Harari

በሐረሪ ባለፉት 24 ሰዓት 120 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 53 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 645 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 50 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 184 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 18 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

@tikvahethiopiaBOT
#ATTENTION📣

በድሬዳዋ የተከሰተ አንበጣ መንጋ በ10 ሺህ ሄክታር ሰብል እና ግጦሽ ሳር ላይ ጉዳት ማድረሱን የአስተዳደሩ የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ለኢዜአ አስታውቋል።

መነሻውን ከሶማሌ ላንድ ያደረገ የአንበጣ መንጋ ከመስከረም 21 ቀን 2013 ዓም ጀምሮ ነው በድሬዳዋ በ22 ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው።

በ4 ሺህ ሄክታር ማሳ ላይ የሚገኝ የበቆሎና ማሽላ ሰብል ላይ ጉዳት አድርሷል፤ በተጨማሪ 6 ሺህ ሄክታር የግጦሽ ሳር ሙሉ ለሙሉ አውድሟል።

በተወሰኑ ቦታዎች ላይ በደረሰ የአተር ሰብል፣ በቲማቲምና ፍራፍሬ ተክሎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

አንበጣ መንጋውን በባህላዊ መንገድ ጭስ በማጨስ እና ድምፅ በማሰማት እና በኬሚካል ርጭት ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ከአቅም በላይ መሆኑን ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የኬሚካል መርጫ አውሮፕላኖች ጥገና ላይ መሆናቸው ችግሩን ያባባሰው መሆኑን ተገልጿል። (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#አስቸኳይ_መልዕክት !

በሓፀቦ አከባቢ የአንበጣ መንጋ እየታየ ስለሆን በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ቦታው በመገኘት የአርሶ አደሩ የመከላከል ስራ እንድትቀላቀሉ ተጠይቋል - (AXUM UNIVERSITY)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,383 የላብራቶሪ ምርመራ 866 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 633 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 84,295 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,287 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 38,316 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE አርመኒያ እና አዘርባጃን በናጎርኖ - ካራባህ ግዛት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው BBC አስነብቧል። የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሁለቱ ሃገራት በሞስኮ ለ10 ሰአታት ከተወያዩ በኋላ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸውን አሳውቀዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአርሜኒያ እና አዛርባጃን መካከል ተደርጎ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ከአንድ ቀን በላይ መዝለቅ አልቻለም።

አዛርባጃን በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀችው የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ከአንድ ቀን በኋላ ለዛሬ እሁድ አጥቢያ የአርሜኒያ ኃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት 7 ሰዎች ተገድለዋል።

ጥቃቱ የተሰነዘረው በአዛርባጃንዋ የጋንጃ ከተማ የመኖርያ መንደሮች ላይ ነው ተብሏል።

በጥቃቱ ከተገደሉት ውጭ ህጻናትን ጨምሮ ሌሎች 33 ሰዎች መቁሰላቸውን የአዛርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ነገር ግን የአርሜኒያ ኃይሎች ውንጀላውን አጣጥለው ይልቁኑ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ የአዛርባጃን ኃይሎችን ተጠያቂ ማድረጋቸው የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል።

በሩስያ አደራዳሪነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ተደርጎ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ለሁለት ሳምንት የሚቆይ እንደነበር የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል። (DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቀወት ወረዳ ወጣቶች እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች የአንበጣ መንጋ መከላከል ስራ በውድቅት ጨለማ እየተጋፈጡት ይገኛሉ።

በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ በቀበሌዎች በመስፈሩና እያደረሰ ያለው የሰብል ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ለነገ ተብሎ የሚታለፍ ባለመሆኑ በባህላዊ ዘዴ የኬሚካል ርጭት ስራ እየተሰራ ይገኛል።

አንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የፀጥታ አካላት የአንበጣ መንጋውን የመከላከል ስራን እየሰሩ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ግብዣ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ !

የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ።

በጉብኝቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኡስማን ሳሌህና የፕሬዜዳንቱ አማካሪያ የማነ ገብረአብም ተካተዋል።

#YemanGMeskel
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ZamZamBank

ዘምዘም ባንክ ለዓመታት ሲያደርግ የነበረው ዝግጅት አጠናቆ ዛሬ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ/ም በይፋ ሥራውን ሊጀምር እንደሆነ ሪፖርተር አስነብቧል።

ባንኩ በኢትዮጵያ 'ከወለድ ነፃ ባንክ' አገልግሎት በመስኮት ደረጃ እንዲሰጥ ምክንያት በመሆን የሚጠቀስ እና የመጀመርያው ከወለድ ነፃ ባንክ ለመሆን ሲንቀሳቀስ የቆየ ባንክ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia