TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ነገ በብሔራዊ መግባባት ላይ ውይይት ይደረጋል! የሀገራችን ፖለቲካ ፓርቲዎች በብሔራዊ መግባባት ላይ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 16 ውይይት ሊያደርጉ መሆናቸውን 'ኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ዘግቧል። በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በሚካሄደው ውይይት ላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።  በነገው ውይይት ሶስት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጥናታዊ ጽሁፍ እንደሚያቀርቡ…
#UPDATE

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በብሄራዊ መግባባት ዙሪያ "በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ" ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት ከ ኢትዮጵያ የምስረታ ዘመን እስከ ስርአቶች ዝርጋታ ታሪካዊ - ጥናታዊ የመነሻ ሃሳብ በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አማካይነት ቀርቦ በፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ውይይት እየተካሄደበት እንደሚገኝ ኤፍ ቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(የኢትዮጵየ ንግድ ባንክ)

የኮንዶሚኒየም ብድር ወርሃዊ ክፍያን በተመለከተ!

የኮሮና ወረርሽኝ የሚያስከትለውን የኢኮኖሚ ጫና ምክንያት በማድረግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኮንዶሚኒየም ብድር ተበዳሪዎች የ3 ወር (ከሚያዝያ 2012 እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም) የወርሃዊ ክፍያ የእፎይታ ጊዜ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ይህ የእፎይታ ጊዜ በሰኔ 2012 ዓ/ም የተጠናቀቀ ስለሆነ የባንኩ ደንበኞች ክፍያቸውን ከ ሀምሌ ወር 2012 ዓ/ም ጀምሮ መክፈል መጀመር እንዳለባቸው ባንኩ አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Congratulations!

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለአስራ አራተኛ (14) ዙር ያሰለጠናቸው ከፍተኛ መኮንኖች በወታደራዊ አመራርነት ዛሬ አስመርቋል።

ኮሌጁ በከፍተኛ ስልታዊ አመራር ካስመረቃቸው ዘጠና ስልጣኞች አስራ ስምንቱ ከአምስት የጎረቤት ሀገር የመጡ ናቸው።

በዛሬው የምረቃ ስነ ስርዓት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሃመድ ተገኝተው እንደነበር ከመከላከያ ሰራዊት ገፅ ገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrHirutKassaw

የሻደይ፤ አሸንድየ እና አሸንዳ በዓላት በማይዳሰሱ ቅርስነት የመመዝገብ ጉዳይ በሚቀጥለው አመት በዩኔስኮ ድምጽ እንደሚሰጥበትና እንደሚመዘገቡ እንደሚጠበቅ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ለአልዓይን ተናግርዋል።

የዘንድሮ አሸንዳ፣ ሻደይ እና አሸንድየ በዓላት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ምክንያት በአደባባይ እየተከበሩ አይደለም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ስፖርታዊ ጉዳዮችን መከታተያ ገፅ : @tikvahethsport
"ሃኪምን ለቤት አስቀምጦ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መከላከል አይቻልም፤ ሃኪምን ከቤት አስቀምጦ የዜጎችን ጤንነት መጠበቅ አይቻልም!" - በ2012 ተመርቀው ቋሚ ቅጥር ያልፈፀሙ ጠቅላላ ሃኪሞች

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
FDRE Defense Force.pdf
599.5 KB
የመከላከያ ሚኒስቴር ቀጥሎ በተመለከቱት ልዩ ልዩ ሙያዎች የሠራዊት አባላትን መመልመል ይፈልጋል !

- መደበኛ ሰራዊት
- ሎጂስቲክስ ሞያዎች
- ፋይናንስ ዘርፍ
- በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ስር ላሉ ሞያዎች
- ኮማንዶ

ማስታወቂያውን በማንበብ እሰከ ነሀሴ 30 ቀን 2012 ድረስ ብቻ በየአቅራቢያችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OLF #BALDERAS

ዛሬ "በብሄራዊ መግባባት" ላይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ባካሄዱት ውይይት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ጥሪ እንዳልተደረገለት አሳውቋል።

ፓርቲው ዛሬ በብሔራዊ መግባባት ላይ ውይይት ሊያደርጉ ነው መባሉ የሰማው ከሚዲያ እንደሆነና ከዚህ ባለፈ ለድርጅቱ የቀረበ ጥሪ የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በፌስቡክ ገጹ እንደገለጸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በብሄራዊ መግባባት ዙሪያ "በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ" እያካሄደ ያለው ውይይት ሁሉን አሳታፊ አይደለም ሲል ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

Via @tikvahethmagazine

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"እኔ እያለሁ ወገኔ አይራብም"

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፣ ዛውያ ቲቪ ኸይር ፈላጊ ፣ ነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት ፣ ተአውን እድር ፣ ፍልውሃ ቶፊቅ መስጂድ በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፋቸውን አድርገዋል።

ምንጭ፦ የስልጢ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 16/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Afar

በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 535 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በአፋር ፦
- 800 በቫይረሱ የተያዙ
- 198 ያገገሙ

#Harari

በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 742 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 93 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በሐረሪ ፦
- 789 በቫይረሱ የተያዙ
- 16 ሞት
- 187 ያገገሙ

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 375 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 10 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 5,441 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 325 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የሁለት (2) ሰዎች ህይወት አልፏል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 62 ከምስራቅ ሸዋ
- 56 ከጉጂ
- 46 ከለገጣፎ ከተማ
- 37 ከአዳማ ከተማ
- 27 ከምስራቅ ሀረርጌ
- 12 ከገላን ከተማ
- 10 ከምዕራብ አርሲ ይገኙበታል።

አጠቃላይ በኦሮሚያ ፦
- 4,468 በቫይረሱ የተያዙ
- 41 ሞት
- 1,384 ያገገሙ

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 391 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- 14 ከዳምቤ (አጋሎ) ወረዳ
- 1 ከፓዌ ወረዳ
- 1 ከአሶሳ ከተማ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ39 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,776 የላብራቶሪ ምርመራ 1,368 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ25 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 567 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 39,033 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 662 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 14,480 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(የአማራ ብልፅግና ፓርቲ)

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ "የግድያ ሙከራ ከሸፈ" በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ከሸፈ የተባሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንዲሁም ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንደወትሮው ሁሉ ያለ ምንም ችግር በስራ ላይ ይገኛሉ ሲል ፓርቲው ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምክክር ፓርቲ ፕሬዘዳንት የሆኑት አቶ ሳሳውልህ ከበደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳሳወቁት ዛሬ በነበረው 'በብሄራዊ መግባባት' ላይ ያተኮረ የኢትዮጵያ ፓርቲዎች የውይይት መድረክ ላይ ተሳታፊ አልነበሩም።

አቶ ሳሳውልህ ዛሬው ስለነበረው የብሄራዊ መግባባት የውይይት መድረክ ከሚዲያ እንደሰሙ ተናግረዋል፣ አክለውም ለገዢው ፓርቲ ቅርብ የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የማቅረብ ሌሎችን የመግፋት ሁኔታ እያየን ነው ብለዋል።

የዛሬው የውይይት መድረክ 'ምክክር ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ፓርቲን' የማይወክል መሆኑን ገልፀዋል።

በሌላ መረጃ ፦

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ ዛሬ የሀገራችን ፓርቲዎች በብሔራዊ መግባባት ላይ ውይይት ሊያደርጉ መሆናቸውን ከሚዲያ ከመስማት ባለፈ ለድርጅታችን የቀረበ ጥሪ የለም' ሲል ገልጾ ነበር።

ነገርግን ኢዜአ ከውይይቱ በኃላ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ቀጀላ መርዳሳን አነጋግሯቸዋል። ይህ በፓርቲው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታዩ ክፍተቶች ጋር ተያይዞ የመጣ ሊሆን ይችላል።

ፓርቲው በውስጡ የተከሰተውን ልዩነት ለመፍታት አደራዳሪዎችን ያሳተፈ ዝግ ውይይት ላይ እንደነበር በቅርቡ ETHIO FM 107.8 መዘገቡ ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 16/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,442 የላብራቶሪ ምርመራ 121 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦

- 21 ከምዕ/ጎንደር ዞን
- 18 ከሰ/ወሎ ዞን
- 17 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 16 ከደሴ ከተማ
- 15 ከዋግ ብ/ሰብ ዞን
- 14 ከደ/ወሎ ዞን
- 8 ከባህር ዳር ከተማ ይገኙበታል።

አጠቃላይ በአማራ ፦
- 1772 በቫይረሱ የተያዙ
- 19 ሞት
- 668 ያገገሙ

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 307 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 13 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሱ ከተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።

አጠቃላይ በድሬዳዋ፦
- 794 በቫይረሱ የተያዘ
- 20 ሞት
- 612 ያገገሙ

#Sidama

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 766 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 113 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በቫይረሱ ተያዙት 113 ሰዎች መካከል አንድ መቶ አምስቱ (105) ከሀዋሳ ከተማ ናቸው።

አጠቃላይ በሲዳማ ፦
- 1,017 በቫይረሱ የተያዙ
- 13 ሞት
- 268 ያገገሙ

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ውስጥ በተደረገው 4,428 የላብራቶሪ ምርመራ 607 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። እንዲሁም በ24 ሰዓታት ውስጥ የ18 ሰዎች ሰዎች ህይወት አልፏል። (12 ከአስከሬን ምርመራ 6 ከጤና ተቋም)

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,177 የላብራቶሪ ምርመራ ሃምሳ አንድ (51) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
(የአማራ ብልፅግና ፓርቲ) በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ "የግድያ ሙከራ ከሸፈ" በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ከሸፈ የተባሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንዲሁም ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንደወትሮው ሁሉ ያለ ምንም ችግር በስራ ላይ ይገኛሉ…
#UPDATE

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎ ከሸፏል ይህንን ጉዳይም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙን 'ሚዛን ቴሌቪዥን' ለተባለ ሚዲያ ተናግረዋል እየተባለ ሲናፈስ ነበር።

በኢትዮጵያ ዜና/መረጃዎች እያጣራ ይፋ እያደረገ የሚገኘው 'ኢትዮጵያ ቼክ ፕሮጀክት' አቶ አበረ በስልክ አነጋግሯቸው "ይህ ፍፁም ስህተት የሆነ ወሬ ነው ፣ አሁን ላይ በክልሉ ምንም አይነት የፀጥታ መደፍረስም ሆነ የተባለው አይነት ችግር አልተከሰተም" ብለዋል።

ሚዛን ቴሌቭዥን የተባለ የዩትዩብ ገፅ ላይ በስልክ ገብተው ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ የሚያወሩት እርሳቸው እንደሆኑ ሲጠየቁ "ግዜውን አላስታውስም፣በፍፁም ግን የቅርብ ግዜ አይደለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ክብር ለጤና ባለሞያዎች!

(በዶ/ር ኤልያስ ገብሩ ኣዕምሮ)

ከላይ የምትመለከቱት ፎቶ ጣሊያን፣ብራዚል ወይም አሜሪካ አይደለም የተነሳው። እዚሁ ኢትዮጵያ ያሉ ኮሮናን የሚዋጉ የጤና ባለሙያዎች ናቸው እንዲህ ከወለሉ ላይ ተዘርረው የምታዩት።

"ጽኑ ህሙማን" ክፍል የሚገቡ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር በጣም እየጨመረ ስለመጣ የሥራው ጫና እጅግ እየበዛባቸው ይገኛል። ወንዝ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው እንዲሉ ኮሮናም ባገራችን ቀስ በቀስ ስር ሰዷል።

ቀጣዮቹ ጥቂት ሣምንታት ከፍተኛውን ተጽእኖ የምናይበት ጊዜ ይመስለኛል። ስለዚህ እንደምንም የራሳችንን ፍላጎት ገድበን ጥንቃቄዎችን ማድረግ ያስፈልጋል።

ማስክን ባግባቡ ማድረግ ፣ ርቀት መጠበቅ ፣ አውቶብሶች እና ታክሲዎች ውስጥ መስኮቶችን በመክፈት ማናፈስ ፣ ቢያንስ ለቅሶን መሰል ብዙ ሰው የሚሰበሰብባቸውን ኹነቶች መገደብ ፣ እጆችን በሳሙና መታጠብ፣ ንክኪዎችን መቀነስ ሌሎችም የጥንቃቄ መንገዶች በመተግበር ራስንና ወገንን መጠበቅ ያስፈልጋል።

በተረፈ ለእነዚህ ጀግና ኢትዮጵያዊ ሐኪሞች እና ነርሶች አክብሮታችሁን ለግሷቸው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia