TIKVAH-ETHIOPIA
(የአማራ ብልፅግና ፓርቲ) በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ "የግድያ ሙከራ ከሸፈ" በሚል እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ከሸፈ የተባሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንዲሁም ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንደወትሮው ሁሉ ያለ ምንም ችግር በስራ ላይ ይገኛሉ…
#UPDATE

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎ ከሸፏል ይህንን ጉዳይም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙን 'ሚዛን ቴሌቪዥን' ለተባለ ሚዲያ ተናግረዋል እየተባለ ሲናፈስ ነበር።

በኢትዮጵያ ዜና/መረጃዎች እያጣራ ይፋ እያደረገ የሚገኘው 'ኢትዮጵያ ቼክ ፕሮጀክት' አቶ አበረ በስልክ አነጋግሯቸው "ይህ ፍፁም ስህተት የሆነ ወሬ ነው ፣ አሁን ላይ በክልሉ ምንም አይነት የፀጥታ መደፍረስም ሆነ የተባለው አይነት ችግር አልተከሰተም" ብለዋል።

ሚዛን ቴሌቭዥን የተባለ የዩትዩብ ገፅ ላይ በስልክ ገብተው ተጠርጣሪዎች እንደተያዙ የሚያወሩት እርሳቸው እንደሆኑ ሲጠየቁ "ግዜውን አላስታውስም፣በፍፁም ግን የቅርብ ግዜ አይደለም" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia