TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#KENYA

ከደቂቃዎች በፊት የኬንያ ጤና ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓት 1,115 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተግልጿል። በሀገሪቱ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 262 ደርሷል።

ዛሬ ሪፖርት ከተደረጉት ከአስራ ስድስቱ (16) ኬዞች መካከል አስራ አምስቱ (15) የኬንያ ዜጎች ሲሆኑ አንደኛው የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓት ሰባት (7) ተጨማሪ ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 60 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሞት እንዳንሸምት እንጠንቀቅ!

(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ)

አስቸኳይ አዋጁ ከወዴት አለ ? ወንድሜ ካልሞተ ፣ እህቴ ካልሞተች ፣ አባቴ ካልሞተ ፣ እናቴ ካልሞተች ፣ ሚስቴ ካልሞተች ፣ ባሌ ካልሞተ ፣ ልጄ ካልሞተ ፣ ጓደኛዬ ካልሞተ በስተቀር የኮቪድ19 ወረሽኝ ምን ያህል ገዳይ እንደሆነ ለማወቅ አልቻልንም።

ዛሬም በርካቶች ዓለም በምን ያህል ጭንቀት እና ዜጎች ለህልፈተ ሞት እየበቁ በሚሊዮን የሚቆጠሩም ከቤታቸው እንዲቀመጡ ተደርገው እኛ በከፍተኛ ቸለተኝነት እንገኛለን።

ይህ ምስል በጀርመን አደባባይ እና በቄራ ገበያ በግን ለመግዛት በግን ለመሸጥ የወጡ ናቸው። በስፍራውም የፀጥታ አካላቶች ይገኛሉ እባካቹ ሞትን ለመሸመት አንውጣ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሐመዱ ቡሐሪ የቅርብ ረዳት የነበሩት አባ ኪያሪ በኮሮናቫይረስ ከተያዙ በኋላ መሞታቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

ከፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት የወጣው መግለጫ "የኪያሪ ህልፈትን ለሕዝቡ ሲያሳውቅ በጥልቅ ሐዘን" እንደሆነ ጠቅሷል።

"ኪያሪ በተደረገላቸው ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ ህክምናም ሲከታተሉ መቆየታቸውን" መግለጫው ጨምሮ አመልክቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrDerejeDuguma

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ህክምና ማገገሚያ ሊሆን ነው!

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በዛሬው ዕለት የሆስፒታሉን ዝግጅት በተመለከቱበት ወቅት ነው ሆስፒታሉ ሙሉ ለሙሉ የኮሮና ቫይረስ ህክምና የሚሰጥበት እንዲሆን መመረጡን የተናገሩት፡፡

(የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ገላቭ የሰረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገለፀ!

በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተያዙ ሰዎች ህክምና ከሚያገኙበት ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ግላቭ የስረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የሆስፒታሉ ሁለት የቧንቧ ሰራተኞች ከሌሎች ሁለት (2) ግበረአበሮቻቸው ጋር በመሆን በየካ ክፍለ ከተማ ከሚገኘው ኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል የሰሌዳ ቁጥር A 74615 አ/አ ቶዮታ የቤት መኪና ግምቱ ከ3 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ ግላቭ ሰርቀው በጥበቃ ሰራተኞችና በፖሊስ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ የኮተቤና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኮማንደር በየነ ዱሬሳ ገልፀዋል፡፡

ግለሰቦቹ ወንጀሉን መጋቢት 9 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ እንደፈፀሙ የጣቢያው የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ፀጋዬ ጴጥሮስ ተናገረው ተመሳሳይ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚረዳ ምርመራ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ እንደቀጠለና በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት (4) ግለሰቦች በቁጥጥር ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WezeroLemlemBezabeh

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰቡ ላይ የሚስተዋለው መዘናጋት ለውጥ ካላመጣ ተጨማሪ የእንቅስቃሴ ክልከላዎችንና እገዳዎችን ለማድረግ እንደሚገደድ ገልጿል፡፡

የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ከጅቡቲ ተመላሽ በሆኑና በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ማቆያ በሚገኙ 574 ተመላሾች ላይ በተደረገ የናሙና ምርመራ ሶስቱ (3) ላይ ቫይረሱ ሊገኝ ችሏል ብለዋል፡፡

የበሮ ኃላፊዋ አክለውም ግለሰቦቹ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የሳቢያን ሆስፒታል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑንና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ከነርሱ ጋር ንክኪ እንዳላቸው የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በመለየትም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የፈረንሳይ ሆስፒታል ተገቢውን ክትትል እንዲያገኙ መለየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡ በበሽታው ላይ ያለው #መዘናጋት ከቀን በቀን እየጨመረ ነው ያሉት ወይዘሮ ለምለም የበሽታውን ገዳይነት በመረዳት የተቀመጡ የአካላዊ ርቀት ፤ ንፅህናን ባግባቡ የመጠበቅ እንዲሁም ተያያዠ ህጎችን በማክበር ለራሱም ሆነ ለማህበረሰቡ ጤና ሊጠነቀቅ ይገባል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በጅቡቲ ያለው የቫይረሱ ስርጭት ድሬዳዋን ስጋት ላይ ጥሏታል" - ወይዘሮ ለምለም በዛብህ /የጤና ቢሮ ኃላፊ/

ወይዘሮ ለምለም በዛብህ በአሁኑ ሰአት በጅቡቲ ያለው የቫይረሱ ስርጭት ድሬደዋን ስጋት ላይ እንደጣላት በዛሬው ማግለጫቸው አስታውቀዋል።

ማህበረሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ካላደረገ በርካቶችን በህመም እንዲሁም በሞት ማጣታችን የማይቀር ነው ይህ ከመሆኑ በፊት ግን ሁሉም ሚተላለፉ ህጎችን ማክበርና ማስከበር ይገባዋል ብለዋል።

አሁን የሚያተው መዘናጋት በዚህ ሚቀጥል ከሆነ አስተዳደሩ ማንኛውንም እቅስቃሴዎች ወደማገድ እንቅስቃሴ ይሸጋገራል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ወይዘሮ ለምለም ማህበረሰቡ አዳዲስ ሰዎችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅም ለቁጥጥር ስራው ውጤታማነት የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መላው የክርስትና እምነት ተከታይ የፋሲካ በዓልን ሲያከብር አካለዊ ርቀትን በመጠበቅና በቤቱ ሊሆን ይገባል ያሉት ወ/ሮ ለምለም ለበአሉ አክባሪዎችም መልካም በአልን ተመኝተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ በመቐለና አርባ ምንጭ ከተሞች የአንበጣ መንጋ መልከታቸው የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል። መንጋው እንዳያርፍና ጉዳት እንዳያደርስም በተለያዩ ባህላዊ መንገዶችን ለማባራረር እንደተሞከረም የቤተሰባችን አባላት ገልፀዋል።

ይህን መልዕክት ያቀረብነው ከኮሮና ቫይረስ ጎን ለጎን በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚታየው የአንበጣ መንጋ ጉዳት እንዳይደርስ ትኩረት እንዲሰጠው ለማስታወስ ያህል ነው።

#NACHU #NATY #KIKI
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekelleUniversity

ዛሬ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በመቐለ ከተማ በሚገኙ የበግ ገበያዎች በመገኘት የግንዛቤ መፍጠር ስራ ሰርተዋል።

በቦታዉ ተገኝተው የነበሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አግልግሎት ሃላፊነቱን እየተወጣ ሲሆን አሁንም በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ምላሽ ግን አጥጋቢ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። እንደዚህ አይነት ስራዎችን በቀጣይነት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

አሁንም ድረስ ሰው በባለሙያ ለሚሰጡ ምክሮች ቦታ እንዳልሰጠ ነው። በተፋፈነ ቦታ ሁነው ከሚገበያዩት ውስጥ የፊት መሸፈኛ ማስክ ያደረጉት በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው። አካላዊ መራራቅ የሚባለውም ምንም ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም።

የከተማ አስተዳደሩ ይህን ችግር ለመቅረፍ በከተማው ከ20 በላይ የበግ መገበያያ ቦታዎችን ያዘጋጀ ሲሆን እስካሁን ግን አይደር እና ሽላናት አካባቢ ያሉት ብቻ ናቸው በሰው ተጨናንቀው ያሉት።

በተጨማሪ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት ለፋሲካ በዓል ያስተላልፉትን መልዕክት በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ : https://t.co/VyAlYvQ1o1

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ድጋፎች ሲደረጉ ጥንቃቄ ይደረግ!

(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ)

በበጎ ፍቃደኞችም ሆነ በመንግስት የሚደረገው ድጎማ ቅድመ ጥንቃቄ ሊኖረው ይገባል። በተለይ አረጋውያንን ለመርዳት የሚደረገው እርብርብ የሚበረታታ ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ ከሰው ወደሰው የሚተላለፍበት መንገድ በንክኪ ስለሆነ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

ትላንት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አመራሮች ለደካማ አረጋውያኖች የፋሲካን በዓል ምክንያት በማድረግ ዱቄት ሲያድሉ የነበረው ግፊያ እና ንክኪ ለበሽታው ተጋላጭ ስለሚያደርግ ሌሎች ቦታ ላይ ጥንቃቄ ቢወሰድ መልካም ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬን መጠንቀቅ ለነገ ጤናችን መሰረት ነው!

(በጋዜጠኛ ኤልሳ አሰፋ)

ጤና ይስጥልኝ የሀገሬ ልጆች የኮቪድ ወረርሽኝ አለም ላይ ተቀጣጥሎ ወላፈኑ ይለበልበን ጀምሯል።

ብዙዎቻችን ግን እምብዛም አልሞቀን፣ የእሳቱ ግርፋትም የሚደርስብንም አልመሰለን። እሳትን ለመፍራት፣ ለመጠንቀቅ ፣መቃጠልን እየጠበቅን ነው።

ጭራሽ ማገዶ ለመሆን እራሳችንን፣ ቤተሰባችንን ልንማግድ የተነሳን ይመስላል። በየገበያው ስፍራ ያለው ትርምስ ይህን ያረጋግጣል።

ዛሬን መጠንቀቅ ለነገ ጤናችን መሰረት ነው። እርቀታችንን እንጠብቅ፤ እጃችንን በአግባቡ እንታጠብ፥ ለእራሳችንና ለሌሎች ሀላፊነትን እንወጣ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኃይል መቋረጥ ችግር፤ 905 አማሮናል!

በበዓል መብራት ጠፍቶብን ውለናል አሁንም እንደጠፋ ነው የሚሉ መልዕክቶች ከአዲስ አበባ ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም ከአሰላ ከተማ መልዕክቶች መጥተዋል።

ይህን የቤተሰቦቻችን መልዕክት ለማስቀመጥ የወደድነው በርካታ የቲክቫህ አባላት በ905 በኩል ቅሬታና ጥቆማ ለመስጠት በተደጋጋሚ ቢደውሉም አገልግሎት ማግኘት እየቻሉ እንዳልሆነ እገለፁ በመሆኑ ነው።

ትናንት ለሊት በአዲስ አበባ ጀሞ አካባቢ በጋራ መኖሪያ ቤት ግቢ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች በትረንስፎርመር ለይ ኮንታትክት ተፈጥሮ በ905 ላይ ጥቆማ ለመስጠት ረጅም ሰዓት ስልክ ቢሞክሩም እንዳልተሳካና ችግሩ ከነጋ በኃላ እንደተፈታ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- አርጀንቲና ግዙፉን የኢግዚቢሽን ማዕከል ወደ ኮቪድ-19 የህክምና ማዕከል ቀይራለች። እስከ 2ሺህ 5መቶ የሚጠጉ የኮቪድ 19 ታማሚዎችን ለማከም እንዲውልና ማዕከሉ በሆስፒታሎች የሚኖረውን ጫና ለማገዝ እንደሚረዳ ተገልጿል #VOA

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት 888 ሰዎች ሞተዋል። ቁጥሩ ባለፉት 7 ቀናት ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው። በሌላ በኩል 5,526 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 114,217 ደርሷል።

- በጃፓን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 10,000 ደርሷል።

- በአውሮፓ ብቻ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,000,000 ደርሷል።

- ደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 18 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች። ዘጠኙ ከውጭ የገቡ ናቸው። በደቡብ ኮሪያ ከFebruary በኃላ የተመዘገበ ዝቅተኛው ኬዝ ነው።

- በቻይና 27 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። አስራ ሰባቱ (17) ከውጭ ሀገር የገቡ ናቸው።

- በጣልያን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እንዲሁም የሟቾች ቁጥር መቀነስ አሳይቷል። ባለፉት 24 ሰዓት 482 ሰዎች ሲሞቱ 3,491 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት 585 ሞተዋል።

- ጅስቲን ትሩዶ የካናዳ እና የአሜሪካ ድንበር ተዘግቶ እንደሚቆይ ተናግረዋል። ድንበሩ ተዘግቶ እንዲቆይ ሁለቱም ሀገራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተሰምቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

- የነቀምቴ ከተማ ወጣቶች ባለፉት ቀናት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሊቸገሩ ለሚችሉ ወገኖች እገዛ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰሩ እንደነበር አሳውቀውናል።

- በይርጋዓለም ከተማ የሆስፒታል ሰፈር ወጣቶች 'እኛ ለእኛ' በሚል ስያሜ በተቋቋመው ማህበር ከማህበሩ አባላትና ከአንዳንድ በጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ እህል እና የፅዳት መጠበቂያ ሳሙናዎችን ለአቅመ ለሌላቸው ወገኖች የመጀመሪያ ዙር እርዳታ ማድረጋቸውን አሳውቀውናል።

- የዲላ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር/ Dilla Town Health Sport Association ማዕዳቸውን አጋርተዋል። ዲላ ከተማ ጤና ስፖርት ማህበር በየወሩ ከሚያግዛቸው ስዎች በተጨማሪ የኮረና ወረርሽኝ መግባቱ ከታወቀ በኃላ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው በድጋሚ ሁለተኛ ዙር 35 እረዳት የሌላቸውን እናትና አባቶች ድጋፍ አድርገዋል።

PHOTO : (1-ይርጋለም) (2 - ዲላ) (3- ነቀምቴ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia