TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሁቤይ ግዛት ከውሃን ቀጥላ በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ የተጎዳችው #Xiaogan ከተማ ሰዎች ወደቀደመው ህይወታቸው እየተመልሱ ነው።

#BackToWork
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በውሃን ከተማ የዴሊቨሪ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ወደ መደበኛ ስራቸው እየተመለሱ ነው። ባለፉት ሶስት ቀናት የትዕዛዝ ቁጥሮች መጨመራቸው የተነገረ ሲሆን እሁድ ብቻ 1 ሚሊዮን ትዕዛዞች ለደንበኞች ደርሰዋል። ምግብ፣ ማስክ እንዲሁም አልባሳት በብዛት በኦንላይ ከታዘዙት ውስጥ ይገኙበታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በውሃን እየተደረገ የሚገኘው ዝግጅት!

APRIL 8 በውሃን የተጣለው ያለመንቀሳቀስ ገደብ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል። ከተማይቱ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትችን ወደስራ ለማስገባት እያዘጋጀች ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ከዱባይ የመጡ ኢትዮጵያውያንን መቀበሉን ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ በአስተዳደሩ ወደተዘጋጀላቸው ከውጭ የሚገቡ ሰዎች ለሁለት ሳምንታት የሚቆዩበት ስፍራ እንደሚገቡም አስታውቀዋል፡፡

አስተዳደሩ በብዙ ርብርብ ከውጭ የሚገቡ ሰዎች ለሁለት ሳምንታት የሚቆዩበት ቦታ ማዘጋጀቱን ከከንቲባ ጽህፈት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮሮና ቫይረስ የተያዘ 1 ተጨማሪ ሰው መገኘቱ ተገለፀ!

መጋቢት 3/2012 ዓ.ም የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በሀገራችን ከተገኘ ወዲህ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ (1) ተጨማሪ ሰው በመገኘቱ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል።

ታማሚው የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከዱባይ ወደ ሀገር ውስጥ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም የገባ ነው።

ግለሰቡ የሕመም ምልክት የነበረው በመሆኑ በመጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄደ ሲሆን ተቋሙም ለኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖረት በማደረግ በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ሲሆን ጤንነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ግንኙነት የነበራቸው 15 ሰዎች በክትትል ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

- በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ተጨማሪ ሰው በመገኘቱ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 12 ደርሰዋል።

- ይህ ታማሚ የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ነው፤ መጋቢት 10 ነው ከዱባይ ወደ ኢትዮጵያ የገባው።

- ግለሰቡ የህመም ምልክት ያሳየው መጋቢት 13/2012 ዓ/ም ነው። በተደረገለት ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጣል።

- ከታማሚው ጋር ግንኙነት የነበራቸው 15 ሰዎች በክትትል ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መስፋፋትን ለመግታት ያስችላል ያሉትን የዜጎችን አኗኗር የሚቀይሩ ጥብቅ እርምጃዎች ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ የተከለከሉ ሲሆን ፤ መውጣት የሚቻለው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ፣ “የግድ አስፈላጊ” ለሆኑ ሥራዎችና ጉዞዎች ፣ መሰረታዊ ነገሮችን ለመግዛትና የህክምና ክትትልና ድጋፍ ለማግኘት ብቻ ይሆናል።

መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን የሚሸጡ መደብሮች እንዲዘጉ የተነገራቸው ሲሆን አብረው ከሚኖሩ ሰዎች ውጪ በሕዝብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች ከሁለት በላይ ሆኖ መገኘትም ተከልክሏል።

ዜጎች በመንግሥት የወጣውን ግዴታ ተግባራዊ የማያደርጉ ከሆነ የመቅጣትና የተሰበሰቡ ሰዎችን የመበትን ስልጣን ፖሊስ ተሰጥቶታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን ከጽህፈት ቤታቸው በቴሌቪዥን ቀርበው አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 1,872 ደርሷል። 50 ሰዎችም በቫይረሱ መሞታቸውን #TheStar ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የማህበራዊ ርቀት አሁንም በሚፈለገው መልኩ ተግራባራዊ እየተደረገ አይመስልም። ይህ ፎቶ ዛሬ ጥዋት ቦሌ ክፍለ ከተማ መሬት ማኔጅመት ፅ/ቤት የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው። እኚህ ትንሽ የሚመስሉ ችግሮች ነገ ዋጋ ማስከፈላቸው አይቀርም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጣልያን በቅድሚያ በሀገሯ የተመዘገበው የኮሮና ቫይረስ ኬዝ 2 ብቻ ነበር። በወቅቱ ማንም ዛሬ ያሉበት ሁኔታ ላይ ይደርሳሉ ብሎ የገመተ የለም። የጤና ባለሞያዎችን ምክር ፈጥነው ባለመቀበላቸው ባለመተግበራቸው ይኸው ዛሬ ዋጋ እየከፈሉ ነው።

ማህበራዊ ርቅተን መተግበር አልችልም፣ ከመጨባበጥ፤ ከመሰባሰብ አልቆጠብም የሚል ግለሰብ ካለ ለእራሱ ለአንድ ህይወቱ ሲል ቤቱ ቢቀመጥ የተሻለ ነው። ኮሮና ቫይረስ መድሃኒት የለውም፤ ልናደርግ የምንችለው የጤና ባለሞያዎችን ማዳመጥ ብቻ ነው።

አትፍሩ ማለት አትጠንቀቁ ማለት አይደለም!
ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መስሪያ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመከላከል ከተቋማቸው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር መፍትሔዎችን መውሰድ እንደሚገባቸው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አሳሰበ።

ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ እንደገለጹት ሰራተኞች በጤና ሚኒስቴርና በሌሎች አካላት የሚተላለፉ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸዋል።

ተቋማት የሰራተኞቻቸውን ጤና በመጠበቅና በቢሮ ውስጥ የሚኖሩ መጨናነቆችን በመቀነስ ረገድ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኪዱ ቬንቸር ኃሳብ ላላቸው ጥሪ አስተላልፏል!

ኩዱ ቬንቸር ለቲክቫህ በላከው መልዕክት ከዚህ ቀደም ለሥራ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሶ አሁን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እንደ ሀገር የሁሉም አካላት ቅንጅት እንደሚያስፈልግ ስለተረዳ የበኩሉን ሀገራዊ ግዴታ ለመወጣት ያሉትን አቅሞች አስተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህንን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያግዝና ዜጎችን በችግር ግዜ የሚረዳ ማንኛውም የፈጠራ ኃሳብ ያላቸውን የፈጠራ ባለቤቶች ኩዱ ቬንቸር አብሮ ለመስራትና ለማገዝ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በመሆኑም ወረርሽኙን ለመከላከል ይጠቅማል የሚል ኃሳብ ያላችሁ የፈጠራ ሥራ ባለቤቶችም ሆነ ድርጅቶች በሚከተለው ሊንክ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

https://forms.gle/E7gAqJrRoXZFTtHT6

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የግብፁ ፕሬዝደንት አብደልፈታህ አል-ሲሲ እና ቤተሰባቸው ለሁለት ሳምንት በኳረንቲን እንደቆዩ Middle East Eye ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ ፕሬዝደንቱ በኳረንቲን እንዲቆዩ ተደርገው የነበረው ሰኞ በኮሮና ቫይረስ ህይወቱ እንዳለፈ ከተነገረው አንድ ከፍተኛ የግብፅ ወታደራዊ አባል ጋር ግንኙነት ስለነበራቸው ነው።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የአዲስ ከተማ መለስተኛ መናኸሪያ አገልግሎት ወደሌሎች መናኸሪያዎች እንዲዛወር ተደርጓል፦

የሆሳዕና ፣ ቡታጅራ ፣ ቱሉቦሎ ፣ ወሊሶ ፣ ወልቂጤና ሰባት ቤት ጉራጌ ሥምሪቶች በአየር ጤና መናኸሪያ የሚሰጡ ይሆናል። የአዳማ እና ቢሾፍቱ ሥምሪቶች ደግሞ በላምበረት እና በቃሊቲ መናኸሪያዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተዛውረው አገልግሎት የሚሰጡ ይሆናል።

የትራንስፖርት ባለሥልጣን ይህን ያደረገው የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት፤ የሰዎች ጥግግትን በመቀነስ ማኅበራዊ ርቀትን ለማስጠበቅ ነው።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየደረሰባት ላለው የኢኮኖሚ ቀውስ ማቅለያ 150 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ኢትዮጵያ ለቡድን 20 አባል ሀገራት ጥሪ አቅርበች። ኢትዮጵያ ላለባት ብድር የወለድ ስረዛ እንዲደረግላትም አባል አገራቱን ጠይቃለች፡፡

#ShegerFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia