ኪዱ ቬንቸር ኃሳብ ላላቸው ጥሪ አስተላልፏል!

ኩዱ ቬንቸር ለቲክቫህ በላከው መልዕክት ከዚህ ቀደም ለሥራ ፈጣሪዎች ከፍተኛ ገንዘብ መድቦ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሶ አሁን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እንደ ሀገር የሁሉም አካላት ቅንጅት እንደሚያስፈልግ ስለተረዳ የበኩሉን ሀገራዊ ግዴታ ለመወጣት ያሉትን አቅሞች አስተባብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህንን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚያግዝና ዜጎችን በችግር ግዜ የሚረዳ ማንኛውም የፈጠራ ኃሳብ ያላቸውን የፈጠራ ባለቤቶች ኩዱ ቬንቸር አብሮ ለመስራትና ለማገዝ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በመሆኑም ወረርሽኙን ለመከላከል ይጠቅማል የሚል ኃሳብ ያላችሁ የፈጠራ ሥራ ባለቤቶችም ሆነ ድርጅቶች በሚከተለው ሊንክ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

https://forms.gle/E7gAqJrRoXZFTtHT6

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia