መስሪያ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመከላከል ከተቋማቸው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር መፍትሔዎችን መውሰድ እንደሚገባቸው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አሳሰበ።

ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ እንደገለጹት ሰራተኞች በጤና ሚኒስቴርና በሌሎች አካላት የሚተላለፉ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸዋል።

ተቋማት የሰራተኞቻቸውን ጤና በመጠበቅና በቢሮ ውስጥ የሚኖሩ መጨናነቆችን በመቀነስ ረገድ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia