TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ትግራይ ክልልን በኢኮኖሚና ልማት አሻጥር ለማዳከም እየተሰራ ነው?

የበጀት ቀመርን የሚያወጣውና የሚደለድለው የፌዴራል መንግስት ሳይሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በዛሬው ውይይት ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻር ትግራይ በተያዘው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ለቀጥተኛ በጀት፤ 400 ሚሊዮን ብር ደግሞ ለዘላቂ የልማት ግቦች የሚውል በጀት ተመድቦለታል ብለዋል። የተመደበው በጀት በፌዴራል መንግስት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን እንደማያካትት ተናግረዋል።

ለትግራይ ክልል በዘንድሮው ዓመት የተያዘው በጀት ከዚህ ቀደም ከነበሩት በእጅጉ እንደሚበልጥ ጠቅሰዋል።

የትግራይ ክልል ምክር ቤት በጀቱ ለተያዘለት ዓላማ ብቻ እንዲውል መቆጣጠር እንደሚገባውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አውስተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

አሜሪካ እና ዐለም ባንክ ኢትዮጵያ ከአባይ ወንዝ በዐመት 37 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እንድትለቅ የሚጠይቅ አስታራቂ ሃሳብ እንዳቀረቡ የግብጹ ማዳማስር ጋዜጣ አስነብቧል፡፡ ረቂቁ የስምምነት ሰነድ ትናንት ለ3 ሀገራት እንደተላከላቸው ተገምቷል፡፡ በ3 ቀናት ምላሽ ይሰጡበታል፡፡

ኢትዮጵያ 31 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ እለቃለሁ ስትል፣ ግብጽ 40 ቢሊዮን ላይ ጸንታለች፡፡ ግብጽ ግድቡ እና ናስር ሐይቅ ሁሌም የውሃ መጠናቸው እንዲጣጣም እና ግድቡ የሚያመነጨው ሃይል መረጃ በየጊዜው እንዲሰጣት ሃሳብ አቅርባ ኢትዮጵያ አልቀበለችውም፡፡

[ማዳማስር ጋዜጣ፣ ዋዜማ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ የሚገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ ዛሬ አ/አ በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት፦

"የመግባቢያ ነጥቦች እየተጠናቀቁ ወደ ስምምነት ተቃርቧል። አሁንም ግን የሚቀር ሥራ አለ። የሦስቱ አገራት መሪዎችም ሆኑ አሜሪካ፤ የሁሉንም አገራት ፍላጎት ያማከል ስምምነት እንዲደረስ ነው ጥረት ሲደረግ የቆየው። ብዙ ሥራ ይቀረናል፤ በቀጣዩ ወር ግን እንደሚጠናቀቅ ተስፋ አደርጋለሁ።"

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11

45ኛው ዓመት ህወሓት የተመሰረተበት የየካቲት 11 በዓል የተለያዩ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊስት ኃይሎች፣ የፌደራልና የክልል መንግስት አመራሮች፣ ነባር ታጋዮች እና ምራሁራን በተገኙበት የፓናል ውይይት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በሌላ መረጃ፦

45 ተኛው ዓመት የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግል የጀመረበት የካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ ከጎረቤት ሀገር ሱዳን የመጡ እንግዶች ጋር የፓነል ዉይይት ተካሂዷል፡፡

#ትግራይቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ተፈታኞች ኦንላይን ይመዘገባሉ!

ዘንድሮ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የኦንላይን [online] ምዝገባ ስርአት በመላው አገሪቱ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ እንዳሉት በ2010 እና 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በሙከራ ደረጃ ተወስኖ የነበረው የኦንላይን ምዝገባ ስርአት በመላው አገሪቱ ባሉ የፈተና ጣብያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል።

የኦንላይን [online] ምዝገባው ካሁን በፊት ከእንግሊዝ ሲመጣ የነበረውን የምዝገባም ሆነ የመልስ መስጫ ወረቀት እንደሚተካ ገልፀዋል።

ይህንንም ከሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር በትምህርት ቤቶቹ ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱ ጠቁመዋል፡፡

አንዳንድ የግብአትም ሆነ የአቅም ማነስ የሚያጋጥማቸው ጣብያዎች ካሉም በነባሩ አሰራር በወረቀት የመመዝገብ ሂደት ሊተገበር እንደሚችልም ከክልሎች ጋር መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

የኦን ላይን [online] ምዝገባውን በትክክል ለማስኬድም ባለፈው ወር ለክልል የፈተና ጉዳይ አስፈፃሚና ለአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመቐለ ትግራይ ስታዲየም በመከበር ላይ ይገኛል። ማለዳ ላይ በዓሉን በማስመልከት በሰማዕታት ሀውልት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ነባር ታጋዮች የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

በአሁኑ ሰዓት የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በትግራይ ስታዲየም እየተከበረ ሲሆን፥ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ነባር ታጋዮች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

#TIGRAYCOMMUNICATION #FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከስልጤ ዞን ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመወያየት ወራቤ ገብተዋል፡፡

ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ውይይቱ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ትኩረት ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#PMOEthiopia #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኋላ ሁለት እግር የሌለው ጥጃ ተወለደ!

በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ጺዮን ሰጓጅ ቀበሌ ክስተቱ የታየው ንብረትነቷ የአቶ አበበ ጌጡ በሆነች ላም ላይ ሲሆን ጥጃው የኋላ ሁለት እግር የሌለው ጎደሎ ሆኖ የተወለደ ሲሆን አቶ አበበም ላሟ ከሁለት ሳምንት በፊት የመቅበጥበጥና የመደበት ስሜት ያዩባትና ስትወልድም በመቸገሯ ምክኒያት እርዳታ አድረገውላት መውለዷን ጠቁመው ጠንካራና የአንድ ወር እድሜ ያለው የሚመስለው ጥጃ በእንዲህ ያለ ሁኔታ በመወለዱ ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡-Gondar zuria communication
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መኪናችን ተይዞብናል...

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ኮድ 2 ቫን መኪናዎች እየተያዙ እንደሆኑ ተሰምቷል። መኪናቸው ለተያዘባቸው የቤተሰባችን አባላት መካከል ተከታዩን መልዕክት አጋርተዋል፦

"የጉሙሩክ ሰራተኞች አ/አ መካኒሳ ኮሬ አካባቢ ቫኖችን በማስቆም በተሳሳተ ሰነድ የገባ መኪና እንዳለና የኛም መኪና መጣራት እንዳለበት አሳውቀውን ወደ ጉምሩክ 10 የሚሆኑ ቫኖችን ይዘው ሄደዋል። ሆኖም ጉምሩክ ግቢ ውስጥ ከገባን በኃላ መኪናችን እንደማይለቀቅ እና ቫን በኮድ 2 መንዳት እንደማይቻል እና ተጨማሪ ታክስ መክፈል እንዳለብን ነግረውን መኪናችንን ቀምተው መልሰውናል። ታርጋውን የሰጠን መንግስት፣ መኪናውን የሸጠልን የመኪና አስመጪ፤ እኛ በምን ጥፋታችን ነው 700,000 እና ከዛ በላይ አውጥተን የገዛነው መኪና ድጋሚ 700,000 ብር ታክስ ክፈሉ የምንባለው?"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከአዲስ አበባ...

እጅግ በርካታ የቤተሰባችን አባላት በኮድ 2 ማሽከርከር አትችሉም በሚል መኪናቸው እንደተያዠባቸው የሚገልፁ መልዕክቶችን እያደረሱን ይገኛሉ። አንዳንድ የቤተሰባችን አባላት ይህን ጉዳይ በመስማታቸው ዛሬ መኪና ይዘው እንዳልወጡ ገልፀውልናል። በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጪ ካለ ምላሹን እንድታነቡት እናደርጋለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መንግስት ንብረታችንን እየነጠቀን ነው...

መኪና የተነጠቀባቸው የቤተሰባችን አባላት፦

"መንግስት የህዝብ ንብረት መንጠቅ ተያይዞታል። ኮድ 2 ኦሮ VAN መኪኖች የሰጠን ኦሮሚያ መንገድ ትራንስፖርት ስህተት ካለበት የሰጠ አካል ነው መጠየቅ ያለበት ህዝብ ያለጥፋቱ እየተገላታ ነው። ኮድ 2 ኦሮ van መኪኖች እየቀሙ ቃሊቲ ግምሩክ መጋዘን እያስቀምጡ ነው እነሱ የሚሉት ኮድ 3 መሆን ነበረባቸው፤ ኮድ 2 የማይፈቀድ ከሆነ መጠየቅ ያለበት የሰጠ አካል የኦሮሚያ መንገድ ትራንስፖርት ነው የአንድ ሀገር ህግ እስከሆነ በመሀል ህዝብ እየተሰቃየ ነው። ኮድ 3 A.A ያላወጣነው የአ.አ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት አላስተናግዳችሁም በማለቱ ነው እንጂ በወቅቱ ጠይቀን ነበር፤ እና ለዚህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መለሰ መሰጠት ያለበት የአ.አ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ነው"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የራይድ አሽከርካሪ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፦

የራይድ አሽከርካሪዎች የሆኑ የቤተሰባችን አባላት ህጋዊ ሆነን እየሰራን በየአካባቢው እየተደበደብን ነው ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል። በአሁን ሰዓት የራይድ አሽከርካሪ 'ተደብድቦ' የረር አለማየሁ ህንፃ ጋር በርካታ የራይድ አሽከርካሪ ተሰብስቦ ፖሊስና የሚዲያ ሰዎችን እየጠበቀ እንደሆነ ገልፀውልናል ። ህጋዊ ስራ እየሰራን መደብደብ የለብንም፣ ንብረታችን መኪናችንም መሰባበር የለበትም፣ በነፃነት መስራት አልቻልንም፣ ወከባ ይደርስብናል መንግስት ካለ ህግ ያስከብር ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia