የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ተፈታኞች ኦንላይን ይመዘገባሉ!

ዘንድሮ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የኦንላይን [online] ምዝገባ ስርአት በመላው አገሪቱ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ እንዳሉት በ2010 እና 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በሙከራ ደረጃ ተወስኖ የነበረው የኦንላይን ምዝገባ ስርአት በመላው አገሪቱ ባሉ የፈተና ጣብያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል።

የኦንላይን [online] ምዝገባው ካሁን በፊት ከእንግሊዝ ሲመጣ የነበረውን የምዝገባም ሆነ የመልስ መስጫ ወረቀት እንደሚተካ ገልፀዋል።

ይህንንም ከሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር በትምህርት ቤቶቹ ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱ ጠቁመዋል፡፡

አንዳንድ የግብአትም ሆነ የአቅም ማነስ የሚያጋጥማቸው ጣብያዎች ካሉም በነባሩ አሰራር በወረቀት የመመዝገብ ሂደት ሊተገበር እንደሚችልም ከክልሎች ጋር መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

የኦን ላይን [online] ምዝገባውን በትክክል ለማስኬድም ባለፈው ወር ለክልል የፈተና ጉዳይ አስፈፃሚና ለአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia