TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Election2012

ኦፌኮ በጪሮ...

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በጪሮ ከተማ ከደጋፊዎቹ ጋር ተገናኝቷል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው የከተማው ነዋሪ ለኦፌኮ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርጓል። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ጃዋር መሃመድ ጪሮ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የታገቱት 17 ተማሪዎች...

17 የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጸጥታ ስጋት ወደ ትውልቅ ቀያቸው ሲያመሩ በታጣቂዎች ከታገቱ ሳምታት ተቆጠሩ። በታጣቂዎች ታግተው ከሚገኙት 17ቱ የደንቢ ዶሎ ዩኒበርሲቲ ተማሪዎች መካከል 13ቱ ሴት ተማሪዎች መሆናቸውን ከአጋቾቹ ካመለጠች ተማሪ ማወቅ ተችሏል።

More : https://telegra.ph/BBC-01-11

#BBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiBot
የአጋቾቹ ፍላጎት ምንድነው?

ወንድሟ የታገተባት እህት ከወንድሟ ባገኘችው መረጃ መሠረት አጋቾቹ ገንዘብ አይፈልጉም። ከአጋቾቹ እጅ ያመለጠችው አስምራ እንደምትናገረው፤ አጋቾቹ በተደጋጋሚ "ከእናንት ጋር ጸብ የለንም። ጸባችን ከመንግሥት ጋር ነው" እንደሚሉ ትናገራለች። አጋቾቹ "የአማራ ህዝብ ልጆቻችን ታግተዋል ብሎ ሰልፍ ሲወጣ፤ መንግሥት እኛን ያነጋግራል። የዛኔ እኛ ጥያቄያችንን ለመንግሥት እናቀርባለን፤ ጥያቄያችንም ይመሳል" እንዳሉ አስምራ ትናገራለች።

#BBC

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
የመንግሥት አካላት ምላሽ ስለታገቱት ተማሪዎች...

ከኦሮሚያ ክልል፦

የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ "ምንም አይነት መረጃ የለኝም። እኔ የሰማሁት ነገር የለም" ይላሉ።

ጉዳዩ እርሳቸው የሚመሩት ቢሮን በቀጥታ የሚመለከት መሆኑን በመጥቀስ ስለጉዳይ እንዴት መረጃ ሳይኖራቸው እንደቀረ ከቢቢሲ የተጠየቁት ኮሎኔል ገረሱ፤ "እኔ ምንም አልሰማሁም ነው የምልህ። ለምድነው የምትጠይቀኝ?" በማለት መልሰዋል። የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በበኩላቸው ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎች የሉም ብለዋል። ኃላፊው ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ የለም ከማለት ውጪ ማብራሪ መስጠት አልሰጡም።

የአማራ ክልል፦

ቢቢሲ የደወለላቸው የአማራ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር፤ "አሁን ማውራት የማልችልበት ቦታ ነው ያለሁት" በማለት የእጅ ስልካቸውን ዘግተውታል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከአምስት ቀናት በፊት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ "አራት ተማሪዎች ታግተው እንደሚገኙ መረጃው አለኝ" ማለታቸው ይታወሳል። ታግተው የሚገኙት ተማሪዎች በወላጆቻቸው ጋር በስልክ አልፎ አልፎ እንደሚገናኙ ጭምር ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ ተማሪዎቹ ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ከአባ ገዳዎች፣ ከአከባቢው ማህብረሰብ እና ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር ውይይት እያደረግን ነው ብለዋል።

#BBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የጋሞ ብሄረሰብ ባህላዊ እሴቶች...

በጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ ዕሴቶች ዙሪያ በአዲስ አበባ ፅሑፍ ቀርቦ ዉይይት እየተካሄደ ነዉ። የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘዉዴ እየተካሄደ በሚገኘዉ የቋንቋ እና ባህል ዉይይት ላይ የጋሞ አባቶችን እና ወጣቶችን የሠላም ተምሳሌትትን አዉስተዉ በጋራ ለመኖር የአባቶቻችን ባህል ስንቃችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የምግብ ዋጋ ግሽበት...

አዲስ ማለዳ የተሰኘው ሳምንታዊ ጋዜጣ ዛሬ ይዞት በወጣው እትሙ የትግራይ ክልል የምግብ ዋጋ ግሽበት 23 በመቶ መድረሱን ዘግቧል። ግሽበቱ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የአስር በመቶ ጭማሪ አሳይቷልም ብሏል።

- የትግራይ ክልል የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር እስከ አስር በመቶ የሚደርስ ጭማሪ ማስመዝገቡን የብሄራዊ ባንክ ዓመታዊ ዘገባ አመላክቷል።

- ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ግብኣቶች ላይ በክልሉ የተስተዋለው የግሽበት መጠን በ2011 ከነበረበት የአስር በመቶ ጭማሪ በማድረግ አሁን 23 ከመቶ ላይ እንደሚገኝ የባንኩ ዓመታዊ ዘገባ ያስረዳል።

- አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ በትግራይ ክልል ባለፈው ዓመት 13.9 በመቶ ላይ የነበር ሲሆን አሁን 19.8 በመቶ ላይ ደርሷል።

- ምግብን ጨምሮ አልኮል አልባ መጠጦች ላይ የዋጋ ግሽበት በድሬዳዋ፣ ሶማሌ፣ ጋምቤላ ክልሎች ከፍ ብሎ የተስተዋለ ሲሆን የክልሎች አማካኝ የግሽበት መጠን 11.2 በመቶ ላይ እንደደረሰ ታውቋል።

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
ኮለኔል ሮዳሞ ኪአ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ትላንት ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተወሰደ፦

- በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የዶርም አባሉን ህይወት ያጠፋው ተማሪ በቁጥጥር ስር ውሏል።

- ድርጊቱ በቀን 30/4/2012 ዓ.ም ምሽት 4 ሰዓት አካባቢ የተፈፀመ ነው።

- በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በሆኑ ሁለት ግለሰቦች መካከል በግል ፀብ በተፈጠረው በዚህ ግጭት የአንደኛ ዓመት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነው ግለሰብ ህይወት በስለት ተወግቶ አልፏል፡፡

- ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ እና በድርጊቱ የተሳተፉ አካላት በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው በተደረገው ምርመራ እና ማጣራት ወንጀሉ የተፈፀመው በሟች እና በገዳዩ መካከል በነበረ የቆየ ግጭት ምክንያት በተያዘ ቂም ነው።

- በአሁን ሰዓት ከሁሉም የፀጥታ ሀይል የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት በሁሉም ካምፓሶች ተቋቁሟል። አስተማማኝ የፀጥታ ሁኔታ ነው ያለው።

- ግጭቱ በግል ቂም በተፈጠረ ፀብ የተፈፀመ መሆኑ በምርመራ የተረጋገጠ ቢሆንም በማህበራዊ ሚዲያዎች የሁለቱን ተማሪዎች ግጭት የብሔር ካባ በማልበስ የሀሰት መረጃ የሚያሰራጩ አካላት አሉ። እነዚህ ኃላፊነት የጎደላቸው በጥቅም የታወሩ አካላት የሚያሰራጩት የሀሰት መረጃ ከእውነት የራቀ ሚዛናዊነት የጎደለው መሆኑን መላው ህብረተሰብ ሊገነዘበው ይገባል።

- የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስም ለሟች ቤተሰቦች ፣ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

(የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የሴራ በዓል...

በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘውን የሀላባ ብሔር የዘመን መለወጫ ሴራ በአልን ምክንያት በማድረግ 40 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ የተሳተፈበት የሩጫ ውድድር በቁሊቶ ከተማ ተካሄደ። ፋን ኢትዮጵያ ከሀላባ ዞን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚሁ የሩጫ ውድድር ላይ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ሂኪማ ካይሬዲን፣ የሀላባ ዞን አስተዳደሪ ዶክተር መሐመድ ኑሪዬና የፋን ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ አትሌት ፋንቱ ሚጌሶ ተገኝተዋል።

(SRTA, PHOTO: TIKVAH)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#CONGRATULATIONS

#MEKELLE #HARAMAYA

- በሃረማያ ዩኒቨርሲቲ የሐረር የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ያሰለጥናቸውን 239 የህክምና ዶክተሮች ዛሬ አስመርቋል፡፡ ኮሌጁ ለ7ኛ ዙር ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂዎቹ 56ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሃረሪ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋና ሌሎች የክልልና የፌዴራል የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተው ነበር።

- በመቐለ ዩንቨርስቲ የአይደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ11ኛ ጊዜ 390 የህክምና ዶክተሮችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል በጥርስ የህክምና ሙያ የተማሩ ይገኙበታል። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የፌዴራል የጤና ጥበቃ እና የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

(EBC)
@tikvahethmagazine
የዓለም ባንክ...

የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት በ2020 ያድጋል ብሎ ያስቀመጠው ትንበያ ላይ ማስተካከያ አደረገ፡፡ ባንኩ ባለፈው ሰኔ ያወጣው ትንበያ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት በ2020 በ7 ነጥብ 1 በመቶ ያድጋል ብሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ባንኩ በትንበያው ላይ የ1 ነጥብ 9 በመቶ ማስተካከያ በማድረግ እድገቱ በ6 ነጥብ 3 በመቶ ብቻ እንደሚሆን ገልጿል፡፡ በአገሪቱ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የወጪ ንግድ አፈፃፀም ደካማ መሆን እና የኑሮ ውድነት መጨመር ባንኩ በእድገት ትንበያው ላይ ማስተካከያ እንዲያደርግ ያስገደዱ ምክንያቶች ናቸው፡፡

(AHADU TELEVISION)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ...

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራን ለማስቀጠል የሚያግዝ ህዝባዊ የሰላም ኮንፈረንስ ተጀመረ። በኮንፈረንሱ ከምዕራብ ፣ ምስራቅ እና ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች የተውጣጡ አባገዳዎች የኃይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ነው። በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ እዝ ጠቅላይ መምሪያ የተለያዩ ክፍል አዛዥች፣ ሲቪል የመንግስት ስራ ኃላፊዎችና ሌሎችም የህብረተስ ክፍሎች በኮንፍረንሱ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

#ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አይካ አዲስ አሁንም ደሞዝ እየከፈለ ነው...

ዓለም ገና ከተማ የሚገኘው አይካ አዲስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ በእዳ ምክንያት ከተዘጋ 4 ወራትን ቢያስቆጥርም አሁንም ከ 4 ሺ 5 መቶ ለሚልቁ ሰራተኞቹ ደሞዝ እየከፈለ ነው ተብሏል። ድርጅቱ በተጠቀሱት ወራት ውስጥ 40 ሚሊዮን ብር ለሰራተኞቹ መክፈሉንም ነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ የባንኩን እንቅስቃሴ አስመልክቶ የመስክ ምልከታ ላደረጉት የተወካዮች ምክር ቤት አባላት የገለፁት።

#AlAin
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፦

- ታግተው የነበሩ 21 የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መንግስት ባደረገው ጥረት ተለቀዋል።

- በእገታ ላይ የነበሩትን ተማሪዎች በሰላማዊ መንገድ ያለምንም ጉዳት ለማስለቀቅ መንግስት ከአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች ፣ ከወጣቶችና ከመከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ መዋቅሮች ጋር ሲሰራ ቆይቷል። የሰላም ጥረቱ ፍሬ በማፍርቱ ታግተው ከነበሩ ተማሪዎች ውስጥ 13 ሴትና 8 ወንድ በድምሩ 21 ተማሪዎች በሰላማዊ ሁኔታ ተለቀዋል

- ይሁን እንጂ አሁንም ቀሪ 6 ተማሪዎች በእገታ ላይ መሆናቸውን በአካባቢው የተሰማራው የፀጥታ ኃይል መረጃ ሰጥቷል።

- ታግተው ያሉ ቀሪ ተማሪዎችን ያለምንም ጉዳት እንዲለቀቁ ለማድረግ መንግስት ከአገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ጋር በመተባበር በአካባቢው ወግና ስርዓት ለማስለቀቅ እየተሰራ ነው።

- መንግስትም በተከታታይ ከእገታ ያልወጡ 6 ተማሪዎችን ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለውን ጥረት በየጊዜው ለህዝብ መረጃ ያደርሳል።

(EBC, PHOTO: ETHIO FM)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ከኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ ነገ ጥር 3 ቀን 2012 ዓም በጆሃንስበርግ በሚገኘው የኢምፔሪያል ዋንደረርስ ስቴዲየም በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ያገኛሉ። በዚህም ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩና ኢትዮጵያውያኑ ሰፊ የማኅበረሰብ ውይይት ያካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የቲክቫህ ቤተሰቦች...

በዛሬው ዕለት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በጊዮን ሆቴል ከወራት በኃላ ዳግም ተገናኝተው ነበር። ዛሬ የተገናኙት የቲክቫህ ቤተሰቦች የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ባለፈው ዓመት(2011)በተሰሩት የፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ/STOP HATE SPEECH/ የተሳተፉ፣ረጃጅም ርቀቶች እየተጓዙ ለሀገራቸው ሰላም ማድረግ የሚችሉትን አስተዋፆ ያደረጉ ወጣቶች ናቸው።

- ዛሬ በጊዮን ሆቴል በነበረው ዝግጅት ላይ ልዩ የእውቅና እና የምስጋና ሰርተፊኬት ለቤተሰቦቻችን ተብረክቶላቸዋል።

- የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሚኒስቴር የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ባለፈው ዓመት በሰሩት የፀረ ጥላቻ ንግግር ዘመቻ ላበረከቱት አስተዋፆ እውቅና ሰጥቷል፤ የምሳ ግብዣም አድርጓል።

- ለተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ለጉዟችን አስተዋፆ ለነበራቸው አካላት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ስም የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል። ለመቐለ፣ሃዋሳ፣ ወልዲያ፣ወሎ፣ደብረብርሃን፣ ጅማ፣ ሀረማያ፣ ዋቻሞ፣ ወላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ፣ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲዎች የምስጋና ወረቀት ተበርክቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት በቴሌግራም ብቻ የተሰባሰቡ የቤተሰቡን ወጣቶች በማስተባበር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመዘዋወር በወጣቶች መካከል ወንድማማችነት፣ እህትማማችነት እንዲጎለብት፤ በማህበራዊ ሚዲያ የተስፋፋው የጥላቻ ንግግር ሀገሪቱን ወደለየለት ቀውስ ውስጥ እንዳይከታት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የግላቸው አስተዋፆ እንዲያደርጉ፣አንዱ አካባቢ ያለው ወጣት በሌላ አካባቢ ካለው ወጣት ጋር እንዲገናኝ እና ስለሀገሩ እንዲመክር፣ከማህበራዊ ሚዲያው ውጭ መሬት ያለውን እውነታ ወጣቱ እንዲረዳ፣ከምንም በላይ በወጣቶች መካከል መከፋፈል ሳይኖር በአድነት ለሀገር ሰላም መቆም እንዲቻል መጠነኛ አስተዋፆ ማበርከቱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia