የመንግሥት አካላት ምላሽ ስለታገቱት ተማሪዎች...

ከኦሮሚያ ክልል፦

የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በምዕራብ ኦሮሚያ ስላለው ጠቅላላ ሁኔታ "ምንም አይነት መረጃ የለኝም። እኔ የሰማሁት ነገር የለም" ይላሉ።

ጉዳዩ እርሳቸው የሚመሩት ቢሮን በቀጥታ የሚመለከት መሆኑን በመጥቀስ ስለጉዳይ እንዴት መረጃ ሳይኖራቸው እንደቀረ ከቢቢሲ የተጠየቁት ኮሎኔል ገረሱ፤ "እኔ ምንም አልሰማሁም ነው የምልህ። ለምድነው የምትጠይቀኝ?" በማለት መልሰዋል። የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በበኩላቸው ታፍነው የተወሰዱ ተማሪዎች የሉም ብለዋል። ኃላፊው ታፍኖ የተወሰደ ተማሪ የለም ከማለት ውጪ ማብራሪ መስጠት አልሰጡም።

የአማራ ክልል፦

ቢቢሲ የደወለላቸው የአማራ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር፤ "አሁን ማውራት የማልችልበት ቦታ ነው ያለሁት" በማለት የእጅ ስልካቸውን ዘግተውታል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከአምስት ቀናት በፊት ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፤ "አራት ተማሪዎች ታግተው እንደሚገኙ መረጃው አለኝ" ማለታቸው ይታወሳል። ታግተው የሚገኙት ተማሪዎች በወላጆቻቸው ጋር በስልክ አልፎ አልፎ እንደሚገናኙ ጭምር ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ ተማሪዎቹ ተለቀው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ከአባ ገዳዎች፣ ከአከባቢው ማህብረሰብ እና ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር ውይይት እያደረግን ነው ብለዋል።

#BBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot