TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢሬቻ2012

የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት ሙስጠፌ መሀመድ እና የጋምቤላ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት ታኮን ጆክ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው የዋዜማ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል።

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚንስትር ኔታኒያሁ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ከሀገሬ ለማስወጣት ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር ተነጋግሬያለሁ ብለዋል፡፡ ስደተኞቹ ወደ ኤርትራ ቢመለሱ፣ በፕሮጀክቶች እንዲታቀፉ አ(ስ)ደርጋለሁ ሲሉ ዐቢይ እንደነገሯቸው መግለጻቸውን የዘገበው ዘ ታይምስ ኦፍ እስራዔል ነው፡፡ የፕሮጀክቶቹ ምንነትና ዐቢይ ከኤርትራ መንግሥት ጋር ይነጋገሩበት አይነጋገሩበት አልተገለጸም፡፡ በቴላቪቭ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ግን በነሐሴው የመሪዎቹ ውይይት ይሄ ጉዳይ አልተነሳም ሲል አስተባብሏል፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምዕራብ_ጎንደር

በክልሉና በምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላምና ፀጥታ ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ ነበረ ያላቸውን ሁለት ተጠርጣሪዎችን መያዙን የዞኑ ሰላምና ደህንነት ግንባታ መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለኢዜአ እንደተናገሩት ተጠርጣሪዎቹ በአካባቢው ያለውን የፀጥታ መዋቅር በማጥናት ጥቃት እንዲፈፀም ለማድረግ ተዘጋጅተው የነበሩ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም ሰሞኑን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት ወደ ምዕራብ ጎንደር ዞን ለማምጣት በማለም ሲንቀሳቀሱ እንደነበረም ተናግረዋል።

በህብረተሰቡና በፀጥታ አካሉ ትብብር የተያዙት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ጉዳያቸው እየተጣራ መሆኑን ገልጸው ሌላ ተጠርጣሪ እንዳለ ግለሰቦቹ በሰጡት ጥቆማ መሰረትም ፍለጋ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለቱ ግለሰቦች በመተማ እየተንቀሳቀሱ ባለበት ወቅት በህብረተሰቡ ጥርጣሬና ጥቆማ በትናንትናው እለት መያዛቸውንም አብራርተዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሰሞኑን በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተፈጠረው ግጭት በ5 ቀን ብቻ የ22 ዜጎች ህይወት ማለጉን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሙሉውን ያንብቡ👇
reuters.com/article/amp/af/idAFKBN1WJ0Q0-OZATP

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያና የሩሲያ የትብብር ማዕቀፎች በጥቀምት 2012 ዓ.ም በሚካሄደው የሩሲያ አፍሪካ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል። ከመስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሩሲያ ፒተርስበርግ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 7ኛው የኢትዮ-ሩስያ የጋራ ኮሚሽን ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Sagalee Qeerroo Bilisuma

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ነሀሴ 29 ገርጂ አካባቢ በቁጥጥር ስር የዋሉ አምስት የSagalee Qeerroo Bilisumaa አባላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዛሬ ጠይቋል።

Via Elias Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጓንግ እና ቡሆና አካባቢ ይንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ኃይሎች እስከ ትጥቃቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተነገረ!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጓንግ እና ቡሆና አካባቢዎች በፀጥታ ማደፍረስ ተግባር ይንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች ከጦር መሣሪያዎቻቸው ጋር በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ፡፡ የጦር መሣሪያዎቹ ስናይፐር፣ መትረየስ፣ ኤምፎርቲና አብራራው እንደሆኑም ታውቋል፡፡ የታጠቁ ኃይሎቹን እስከ ጦር መሣሪያዎቻቸው በቁጥጥር ሥር ያዋሏቸው የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር የተሠማሩ የፀጥታ አካላት ናቸው፡፡ የጦር መሣሪያዎቹና ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት መስከረም 18 እና 20 ቀናት 2012ዓ.ም መሆኑንም የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

Via አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አውሮፕላን ተከስክሶ የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ!

አንቶኖቭ-12 የተሰኘ አውሮፕላን ሊቭቭ ተብላ በምትጠራው የምዕራባዊ ዩክሬን ከተማ አቅራቢያ ተከስክሶ አምስት ሰዎች ሞቱ። የአደጋው ምክንያትም አውሮፕላኑ ለማረፍ ካቀደበት ከተማ ከመድረሱ በፊት ነዳጅ በመጨረሱ ነው ተብሏል።

አውሮፕላኑ ከስፔኗ ቪጎ ከተማ ወደ ቱርክ ኢስታንቡል በመብረር ላይ እንደነበረ የዩክሬን የመሰረተ ልማት ሚንስትሩ ቭላዲስላቭ ክሪክሊ ተናግረዋል። የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ሚንስቴር እንዳለው ደግሞ በበረራው ሰባት ሠራተኞችና አንድ ሌላ ግለሰብ ደግሞ ከዕቃ ጋር ተጭኖ እንደነበር ገልጿል። የተጫነው ዕቃ ምን እንደነበር ግን የተባለ ነገር የለም።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ግጭቱ የተከሰተው የማኅበረሰቡ አባላት ራሳቸውን ለመከላከል ባደረጉት ርምጃ ነው!"-- የቅማንት ኮሚቴ ሊቀመንበር ፈቃዱ ማሞ

በአማራ ክልል ጎንደር ሰሞኑን #በታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 22 ሰዎች መገደላቸውን ሮይተርስ የዜና ምንጭ ዘግቧል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፕሬዚደንት ደሳለኝ ጫኔን ጠቅሶ እንደዘገበው፦ ግጭቱ የተፈጠረው ባለፈው ዐርብ ታጣቂዎች ወደ ጎንደር የሚጓዙ ሰዎችን ከሚኒባስ አስወርደው 10 ሰዎችን ከገደሉ በኋላ ነው ብሏል። በሚቀጥለው ቀን 12 ወታደሮች መገዳለቸውንም አክለው ጠቅሰዋል ብሏል ሮይተርስ። ፕሬዚዳንቱ የደረሰው ጥቃት ከቅማንት ኮሚቴ ጋር ይያያዛል ማለታቸውንም ዘግቧል።

የቅማንት ኮሚቴ ሊቀመንበር ፈቃዱ ማሞ ወቀሳውን አስተባብለው ግጭቱ የተከሰተው የማኅበረሰቡ አባላት ራሳቸውን ለመከላከል ባደረጉት ርምጃ ነው ማለታቸውንም የዜና ምንጩ አትቷል። የአማራ ክልል ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ «በጥናት ላይ የተመሰረተ የማያዳግም ርምጃ ለመውሰድ» መዘጋጀቱን በመግለጥ «ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እየተሠራ» ነው ሲል አስታውቋል።

Via ሮይተርስ /DW/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲ በሰላማዊ የመማር ማስተባር ሒደት ዙሪያ ከአካባቢ ነዋሪዎችና ከአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ትናንት ውይይት አካሔዷል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት አብሮ የኖረ ፣ ክፉ ደጉን በጋራ ያሳለፈ፣ የተጋባ፣ የተዋለደ፣ የተዋሃደ ሕዝብ ነው!" #አብን

የኢሬቻ በዓልን በተመለከተ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ:-

ከሁሉም በማስቀደም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ወንድም ለሆነው የኦሮሞ ሕዝብ እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል። የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት አብሮ የኖረ ፣ ክፉ ደጉን በጋራ ያሳለፈ፣ የተጋባ፣ የተዋለደ፣ የተዋሃደ ሕዝብ ነው። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ባለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያ የተፈጠሩት ጥራዝ ነጠቅና በአማራ ጥላቻ የሰከሩ ብሔርተኞች የሁለቱን ሕዝቦች ግንኙነት የጨቋኝና የተጨቋኝ ፤ አለፍ ሲልም የቅኝ ገዢና ተገዢ አድርገው በማቅረብ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ለዘመናት የዘለቀውን ጠንካራ ትስስር ለማላላት ቢሰሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ዛሬም እንደትላንቱ የአማራ ሕዝብ ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር በጋራ አርሶ፣ ነግዶ፣ ሰርቶ፣ ተጎራብቶ ፣ እየተጋባና እየተዋለደ፣ በሃዘን በደስታው እየተገናኘ አብሮ እየኖረ ነው።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-04-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AMH-Dawit-Borena-10-3-2019
#update ባለፈው ዓርብ በምሥራቅ ጉጂ ሦስት ሰዎች በመከላከያ ኃይል መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። የግድያው መነሻ በአካባቢው በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በሚንቀሳቀሱና በመከላከያ ኃይል መካከል በተነሳዉ ግጭት መሆኑን ነዋሪዎች አስረድተዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

"አዲስ አበባ የሁሉም #ኢትዮጵያዊያን ከተማ እንደመሆኗ መጠን የኦሮሞ ህዝብም በከተማው የኢሬቻን በዓል ለማክበር በመቻሉ የተሰማኝ ደስታ ከፍ ያለ ነው፡፡ በቀጣይነትም ከተማችን አዲስ አበባ ኃላፊነት ወስዳ የኢሬቻን በዓልን ጨምሮ ሌሎችን የሃገራችን በዓላት እና እሴቶች በሃገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ እና በዓለም መድረኮች ሁነቶችን በመጠቀም ታስተዋውቃለች። ከተማ አስተዳደራችን እና ነዋሪዎቿ በታሪክ አጋጣሚ የዚህ ታሪካዊ ኃላፊነት አስተናጋጅ በመሆናችን ደስታ ይሰማናል፡፡ በመጨረሻም የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በዚህ ደረጃ በተቀናጀ እና ባማረ መልኩ እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ የከተማችን ነዋሪወች እና ባለሃብቶች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡" ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DOHA በከፍተኛ ትንቅንቅ...በአስደማሚ ፉክክር ኬንያ ወርቅ አገኝች!!! ሀገራችን ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አለን! ኢትዮጵያ በ3,000 ሜትር መሰናክል በለሜቻ ግርማ አማካኝነት የብር ሜዳልያ አግኝተናል!

Via @tikvahethsport
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ከኮልፌ...

"ኮልፌ ኮምፕሬንሲቭ ትምህርት ቤት አካባቢ ህብረተሰቡ እና አመራሮች ለነገው የኢሬቻ በዓል ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ያሉ እንግዶችን ውሃና ዳቦ በማቅረብ በክብር እየተቀበሉ ነው።" #Amanuel

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተማሪዎች ቅናሽ አደረገ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደተለያዩ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሚጓዙ ተማሪዎች የ20% የአየር ትኬት ቅናሽ ማድረጉን ገልጿል። ተማሪዎች የአየር መንገዱን የሞባይል መተግበሪያ እና ድረ ገፅ በመጠቀም FNH01 ፕሮሞ ኮድን በማስገባት የቅናሹ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ አስታውቋል።

የሽያጭ ጊዜ : እስከ ጥቅምት 07 ቀን 2012 ዓ/ም
የበረራ ጊዜ : እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ/ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ኤልያስ መልካ ህይወት ማለፉ ተገለጸ!

በኢትዮጵያ የዘመናዊ በሙዚቃ ታሪክ ትልቅ አስተዋጽኦ የተጫወተው ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ዛሬ ማለዳ ህይወቱ ማለፉን ኢትዮ ኤፍ ኤም አረጋግጧል።

Via Ethio FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል! #TIKVAH_ETHIOPIA

PHOTO: TESFAYE & ROBEL
@tsegabwolde @tikvahethiopia