TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‘‘ኢሬቻ ለሰላም’’ የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው!

ኢሬቻ ለሰላም በሚል ስያሜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተሳተፉበት የሚገኘው የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ተጀምሯል። መነሻውን መስቀል አደባባይ ባደረገው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ታዋቂ አትሌቶች ተሳታፊዎች ናቸው። የኢሬቻን በዓል መስከረም 24 በአዲስ አበባ እንዲሁም መስከረም 25 በሆራ አልሰዲ ለማክበር ቀጠሮ ተይዟል።

Via BBC Amharic
ፎቶ: OMN, GIRMA GUTEMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሆሳዕና⬆️

ከዶክተር አብይ አህመድ በተጨማሪ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሆሳዕና ተገኝተዋል።

ፎቶ: Ha/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ላልይበላ⬆️

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች በላልይበላ ከተማ አስተዳደር ሠላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በሰሜን ወሎ ዞን ላልይበላ ከተማ አስተዳደር ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ ሠልፉ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ነው፡፡ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት በህግ እንዲጠየቁም ጥያቄ እየቀረበ ነው።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደባርቅ⬆️

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ አስተዳደር ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ ሠልፉ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ መሆኑን ነው የተገለጸው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍኖተ ሰላም⬆️

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሠላም ከተማ አስተዳደር ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ሠላማዊ ሠልፍ መሆኑን ነው ሰልፈኞቹ የተናገሩት፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንዝ መሐል ሜዳ⬆️

መንዝ መሐል ሜዳ ከተማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ ምዕመናኑ ከየአብያተ ክርስቲያኑ ልዩ ልዩ መልዕክቶችን እያሰሙ ወደ መሐል ሜዳ ከተማ መስቀል አደባባይ እየተጓዙ ነው፡፡

ምንጭ፡- የመሐል ሜዳ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ማርቆስ⬆️

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በደብረ ማርቆስ ከተማ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ሠላማዊ ሠልፍ መሆኑን ነው ሰልፈኞቹ የተናገሩት፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወልዲያ ሼህ መሃመድ አላሙዲን ስቴዲየም⬆️

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በወልዲያ ከተማ አስተዳደር ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ሠላማዊ ሠልፍ መሆኑን ነው ሰልፈኞቹ የተናገሩት፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#IrreechaaPeaceRace ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና⬆️
"ኢሬቻ ለሰላም ሩጫ" አዲስ አበባ⬆️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወረኢሉ ከተማ⬆️

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በወረኢሉ ከተማ አስተዳደር ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ #ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዱራሜ እየተካሄደ የሚገኘው የሰላም ሩጫ ተጠናቋል!
#ኢሬቻ2012

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የኢሬቻ ሰላም ሩጫ ላይ በርካታ ሰዎች ተሳትፈዋል። ከአማራ ክልል፣ ከደቡብ ክልል ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 500 ገደማ አትሌቶችም በሩጫው ተሳትፈዋል።

በሩጫው በክብር እንግድነት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት የተገኙ፣ አቶ አዲሱ አረጋ እና ሌሎችም የመንግስት ሹማምንት ተገኝተው ነበር። በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው ፖለቲከኞች፣ አክቲቪስቶች፣ አትሌቶች አርቲስቶች የዝግጅት አካል ነበሩ። ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ እና ሌሎችም በእንግድነት በቦታው ተገኝተው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ በኢሬቻ ለሰላም ሩጫ ላይ በእንግድነት ተገኝተው ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሆሳዕና⬆️ ከዶክተር አብይ አህመድ በተጨማሪ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሆሳዕና ተገኝተዋል። ፎቶ: Ha/TIKVAH-ETH/ @tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሆሳዕና

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልኡካቸው በሆሳዕና ከተማ ህዝባዊ ውይይት ለማድረግ ሲደርሱ በአካባቢው ነዋሪ በሆሳዕና አቢዮ ስቴድየም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ‘‘ኢሬቻ ለሰላም’’ የጎዳና ላይ ሩጫ አሸናፊዎች ታውቀዋል!

ኢሬቻ ለሰላም በሚል ስያሜ በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ከወንዶች አትሌት በሪሁ አረጋዊ እና ከሴቶች ደግሞ አትሌት ኦብሴ አብደታ አሸናፊ ሆነዋል።

በወንዶችና በሴቶች አሸናፊ ለሆኑት የዋንጫ፣ የምስክር ወረቀት እና የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በውድድሩ በወንዶች ኃይለማሪያም ኪሮስ 2ኛ ሲወጣ ደጀኔ ደበላ 3ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

በሴቶች ደግሞ መስታወት ፍቅሬ 2ኛ አንቻለም ሀይማኖት ደግሞ 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በውድድሩ በሁለቱም ፆታ 2ኛ እና 3ኛ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የ30 ሺህ እና የ20 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ሽልማቱን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮነሬል ደራርቱ ቱሉ እና የኦሮሚያ ክልል ም/ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለአሸናፊዎቹ አበርክተውላቸዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡ ሠልፉ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና በምዕመኗቹ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ነው፡፡ በሰልፉ ላይ ‹‹በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ይቁም፡፡ በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት በሕግ ይጠየቁ፡፡›› የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

ሰልፍ ከተካሄደባቸውን ከተሞችና አካባቢዎች መካከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ይገስኙበታል፦

•ራያ ቆቦ
•ኮን
•ዳንግላ
•ሞጣ
•ዳባት
•ጫጫ
•መሐል ሜዳ
•ውጫሌ
•ደላንታ ወረዳ
•ደብረ ብርሃን
•ደብረ ማርቆስ
•ወልዲያ
•ባህር ዳር
•ላልይበላ
•ደባርቅ
•ቡሬ
•ቢቸና
•ፍኖተ ሰላም
•ወረኢሉ
•ኢንጂባራ
•መርዓዊ
•አረሪቲ

በበርካታ ቦታዎች የተካሄዱት ሰልፎችም በሰላም መጠናቀቃቸውን የቤተሰቦቻችን አባላት ገልፀዋል።

#TIKVAH_ETH

ፎቶ: ከማህበራዊ ሚዲያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማህበራዊ ሚዲያን በስፋት ከሚጠቀሙ ከፍተኛ የODP ባለስልጣናት መካከል አንደኛው የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ ከደቂቃዎች በፊት ይህን "አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና አቶ ጃዋር መሃመድ" ያሉበትን ፎቶ በመለጠፍ -- "weraj Yelem😉" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል በርካቶችም ሲቀባበሉት ተመልክተናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ2012

የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ-ዝግጅት መጠናቀቁን የወላይታ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡ በበዓሉ አከባበር የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

የወላይታ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር የነበረውን አንድነት በይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል በዞኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የጉዞ ግፋታ ልዑካን ቡድን ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች መጓዛቸውን ተነግሯል፡፡

በዚህም የጉዞ ግፋታ አባላት ለትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚኤልና ለአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው ግብዣ አቅርበዋል፡፡

’የጉዞ ጊፋታ’’ ልዑካን ቡድን እንቅስቃሴ ዋና ዓላማው የዘንድሮውን የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል ከመላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በጋራ ለማክበር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በመስከረም 15 ቀን በወላይታ ጉተራ አዳራሽ በሚካሄደው ሲምፖዚየም የብሔሩ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ አስመልክቶ በምሁራን የተዘጋጀው ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚቀርብ ደሬቴድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በዓሉ በዞኑ ማዕከል በመስከረም 18 ቀን 2012 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም እንደሚከበር ተጠቁሟል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የየም የዘመን መለወጫ "የሄቦ በዓል" በደማቅ ሁኔታ በአዲስ አበባ የባህል አዳራሽ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia