TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዝርዝር የቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ  ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፏል። የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስለ ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አለ ? #የመንግስት_ግዥ_ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በመሄድ የውስጥ ገቢ ማስገኛ በሚል " ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ " የተባለ አማካሪ ድርጅት በማቋቋም በስማቸው ንግድ ፍቃድ በማውጣት…
" በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው " - የፍትህ ሚኒስቴር

ትላንት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የፓርላማ አባሉ ዶ/ር ጫላ ዋታ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

የቀድሞው የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጫላ ዋታ፤ #ዛሬ_ረቡዕ ረፋድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፍትሕ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትን ዋቢ በማድረግ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ዘግቧል።

ዶ/ር ጫላ በፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉት #በሙስና_ወንጀል_ተጠርጥረው መሆኑን ዳይሬክቶሬቱ ለድረገፁ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ማስታወሻ ፦ ዶ/ር ጫላ ዋታ የተጠረጠሩባቸው የሙስና ጉዳዮች ምንድናቸው ? እሳቸውስ ትላንት ለህ/ተ/ም/ቤት ምን አሉ ? መለስ ብለው በዚህ ያንብቡ : https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/77517

@tikvahethiopia