TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና!

የሶርያ እና የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች በኢድሊብ በፈጸሙት የአየር ድብደባ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የሶርያ የሰብዓዊ መብት ታዛቢ ቡድን አስታወቀ። ካለፈው #ሚያዝያ ጀምሮ የሶርያ መንግሥት እና ሩሲያ የተቃዋሚዎች ጠንካራ ይዞታ በሆነው #የኢድሊብ አካባቢ እረፍት የለሽ ዘመቻ ላይ መሆናቸውን የዜና አውታሮች ዘግበዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

• "...ውጤቴን ከተስተካከለ በኃላ ነው ትላንት ማታ ያወኩት፤ 32 ነበር አሁን 95 ሆኗል።"

• "ከታች ባሉት ክፍሎች ተማሪ እያለሁ የደረጃ ተማሪ ነበርኩ፤ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ግን 1ኛ ነው የወጣሁት።"

• "ፓይለት መሆን ነው የምፈልገው"

• "በትንሹ 600 ቤት ለመግባት በደንብ አስቤበት ስዘጋጅ ነበር"

#ቃልኪዳን_አስቻለው በአዲስ አበባ ከተማ የካቴድራል ትምህርት ቤት ተማሪ ናት በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 643 ነው ያስመዘገበችው። TIKVAH-ETH ከታች ላሉት ተማሪዎች ተሞክሮዋ ይጠቅማል ብሎ በማሰብ አነጋግሯታል በቀጣይ ቀናት ይቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት #ከጅማ_ዞን #ጌራ_ወረዳ

"እቅዴ ከዚህም በላይ ነበር፤...ይህን በማምጣቴ ደስ ብሎኛል"

"የአፕቲትዩድ ውጤቴ መጀመሪያ 29 ነበር፤...ተስተካክሎ የመጣው 97 ነው"

"የመጀመሪያ ፈተና ስለነበር ደንግጬ ነበር ፈርቼም ነበር፤ ...ወደ መልስ መስጫ ወረቀቴ በችኮላ ነው የገለበጥኩት በዛ ሰዓት የፈጠርኩት ስህተት ነው ብዬ ገምታለሁ"

"ያለኝን ሰዓት በሙሉ ነበር ተጠቅሜ እያነበብኩ የነበረው"

"የስልክ ተጠቃሚ አይደለሁም፤ የማህበራዊ ሚዲያም ላይ የለሁም፤ ያለኝን ሰዓት በሙሉ ማሳለፍ የምፈልገው በትምህርቴ ላይ ብቻ ነው"

"በራሴ ስለምተማመን ሜዲስን እደምገባ እርግጠኛ ነኝ፤ እዛም ሰቅዬ እንደምወጣ እርግጠኛ ነኝ!"

"ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስካሁን 1ኛ ነው የወጣሁት"

"ለዚህ ፈተና መዘጋጀት የጀመርኩት ከ11ኛ ክፍል ጀምሮ ነው።"

#ነኺማ_ቲጃኒ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን #ጌራ_ወረዳ በሚገኘው የጌራ ፕሪፓራቶሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 638 ነው ያስመዘገበችው። TIKVAH-ETH ከታች ላሉት ተማሪዎች ተሞክሮዋ ይጠቅማል ብሎ በማሰብ አነጋግሯታል በቀጣይ ቀናት ይቀርባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ዐብይ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጰያዊያንን በመያዝ አዲስ አበባ ገቡ!

ጠቅላይ ሚኒስር ዶክተር አብይ አህመድ #በሱዳን እስር ላይ የነበሩ 105 ኢትዮጰያዊያንን በመያዝ አዲስ አበባ ገቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል በመሰረቱት የሽግግር መንግስት ዙሪያ የመጨረሻ የስምምነት ፈርማ ስነ ስርዓት አጠናቀው ሲመለሱ ነው ኢትዮጵያዊያኑን በመያዝ አዲስ አበባ የገቡት፡፡ ኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች በሱዳን እስር ቤቶች የነበሩ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግት የስራ ሃላፊዎችን ያሳተፈ የጽድት ዘመቻዛሬ ጠዋት በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ ኢተያ ከተማ ተካሄዷል፡፡ በጽዳት ዘመቻው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የመከላከያ ሚኒስተሩ አቶ ለማ መገርሳ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተሳትፈውበታል፡፡ አሁን ላይም በአካባቢው በኩታገጠም ልማት በአርሶ አደሮች የለማውን የስንዴ ማሳ በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአርሲ ዞን በኩታ ገጠም የለማ ስንዴማሳ እየጎበኙ ነው፡፡ በዚሁ ጉብኝት ላይም የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተገኝተዋል፡፡ ዛሬ ረፋዱ ላይ 78 ሄከታር ማሳ ላይ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በአርሶ አደሮች በኩታ ገጠም የለማውን የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡ አሁን ላይም በተመሳሳይ መልኩ በኢገሉጢጆ ወርዳ በኩታ ገጠም በአርሶ አደሮች የለማውን የስንዴ ማሳ ለመጎብኘት ወደ ዚያው አምርተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቀጣዩ 4 ወራት ውስጥ 9,000 የ 40/60 ኮንደሚንየም ቤቶች እጣ ይወጣል ተባለ። 200,000 ባለ 20/80 እና 100,000 ባለ 40/60 ቤቶች ግንባታ ለመጀመርም ታቅዷል።

Via Tesfaye Getnet/ካፒታል ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሶሳ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ብሄራዊ ክልሎች መንግስታት የልማትና የጸጥታ ትብብር የጋራ ምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡ የምክክር መድረኩን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት አቶ አሻድል ሀሰንና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ እየመሩት ሲሆን የካቢኔ አባላትም እየተሳተፉ ናቸው፡፡

በምክክር መድረኩ በ2011ዓ.ም በልማትና በጸጥታ ዘርፎች በጋራ የሰሯቸው የጸጥታ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል፡፡ የተመዘገቡ መልካም ውጤቶችና ያጋጠሙት ተግዳሮቶች ይገመገማል፡፡ ስኬቶችን ለማስቀጠልና ተግዳሮቶችን ለማስወገድ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የ2012 እቅድም ቀርቦ ውይይት ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸"የደብረታቦር በጌምድር ሴቶች አሸንደዬ አሸንድ አበባ እርግፍ እንደ ወለባ እያሉ ሲዘፍኑ" #ETHIOPIA

ሁላችንም በድምቀት እምናከብረው የደብረታቦር ቡሄ አሸንድየ በዓል በድምቀት ለማክበር ደብረታቦር ዝግጅቷን አጠናቃ ሰኞ ነሀሴ 13 2011 እናተን ትጠብቃለች።

በዓላዊ ትውፊታችንና ሃይማኖታዊ ሥርዓቱ እንዳይጠፋ እና እንዳይበረዝ ግዴታችን ልንወጣ ይገባል በድጋሜ እንኳን ለደብረታቦር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

Via @Walebirku
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንዲት እስራኤላዊ ተማሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ጠፍታ እየተፈለገች ነው!

/ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/

የ21 አመቷ አያ ናምኔህ ባለፈው ቅዳሜ የደናኪል በረሀ አካባቢ ከሌሎች ሰዎች ጋር ጉብኝት ስታደርግ ቆይታ ደብዛዋ መጥፋቱ ታውቋል። የአያን መጥፋት ተከትሎ በነብስ አድን ቡድኖች እና የአካባቢው ፖሊስ አሰሳ እየተደረገ ሲሆን የአካባቢው ሙቀት አሁን ላይ 50 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መሆኑ ለህይወቷ ስጋት እንዳለው የእስራኤል ሚድያዎች እየዘገቡ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህችን እስራኤላዊ ያለችበትን የሚያውቅ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውሎ ያሳውቀን +251 - 914940462

Dear Ethiopia.

I write you with urgent news. One of my town residents was on a trip to Ethiopia and went missing.

She was last seen hiking in the Danakil depression area and went missing after. She is 22. My entire town is nervous for her - and I hope you can help us share this message around to find her.

Thank you so much Ethiopia.
If you have any information on her, please call: +251 - 914940462

#NAS_DAILY

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ2012 ዓ.ም በዩኒቨሲርቲዎች፦

• ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች 15 አዳዲስ ትምህርቶች ይሰጣሉ
• የዲግሪ ፕሮግራም አራት ዓመት ይሆናል

በ2012 ዓ.ም ወደ መንግሥትም ሆነ የግል ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ አዲስ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩት በ15 አዳዲስ ትምህርቶች መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ። በሦስት ዓመታት ይጠናቀቅ የነበረው የዲግሪ ፕሮግራም ወደ አራት ዓመት ከፍ ብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሚሰጡት ክሪቲካል ቲንኪንግ፣ ሂስትሪ(ታሪክ) ኤንድ ዘሆርን፣ ጂኦግራፊ ኤንድ ዘሆርን፣ አንትሮፖሎጂ፣ ሳይኮሎጂ፣ ሂሳብ እና ሌሎቹም ለሁሉም የሚሰጡ የጋራ (ኮመን ኮርሶች ) ሲሆኑ ይህም ተማሪዎች በአስተሳሰብ ምጡቅ እንዲሆኑ፣ ብዝሀነትን፣ የሀገርን ባህል፣ አገር በቀል ዕውቀቶችንና ታሪክ እንዲያውቁ የሚያደርጉ ናቸው።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱአለም አድማሴ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራት፣ ስነምግባር እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በሚመለከት የሀገሪቱ የትምህርት ስርዓት እንዴት ይቃኝ በሚለው ላይ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በምሁራን ሰፊ ጥናት ሲደረግና በርካታ ህዝብም ሲወያይበት ቆይቷል። ይሄንኑ መነሻ በማድረግም ብዙ ማሻሻያ እና ለውጦች ተደርገዋል።

በዚሁ መሰረት በ2012 ዓ.ም #ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚገቡ ተማሪዎች አዳዲስ ኮርሶችን መስጠት እንዲችሉ ስምምነት ላይ ተደርሶ ለዚሁ ዝግጅት መደረጉን ጠቅሰው፣ አሁን ያለው ሁኔታ ትምህርቱን ለመጀመር የሚቻል ነው ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-18

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ2012 ዓ.ም ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የሚሰጡት የትምህር ዓይነቶች ለሁሉም የትምህርት ክፍሎች የጋራ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እስራኤላዊቷ ተማሪ ህይወቷ አልፏል!!

የ21 አመቷ እስራኤላዊት #አያ_ናምኔህ ህይወት አልፎ መገኘቷን #TheJerusalemPost ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእስራኤላዊቷን ተማሪ አስክሬን የያዘው ሂሊኮፕተር🚁ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ነው! #ESK #ETHIOPIA #ET

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከደብረ ብርሃን...

"በደብረ ብረሀን አካባቢ በሚገኘው የሚኒሊክ የትውልድ ስፍራ አንጎለላ #እንቁላል_ኮሶ የሚኒሊክ 175ኛ አመት የልደት በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል" ሠለሞን ከበደ ከደብረ ብርሃን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቦንብ ጥቃት የ63 ሰዎች ማለፉ ተሰማ!

በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል ከተማ የሰርግ ስነ ስርዓት ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት የ63 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈው 63 ሰዎች በተጨማሪ ከ180 በላይ የሰርጉ ታዳሚዎች መቁሰላቸው ተነግሯል፡፡

ጥቃቱ በአጥፍቶ ጠፊዎች ስለመፈጸሙ የአይን እማኞች ለመገናኝ ብዙሃን ተናግረዋል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው በመዲናዋ ምዕራባዊ ክፍል የሺዒኣ ሙስሊሞች በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ ነው ተብሏል፡፡ የታሊባን ተዋጊዎች ቡድን ከዚህ ጥቃት ጀርባ እንደሌለበት አስታውቋል፡፡ እስካሁን የጥቃሩን ሃለፊነት የወሰደ አካል እንደሌለም ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

ምንጭ፡- ቢ ቢ ሲ/fbc
ፎቶ: VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የተሳተፉበት የፅዳት ዘመቻ ዛሬ በአዲስ አበባ ኦሮሞ ባህል ማእከልና አካባቢው ተካሂዷል። በመላው ኢትዮጵያ በዛሬው እለት አገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ በመካሄድ ላይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድም ዛሬ ማለዳ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ኢተያ ከተማ በተካሄደው የፅዳት ዘመቻ ላይ ተሳትፈዋል።

በአዲስ አበባም የከተማው ነዋሪዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናትና የተለያዩ ድርጅቶች ዛሬ ከማለዳው  ጀምረው አካባቢያቸውን በማፅዳት ላይ ናቸው። በከተማዋ በሚገኘው የኦሮሞ ባህል ማዕከልና አካባቢው ላይም በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቢሮ  ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተሳትፎ የፅዳት ዘመቻው ተካሂዷል።  በአካባቢው የችግኝ ተከላም አከናውኗል። የጽዳት ዘመቻው በሁሉም የኦሮሚያ ክልል በመካሄድ ላይ መሆኑም ታውቋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር ታከለ ኡማ በከተማዋ ባሉ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የዕድሳት ሂደቱ ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል፡፡ ቦሌ መሠናዶ ፣ ኮከበ ጽበሃ እና ጥቁር አንበሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በዛሬው ዕለት ምልከታ ከተደረገባቸው ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይገኙበታል፡፡

Via MayorOfficeAA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢንሳ የቀድሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሌተናል ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ዋስትና ታገደ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በ30,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ለይግባኝ ሰሚው ችሎት ይግባኝ አቅርቦ እንዲታገድ አድርጓል፡፡

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው #በእስር ላይ የሚገኙት ቀድሞ የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ፣ በተመሠረተባቸው ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ የሙስና ወንጀሎች አዋጅ ቁጥር 881/2007፣ አዋጅ ቁጥር 780/2005፣ አዋጅ ቁጥር 591/2007 የወንጀል ሕግ 808 ተላልፈዋል በማለት ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ በማስረዳቱ በአምስት ክሶች  እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር፡፡

የተጠቀሱባቸው #የሕግ ድንጋጌዎች #ዋስትና እንደማይከለክሉ በማስረዳት ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም በጠበቃቸው አማካይነት ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን እንዲጠብቅላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የተጠቀሱት ሕጎች ከ15 ዓመታት በላይ ሊያስቀጧቸው እንደሚችሉ በመግለጽ፣ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲደረግ ተከራክሮ ነበር፡፡

ፍርድ ቤቱ የዋስትና ጥያቄው የሕግ ክልከላ ያለበት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን መርምሮ፣ የዓቃቤ ሕግን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በ30,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቁና ዓቃቤ ሕግ ይግባኝ የሚል ከሆነ በማለት አሥር ቀናት ለመጠባበቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግም ይግባኙን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ‹‹ያስቀርባል›› በመባሉ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ዋስትናው መታገዱ ታውቋል፡፡

Via Reporter
@tsegabwolde @tikvahethiop
#ነቀምቴ አንድነታቸውን አጠናክረው ለአካባቢያቸው ጽዳትና ደህንነት ተግተው እንደሚሰሩ በነቀምቴ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። ብሔራዊ የጽዳት ቀን ዛሬ በነቀምቴና ቁኒ ከተሞች ተካሄዷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia