TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቀጠለ...

ኪያ፦

"ሶሻል ሚዲያው ላይ ላለው አክቲቪስት የፖለቲካ ታሪካችን ውጤት ነው ብዬ ነው ማስበው፡፡ ምን አስተዋጽዖ ማድረግ ችላሉ ለሚለው ግን ብዙ ማድረግ ይችላሉ ባይ ነኝ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸውን ለመልካም ዓላማ መጠቀም ይችላሉ፡፡ የአክቲቪስቶች ስራ ሙሉ ሰዓት መቃወም ብቻ አይመስለኝም ሀገራዊ ስራዎች ላይ ሰላም ላይ መስራት ይቻላል።"

አሁን ላይ የሚታየው የሚዲያና የአክቲቪዝም መደበላለቅ እንዴት ትመለከቱታላችሁ፦

• ሚዲያና አክቲቪዝም መለያየት ያለባቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ከአክቲቪዚሙ ይልቅ ለፖለቲካ አቋም ያላቸው አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች በዝተዋል በግሌ ይሄ መሆን አለበት ብዬ አላምንም (ታምራት )

• ፐብሊክ ሚዲያው ነጻ መሆን አለበት፡፡ የመንግስት የአቋም መግለጫ ሙሉውን የሚያነብ ሚዲያ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስብሰባ እንኳን ሳይጠቅስ ያልፋል፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ (ዶ/ር እንዳለማው)

• አሁንም ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ ሚዲያ ኖሮ አያውቅም፡፡ አሁን ላይ የሀሰት ዜናዎችን እያሰራጩ ያሉት የመንግስት ሚዲያዎች ናቸው፡፡ አሁንም ቢሆን ሶሻል ሚዲያውን እንዴት በአግባቡ መጠቀም አለብን በሚለው ላይ ተስፋ ይታየኛል፡፡ (ኤቤል)

• በተለይ ዋና ዋና አክቲቪስቶች ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ከሁሉም ክፍል ያሉ ህዝባችንን እንወክላለን ያሉ ተሰብስበው በፈቃደኝነት ተሰብስበው ለራሳቸው ህግ ቢያወጡ ጥሩ ነው፡፡ በተረፈ ግን እንደ ሀገር ያለንበትን ጉዳይ አልተረዳነውም ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ እያገናዘብን እንቀሳቀስ እንጂ በዲሞክራሲና በፕሬስ ሚዲያ ሩቅ የደረሱ ሀገሮችን እንደ ምሳሌ እየጠቀስን መነቃቀፍ የትም አያደርሰንም። (ኪያ)

• ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ብሔርና እንደ ፖለቲካ የተመሰረተ ሚዲያ እንጂ ነጻ ሚዲያ የለም፡፡ አሁን ላይ ስለ ሚዲያ ማውራት አንችልም። (አልበርቱ ቢጠና)

#ቲክቫህ
የሀሳብ ማዕድ!

ክፍል ሁለት!

አክቲቪስቶች በጋራ ሆነው የሚመሩበት ህግ በማውጣትና እርስ በእርስ መገማገሚያ መድረክ ቢያመቻቹ ጥቅሙ ምንድን ነው?

• ይህንን ማድረግ የፖለቲካ ስርዓቱ መስተካከል አለበት፡፡ ፖለቲከኞቹ ባለመግባባታቸው ህግ እየተከበረ አይደለም በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ግጭት የሚፈጥሩ ሰዎች በህግ ተጠያቂ እየሆኑ አደለም ስለዚህ መጀመሪያ ህግ መፍራት ለህግ ተገዢ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ከዛ ይልቅ ግን እንደዚህ አይነት መድረኮች መኖራቸው እርስ በዕርስ ተቀራርቦ ማውራቱ ቀዳሚ መሆን ይኖርበታል። (ዮናታን)

• አክቲቪዝሙ በራሱ በአንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ እንጂ ሌላውን ማህበረሰብ ለማካተት አይፈቅዱም፡፡ አሁን ያለው አክቲቪዝም ላይ ያሉ አክቲቪስቶች ቁጭ ብሎ ለማውራት እንኳን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡(በፍቃዱ)

• መጀመሪያ ላይ ችግሩ ላይ መስማማት ያለብን ይመስለኛል በዚህ ላይ ካልተስማማን የራሳችንን ጽንፍ ይዘን እንቀሳቀሳለን እንጂ መግባባት አንችልም፡፡ አቋም እንዳለን እንስማማ አንድ ላይ ቁጭ ብለን ስንደራደር መፍትሔ እንደምናገኝ እንመን ሁላችንም ያገባናል የምንል ከሆነ ሀሳባችንን ለድርድር ማቅረብ አለብን፡፡

• አብዛኛው ሰው ተስፋ የቆረጠ ነው፡፡ ይህ ደግሞ መሸሸጊያ ምሽግ እንዲፈልግ ያደርገዋል፡፡ እንደዚህ አይነት መድረኮች መኖሩ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋ ይሰጣል፡፡(ያሬድ ሹመቴ)

• መሰረታዊ ችግሩን ሳናወራው ስለመፍትሔ ማውራ መፍተሔ አያመጣም፡፡ የጋራ ሀገራዊ ማንነት ላይ መግባባት ያስፈልጋል፡፡ የብሔር ማንነትና ብሔራዊ ማንነትን ማስታረቅ በጣም ያስፈልጋል፡፡ ጥላቻን ማደስ ላይ ተጠምደናል፡፡ (አንሙት)

#ቲክቫህ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
የተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ መልዕክት ለወጣቶች፦

- የበላዩ የበታቹን ማወያየት አለበት፣ ማዳመጥ፣ መስማት ይገባል፡፡ ጥሩ ሀሳብ ከሆነ መከተል ነው፡፡ የበታቹ ደግሞ የበላዩን ሊያከብር ሊሰማ ይገባል፡፡ እስልምናው ይህንን ያዛል፡፡

- ጥቅም የሚገኘው ከአንድነት ነው፣ ጥቅም የሚገኘው ከሰላም ነው፣ ጥቅም የሚገኘው ከመከበር ነው፣ ጥቅም የሚገኘው ከመተባበር ከመረዳዳት ከመሰማማት ነው፡፡

- የሚጠቅመው መቀራረብ መመካከር መረዳዳት አላግባብ እንደሆነ መመለስ መጸጸት ወደፊት አንድነቱን ማጠንከር ሰላሙን ማጎልበት ማጠንከር ነው፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahetiopia @tsegabwolde
"በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘላቂ ሰላምን መገንባት!" በሚል ርዕስ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከኢንሼቲቭ አፍሪካ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው መርኃግብር ነገ በUNECA መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በኮንፍረንሱ ላይ የሁሉም የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችና የሰላም ፎረም አባላት ይገኙበታል፡፡ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦችም ባለፈው ዓመት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ባካሄዱት "የጥላቻ ንግግር እናቁም!" ዘመቻ ምክንያት በዚህ ስብሰባ ላይ የሚገኙ ይሆናል፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ምንም ሁኔታዎች ባይመቹም ከበጎነት ወደኋላ የሚመልሰን ነገር አይኖርም!

#ቅዳሜን_ደሜን_ለወገኔ

ዶ/ር ሜላት ሰለሞን እባላለሁ፡፡ እኔ O+ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሽ ነኝ። ለ9ነኛ ጊዜ ደም ለግሻለሁ። ደም በመለገስ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትማዳን እንደሚቻል ተረድቻለሁ፡፡ ደም በመለገስ የሚያገኙትን የደስታ ጥግ የትም ፣ ምንም ላይ አያገኙትም ! ደም መለገስ ከየትኛውም ደግነት፣ ከየትኛውም ሩህ ሩህነት ይልቃል፡፡ዛሬ ጥቅምት 15 በሚደረገው የደም ልገሳ ላይ ይሳተፉ!

እርሶስ ደም ለግሰዋል?

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tikvahethiopia @tsegabwolde
“ሁላችንም አንድ እንሁን፣ #ሰላም እናስፍን፣ ከእንደዚህ አይነቱና አላህ ከማይወደው ተግባር እንራቅ፣ እስላም ክርስቲያኑ ሁሉ በአንድ ሆነን አገራችንን እናልማ፣ ሰላም እንፍጠር፣ ከመተላለቅ እንዳን። እባካችሁ ሁላችንም ለአላህ ብለን ከዚህ ተግባር እንቆጠብ...ሰላም ማጣታችን ያሳዝናል። ፍቅር ማጣታችን ያሳዝናል። ኡለማዎችንን ማስለቀሳችን ያሳዝናል። አንድነት ማጣታችን ያሳዝናል። አሁን #አንድ_ሆነን_ቆራጥ ሆነን ልንነሳ ይገባል። አንድ እንሁን፤ የከተማውም የገጠሩም እስላም እና ክርስቲያኑም አንድ እንሁን። አንድ ሆነን ቆራጥ ሆነን እንነሳ። እውነቱም ይታወቃል፤ ውሸቱም ይታወቃል። ለእውነት እንድትሰሩ አሳስባለሁ። አደራም እላለሁ። አሚን።” ሀጂ ኡመር ሙፍቲ (ኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ፕሬዚዳንት )

#share #ሼር

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Vote!

ፍሬወይኒ መብራቶም የ2019 CNN Hero ምርጥ አስር ውስጥ ገብታለች፡፡ ለዚህም የበቃችው የሚታጠብና መልሶ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዲየስ) በመስራቷና ሴቶች ተማሪዎች ተፈጥሯዊ በሆነው የወር አበባ ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ በምትሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዋ ነው፡፡ እንደ ዩኒሴፍ ጥናት በኢትዮጵያ ከ10 ሴቶች አንዷ በዚህ ምክንያት ትምህርቷን ታቋርጣለች፡፡ ፍሬወይኒ ይህንን ውድድር ካሸነፈች 100,000 የአሜሪካን ዶላር አሸናፊ ትሆናለች፡፡

ምረጧት 👉 https://edition.cnn.com/SPECIALS/cnn.heroes/vote/10/

የድምጽ አሰጣጥ ሂደት:
1. ሊንኩን (ማስፈንጠሪያውን) መጫን። ከተጫን ነው ቡሃላ ውደድ የCNN የአመቱ 10 ጀግኖች ዝርዝር እንግርባለን ከዛ የፍሬወይን መብራቶም ስምችና ፎቶዋ ዜግነት Ethiopian የሚል ፈልገን እንጫናለኝ።
2. የሷን ፎቶ ከተጫንን ቡሃላ ዝቅ ብለን ከሷ ፎቶ በታች 1 or 0 ቁጥር ይኖራል vote ከሚለው በላይ slide for more ከሚለው በታች የለቸውን መሳቢያ ወደቀኝ በመሳብ 10 ድምጽ መስጠት ይችላሉ።
3. Vote የሚለውን ከተጫንን ቡሃላ email or fb account ያለን ብቻ ነው የምን መርጠው ከላይ አንብባቿል ዲስኮርሱን የሚል ሲመጣ ማንበብ ወይም አንቢብያለሁ ማለት ከዛ account ይጠይቀናል እናስገባና ማረጋገጫውን እንጫን ከዛ አበቃ።

ማሳሰቢያ:- ሁሉም ሰው በየቀኑ 10 ድምጽ መስጠት ይችላል። ማብቂያው ህዳር 21 ነው፡፡

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ(@tikvahethmagazine)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CONGRATULATIONS

በአሁን ሰዓት "ጎንደር ዩኒቨርስቲ" የህክምና ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ እያስመረቀ ይገኛል፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተማሪ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine
በዜሮ ዓመት የወጣ ክፍት የስራ ማስታወቂያ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሐብት ልማት ቢሮ ለ2010 እና 2011 ተመራቂዎች 5095 ክፍት ቦታዎችን አውጥቷል፡፡

• በ2010 እና 2011 ዓ.ም የተመረቃችሁና ከታች መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች

• አንድ ሰው መመዝገብ የሚችለው ለአንድ የስራ መደብ ብቻ ይሆናል፡፡

• የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

#ቲክቫህ_ጥቆማ
@tikvahethmagazine @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል። "በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!" "እኛ ወንድምና…
#አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት #ቲክቫህ #ፒስሞዴል

የኡቡንቱ የማጠቃለያ ፕሮግራም በሀገራችን ብሔራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የጋሞ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ እሸቱ አልቶ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በዚሁ ንግግራቸው ወቅት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሙሉ ወጣቶች መሆናቸው መርኃግብሩን ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡ አቶ እሸቱ አክለውም 500,000 ቤተሰቦችን ስለ ፍቅር እና አንድነት ብቻ እየሰበከ ላሰባሰበን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ቀጥሎም የኃይማኖት አባቶች፣የጋሞ አባቶች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ በተለይ ለወጣቱ ባስተላለፉት መልዕክት፦ እርስ በእርስ መከባበር እና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ማስቀደም እንደሚገባ አበክረው ገልፀዋል፡፡

አሁን "ስለ እርቅ ለመወያየትና ለማስታረቅ እድሜ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?" በሚል ርዕስ ወጣቱም ስለ ዕርቅ፣ ስለ ሰላም የበኩሉን እንዲወጣ በፈጣሪ አሰፋ አማካኝነት ምክክር እየተደረገ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia