TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Ministry of Agriculture ~ #አረንጓዴ_አሻራ
#MTA Law Office staff- Green Legacy
ቤንሻንጉል #አረንጓዴ_አሻራ
CBE Jimma District be Jimma Kito Furdissa #አረንጓዴ_አሻራ
Ambo Gedo Road project planted total of 8500 trees!
የአ/አ ቀቤና ወጣቶች ማህበር አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል!
የአዲ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ #አረንጓዴ_አሻራ
205,872,988👍#Done!
በ"ወገኛ ነች" "እስከመቼ" እና ሌሎችም ተወዳጅ ሙዚቃዎቹ የምታውቁት ዘሩባቤል ሞላ የመጀመሪያ አልበሙን “እንፋሎት” በቅርቡ ለህዝብ ያቀርባል፡፡

ሰኞ ሐምሌ 22 እንፋሎት በአውታር አፕሊኬሽን ላይ ለህዝብ የሚቀርብ ሲሆን: እንዲሁም ሐሙስ ሐምሌ 25 አልበሙን በመላው ኢትዮጵያ በሲዲ፣ በውጪ ሐገራት ለምትገኙ ደግሞ በሲዲ ቤቢ፣ በስፖቲፋይ፣ አፕል ሚዩዚክ፣ እና አማዞን ሚዩዚክ ላይ ያገኙታል፡፡

ለበለጠ መረጃ 👇
https://publielectoral.lat/zerubabelmolla
221,149,411👍
ከ224 ሚሊዮን በላይ!

በዛሬው ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን የዛፍ ችግኞችን ለመትከል የተያዘው ዕቅድ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በፊት መሳካቱን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመረጃው መሰረት እስከተጠቀሰው ሰዓት ድረስ ከ205 ሚሊዮን በላይ፤ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ደግሞ ከ224 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል፡፡

Via #etv
"በኃይልና በጉልበት #በአመፅና #በሁከት ሰላምን ብንፈልገውም አናገኘውም"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
.
.
በዛሬው ዕለት በወላይታ ሶዶ በመገኘት የዛፍ ችግኞችን የተከሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በከተማይቱ ስታዲየም ለተሰበሰበ በርካታ ህዝብ ንግግር አድርገዋል።

“በፍትሕና በምህረት አውድ ውለን ልናድር ካልሆነ በቀር በኃይልና በጉልበት በአመፅና በሁከት ሰላምን ብንፈልገውም አናገኘውም” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው።
“በጦርነትና ግጭት ውስጥ ስንመላለስ የምንቀማው ክብር ሕይወታችንን፣ አካላችንን፣ በድካም ያፈራነውን ሀብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን ታላቁን የሕሊና ሰላማችንንም ነው የምናጣው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከወላይታ ሶዶና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው። #PMO
“በፍትሕና በምህረት አውድ ውለን ልናድር ካልሆነ በቀር በኃይልና በጉልበት በአመፅና በሁከት ሰላምን ብንፈልገውም አናገኘውም::” - ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በወላይታ ሶዶ ታዲየም ባደረጉት ንግግር

#PMOEthiopia
“በጦርነትና ግጭት ውስጥ ስንመላለስ የምንቀማው ክብር ሕይወታችንን: አካላችንን: በድካም ያፈራነውን ሀብትና ንብረት ብቻ ሳይሆን ታላቁን የሕሊና ሰላማችንንም ነው የምናጣው::” - ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ

#PMOEthiopia
#ጎንደር

የኢፌዴሪ ኘሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጎንደር ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ጎበኙ። ፕሬዘዳንቷ የፋሲል ግንብን፣ የደብረ ብርሃን ስላሴ ቤተክርስቲያን አና ጥምቀተ ባህሩን ጎብኝተዋል። በተጨማሪም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህሙማን የተመላላሽ ህክምና አዲሱን የእናቶች እና ህፃናት ማዕከልን ጎብኝተዋል። በጎብኝቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች አመራሮች ተሳትፈዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ ወደሃዋሳ ያቀናሉ...

በሶዶ የደኢሕዴን አመራሮች ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ፣ ዶ/ር ጌታሁን ጋረደውና የዎላይታ ዞን አስተዳዳሪ ዳጋቶ ኩምቤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ነበሩ። ዶ/ር አቢይ የደኢሕዴንና የደቡብ ክልል አመራሮች ከሐሙስ ጀምሮ ወደ ተሰበሰቡበት ሐዋሳ ያቀናሉ ተብሏል።

Via Eshet Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ክብረወሰን ሰበረች!

በአለም አቀፍ ደረጃ በህንድ ተይዞ የነበረው 66 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል ክብረ ወሰን ዛሬ ኢትዮጵያ ከ234ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በሰፊ ቁጥር መስበሯ ይፋ ሆኗል።

ቢቢሲ በድረገጹ እንዳስነበበው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ በአገር አቀፍ ደረጃ በርሃማነትን ለመቀነስ ያለመ አካሄድ መሆኑን ገልጾ፤ 1 መቶ ሚሊዮን ህዝብ በነፍስ ወከፍ ቢያንሰ ሁለት ይተክላል በሚል የታሳቢ ቢሆንም ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራቸውን እዚያው በማድረግ እየተከሉ መሆናቸውን ጠቅሷል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/200M-07-29

ፎቶ፦ ከትምህርት ሚኒስቴር/TIKVAH-ETH/
#አረንጓዴ_አሻራ በሀገር ደረጃ እስካሁን በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ቀን 232 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን ያስታወቁት በወላይታ ሶዶ ከተማ ከአካባቢው የህብረተስብ ክፍሎች ጋር እየተወያዩ ባሉበት ወቅት ነው።

#አሁን በደረሰን መረጃ በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ በኦሮሚያ 132 ሚሊዮን ፣ በደቡብ 45 ሚሊዮን፣ በትግራይ ስምንት ሚሊዮን 400ሺህ አማራ 38ሚሊዮን እና አዲስ አባባ ከሶስት ሚሊዮን በላይ የተከናወኑ ይገኙበታል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ዛሬ ጥዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ለመትከል የታቀደው 200 ሚሊዮን ቢሆንም እስካሁን የተከናወነው ከዚህ በላይ መድረሱን ነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ ለማወቅ የተቻለው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አረንጓዴ_አሻራ #ከፍተኛ_ጥንቃቄ_ይደረግ

ፌስታሉን ካልሰበሰብነዉና ካላነሳነዉ ሌላ ዘመቻ ያስፈልገናል 200 ሚሊዮን ፌስታል ለመልቀም ~ የሚተክል ያስተዉል፤ ጉዳዩ ጥንቃቄ ያሻዋል!!

#ሼር #share

Via #ዝንቅ
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia