TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ቆም ብለን …

በርካታ የአለም ሀገራት የማህበራዊ ሚዲያ ቴክኖሎጂን በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና በፖለታካዊ ዘርፎች ለተጎናጸፉት ውጤት ሁነኛ መሳሪያ አድርገው እየተጠቀሙበት ነው፡፡ በተቃራኒው ከነበሩበት የእድገት ሂደት እና ከሰላማዊ ህይወት አሽቆልቁለው ማንም አካል አትራፊ ወዳልሆነበት በእርስ በርስ #ጦርነት ሀገራቸውን #አፍርሰው ለዜጎቻቸው ሞት፣ በረሀብ አለንጋ መቀጣት፣ ለወረርሽኝና  ስደት መዳረግ እጣፈንታቸው እንዲሆን የጥላቻና የሀሰት መረጃዎች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ በተለያዩ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ይፋ እየተደረገ ነው፡፡

በሚወርድባቸው የከባድ ጦር መሳሪያ ወደ ፍርስራሽነት በመቀየር ላይ ያሉትና እስካሁን #መቋጫ መፍትሄ ያላገኘው የመካከለኛው መስርቅ የቅድመ ስልጣኔ ምድር የነበረችው ሀገረ #ሶሪያን እና ለኢትዮጵያ የቅርብ ጎረቤት በሚባል አቅራቢያ የምትገኘው #የመን በምሰሌነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ኢትዮጵያም ለዜጎቿ ህይወት የሚበጁ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን ዘመኑ ከፈጠረው የማህበራዊ ሚዲያ ቴክኖሎጂ መጠቀም የምትችልበት ምቹ ሁኔታዎች እየሰፋ ቢመጡም በተቃራኒው በቴክኖሎጂው በሚሰራጩ የሀሰት ወሬዎች፣ ብሄርን ወይም  ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ የጥላቻ መረጃዎች ያለገደብ የሚለቀቅበት ሁኔታ አመዝኖ የስጋት ምንጭ  እየሆነ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያ የሆነ ቡድን ወይም አካል መነሻው ምን እንደሆነ ለማወቅ በሚያዳግት መልኩ በስሜታዊነት የሚፈረጅበት፣ የጥላቻ መረጃዎች  እየተፈበረኩ በተቀናበሩ ፎቶዎች የሚቀርብበት፣ በሀገሪቱ ለረጅም ጊዜያት ጸንተው ለነበሩ የመቻቻልና የአብሮነት እሴቶችን ለሚንዱ የጥላቻ መረጃዎች መጫዎቻ ሜዳ ሲሆን ይስተዋላል፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ባሉ የሀሰትና የጥላቻ መረጃዎች በሀሪቱ ላይ እየፈጠሩ ባለው ችግርና መፍትሄው ላይ  ውይይት ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይም ሀገራችን ከማህበራዊ ሚዲያ ምን አተረፈች? በማለት በጥያቄ ሀሳባቸውን ማካፈል የጀምሩት በቀድሞው የኢፌዲሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ  ቡድን መሪ  አቶ በቀለ እውነቱ በማህበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ መረጃዎች ለህብረተሰቡ ከሚሰጡት ጠቀሜታ ይልቅ  ጉዳቱ እየበዛ  ነው ያሉት፡፡

ለመልካም ነገር የተጠቀሙ የአለም ሀገራት ፈለግ በመከተል ቢሰራበት በርካታ  ተግባራትን  በቀላሉ ለመከውንና አማራጭ  የመሆን  አቅም ያለው  ቴክኖሎጂ ነው ያሉት አቶ በቀለ “እኛም እያደረሰ ያለውን ጉዳት በመቀነስ እውቀት ለሚጨምሩና ኑሮን ለሚያቀሉ ተግባራት ማዋል ላይ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል’’ ብለዋል፡፡

በሀገሪቱ ሚዲያውን እየተጠቀመ ያለው ቢያንስ መጻፍና ማንበብ የሚችል የህብረተሰብ ክፍል ነው የሚሉት ባለሙያው መረጃን በመመልከትም ሆነ ሀሳቡን  ተቃውሞና ደግፎ የሚሳተፈው አካል ለበጎ ተግባር የመጠቀም ሂደት ገና አልዳበረም በማለትም  ትዝብታቸውን ገልጸዋል፡፡

በማህበራዊ ገጾች የሚተላለፉ መረጃዎችን የማመዛዘን አቅም ማዳበር ይጠይቃል  የሚሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አቢዮት ባዬ፤ በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 17 ሚሊዮን ባላይ መድረሱንም ጠቁመዋል፡፡

ቀደም ሲል ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ባለመረጋገጡ ሰዎች በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ባህል እንዲዳብርና መብት እንዲከበር ማንነታቸውን በመደበቅ በስውር የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከፍተው ለዴሞክራሲ መጎልበት የሚሰሩበት ወቅት እንደነበር ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

ከሞላ ጎደል ነገሮች በተስተካከሉበት በአሁኑ ወቅት ሀሳብን በነጻነት ለመግልጽ ምቹ በሆነት ዘመን በተቃራኒው ሀሰተኛ መረጃዎችን አቀናብሮ በማሰራጨት ዴሞክራሲን የሚያቀጭጭ፣ ብሄርን ከብሄር ወይም በሃይማኖቶች መካካል ቅራኔና ግጭት ለመፍጠር እየተሰራ ይታያል ይላሉ። ለሀገር ሰላምና አንድነትም ስጋት እየሆነ ይገኛል ነው ብለዋል፡፡

ሀሰተኛ ወሬዎችን እያጋነነ የሚያሰራጨው አካል ምን ፍላጎት ቢኖረው ነው? ለምን ይነግረኛል? ብሎ እራስን በመጠይቅና መረጃውን ከሌሎች ታማኝ ምንጮች በማጣራት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ነው ዶከትር አቢዮት  የገለጹት፡፡

የጥላቻ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት አላማቸው ለበርካታ የቴክኖሎጂው ተጠቃሚዎች መልእከታቸውን መበተን በመሆኑ ሀሳቡን ደግፎ ወይም ተቃውሞ ምላሽ ባለመስጠት የድርጊቱ ፈጻሚዎችን አንድም እራሳቸውን ከሀሰት መረጃ እንዲያርሙ ወይም የተከታይነት ተጽኖ ማመናመን እንደሚገባም ባለሙያው መክረዋል፡፡

በሌላ ሰው ወይም ተቋም ስም ሀሰተኛ የማህበራዊ ገጽ በመክፈት የፈጠራ ወሬን ተዓማኒነት በሌላቸው ፎቶዎች በማቀናበር ሀገርንና ዜጎችን አደጋ ላይ የሚጥል መረጃዎችን የሚያስተላልፉ አካላትን ለማስቆም እንደሀገር ቆም ብለን ማሰብ አያስፍልገንም? በማለት ሀሳባቸውን በጥያቄ ያነሱት የሀይማኖት አባት ሀጂተሸለ ኪሮ እንዳሉት ወጣቱ ትውልድ የሀገሩን አንድነትና ሰላም አስጠብቆ ማስቀጠል አለበት ፡፡

“ማህበራዊ ሚዲያ በብሄሮችና በሃይማኖቶች መካካል የጥላቻ ወሬ መርጨት  ብቻ አይደለም” የሚሉት ሌላው  የሃይማኖት አባት አባ መላከሂወት ወልደየሱስ  በአንድ ቤተ እምነት ውስጥ ጭምር የአሉባልታና የሀሰት መረጃዎችን በማሰራጨት የመተማመንና የመከባበር  ባህልን እየሸረሸረ ነው ብለዋል፡፡

በርካታ የመረጃ አማራጮች መኖር መልካም አጋጣሚ መሆኑን የነገሩን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት መምህር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ፤ መረጃዎች ሁሉ እውነተኛና ጠቃሚ ባለመሆናቸው ተፈትሸውና ተለይተው መወሰድ እዳለባቸው ይመክራሉ፡፡

“በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ የሚቀርቡ መረጃዎች፤ የበሰለ የፖለቲካ ሀሰብን ከማቅረብ ይልቅ የአንድ ግለሰብን ወይም ቡድንን ስሜትና የጥላቻ መረጃ የሚቀርቡበት ሜዳ ሆኗል” የሚሉት ዶክተር ጌታቸው ህብረተሰቡ ስጋቱን እየተረዳው መምጣቱን ነው የተናገሩት።

መደበኛ የመገናኛ ብዙሃን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መሻሻሎችና አማራጭ የህዝብ የመረጃ ምንጭ እየሆነ ቢመጣም ለበርካታ አመታት “ለገዢው ሃይል  የሚዘምር” ነበር ይላሉ።

ዶክተር ጌታቸው እንደሚሉት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለህብረተሰቡ የማስተማር፤ በቁጥር እያደገ በመጣው የኤፍ ኤምና ቴሌቭዥን መገናኛ ዘዴዎች መንግስት መረጃዎችን በፍጥነት መስጠትን በመፍትሄነት መጠቀም ግድ ይላል። ማንነቱን ያልገለጸ አካልን ጓደኛ ማድረግም ሆን መከትል እንደማያስፍልግም በማስረዳት፡፡

የድሬ ትዩብ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም ነገሰ  ፌስ ቡክ የመጠቀሚያ ቴክኖሎጂውን በየጊዜው ይበልጥ ቀላልና ባለብዙ አማራጭ እያደረገው መምጣቱ በሀገሪቱ እየመጣ ያለውን አደጋ ያባብሰዋል የሚል ስጋት ነው ብለዋል።

አቶ ቢኒያም  “በድሬ ትዩብ ስም በተከፈት የሀሰተኛ  ገጽ ላይ በተለቀቀ የአንድ ድርጅት ስም ማጥፋት መረጃ እኛን ጥፋተኛ ሊያደርግ የነበረን ድርጊት የፌስቡክ ባለቤት ጋር በአካል በመሄድ ሀሰተኛ መሆኑን በማስረዳት የኛን ትክክለኛ ገጽ በማረጋገጥ ከችግሩ ዳን” በማለት በተሞክሮነት አንስተዋል፡፡

አሁን በሀገሪቱ  በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ የሚስተዋለውን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት ጥናት ላይ የተመሰረትና ቴክኖሎጂውን በአግባቡ በመጠቀም ብሎም ውጤት ካስመዘገቡ  ሀገራ ተሞክሮ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት፡፡

የጥላቻ ሀሳቦችን የሚያንጸባርቁ  ገጾችን የሚከላከል አንድ ተቋም በማቋቋምና በቂ እውቀት ያላቸው ባለሞያዎችን መድቦ መስራት ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ፌስቡክ በአፍሪካ ያለውን አገልግሎት
"ለኢትዮጵያውያን #ከሶሪያ የተላኩ መልእክተኞች"!

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሶሪያ ስደተኞች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ #ምፅዋት ሲለምኑ የሚያሳይ ምስል በብዛት እየተሰራጨና share እየተደረገ ይገኛል።

አዎን ቢገባን ብናስተውለው እነዚህ ሶሪያኖች እኛ ሐገር የተላኩት ከፈጣሪ መልእክተኛ ሆነው ነው። አሁንም ልብ ካልገዛን፣ ጥላቻን ትተን ይቅርታን ካልተላበስን፣ መለያዬትን ትተን አንድነትን ካልያዝን፣ የጦርነት አታሞ/ ከበሮ መደለቅ ካላቆምን እንደ እነዚህ ሶሪያኖች ትሆናላችሁ ተጠንቀቁ ሲል ነው የላከልን፤ ከእንግዲህ መለያየትን፣ ዘረኝነትን የምትሰብኩ የጦርነት ነጋሪን የምትጎስሙ #ጦርነት ናፋቂዎችና እነሱን ተከትላችሁ የምታብዱ ተከታዮቻቸው ፈጣሪ ከዚህ በላይ ወርዶ አይነግራችሁምና ልብ ግዙ።

አንደበታችሁ ሰላምን ያውራ፣ እግራችሁ ወደ ጥፋት ሳይሆን ወደ ሰላም መንገድ ያቅኑ፣ እጆቻችሁ የመሳሪያ ቃታን ሳይሆን በሐሳብ የምታሸንፉበት እስክርቢቶን ይያዙ። ኢትዮጵያ ፈርሳ ላትፈርስ ተለያይተን ላንለያይ ትዝብት ላይ አትውደቁ። ጉልበታችሁንም አትጨርሱ።

©Kibrom Adhanom Ghebreyesus
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይሄ ፊልም አይደለም!! የግጭት እና የጦርነት ውጤት መሬት ላይ ያለው እውነታ ነው!! ጦርነት እና ግጭት #ፌስቡክ ላይ #ተዘፍዝፎ እንደመለፍለፍ ቀላል ከመሰለህ ሶሪያ፣ የመን፣ ደቡብ ሱዳን ጎራ በል በጥይት ድምፅ ስትሳቀቅ፤ ያቀረብከውን ምግብ ለመብላት ሲያቅትህ፤ ብር ኖሮህ ምግብ ለመግዛት ከቤትህ ለመውጣት ሲከብድህ፤ መብራቱና ኔትዎርኩ ተቋርጦ ጨለማ ውስጥ ስትቀመጥ ያኔ #ግጭት እና #ጦርነት ትርፉ ምን እንደሆነ ይገባሃል!!
.
.
#ሰላም_ብቻዋን_ታዋጣለች!!
#TIKVAHETHIOPIA #ቲክቫህኢትዮጵያ

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፈጣሪ ያውቃል⁉️

በረሐ እና ባሕር አቋርጠው ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚተሙት ኢትዮጵያውያን በየመን ጦርነት እንዳለ እንኳ አያውቁም። አንድ ወደ #ጅቡቲ የተሰደደ #የመናዊ በመንገድ ያገኟቸውን ኢትዮጵያውያን «ወዴት ነው የምትሔዱት? በመንገዳችሁ ጦርነት አለ ስንላቸው ፈጣሪ ያውቃል» የሚል መልስ ሰጡን ሲል ለኢኤንኤን ተናግሯል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ድረ-ገፅ እደሚጠቁመው በየመን የርስ በርስ #ጦርነት

•5,900+ ሰላማዊ ሰዎች #ተገድለዋል

•9,400+ ሰላማዊ ሰዎች #ቆስለዋል

•3 ሚሊዮን ከመኖሪያ ቀያቸው #ተፈናቅለዋል

•22.2 ሚሊዮን ሕይወታቸውን ለማቆየት የለት ደራሽ ዕርዳታ #ጥገኛ ናቸው

•2.5 ሚሊዮን ሕፃናት ከትምህርት ገበታ እርቀዋል፤ ቢሆንም #ኢትዮጵያውያኑ ፈጣሪ ያውቃል እያሉ መንገድ ላይ ናቸው።

Via Eshet Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌስቡክ ጦረኞች...

#የቃላት_ጦርነትና እስጥ አገባ ከሮና ገሮ ሲያበቃና ሲበጠስ ነው ሀገራት ወደ #ጦርነት ውስጥ የሚገቡት፡፡ ለዚህም ይመስላል የቻይናው ከሚኒስት መሪ የነበሩት ማኦ ዜዱንግ ጦርነት የፖለቲካ ትግሉ በሌላ መልኩ ቀጣይነት ነው ያሉት፡፡ ማሕበራዊ ድረገጾች ከፍተኛ የኃሳብ ፍልሚያ የሚካሄድባቸው ከጦርነት ያልተናነሱ አውድማዎች ናቸው፡፡ የማሕበራዊው ሚዲያ ጥይት ባይጮህበትም ከመድፍና ታንክ በላይ #በሰው_ሕሊና ውስጥ የሚያጓራ ከሚሳኤልም በላይ ተምዘግዝጎ የሚወነጨፍ፣ የሚጮህና አናዋጭ፤ በስሜታዊነት የሚነዳ ለጥፋትም የሚያነሳሳ ነው፡፡ #ፌስቡክ የኃሳብ ፍልሚያና ግብግብ የሚካሄድበት ጎራ መሆኑ በጀ እንጂ ሌላማ ቢሆን የከፋ እልቂትና ውድመት ሊያመጣ ይችል የነበረ የዘመኑ ሚዲያ ነው፡፡

ሙሉውን ፅሁፍ ያንብቡ👇

https://telegra.ph/የፌስቡክ-ጦረኞች-03-04
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግልፅ የሆነ ጦርነት ውስጥ እንገባለን...

"....ሳታሸንፍ አሁን ባላደራ፤ ባደራ እንደሚባለው አይነት ጨዋታ ምትጫወት ከሆነ ግን ግልፅ የሆነ #ጦርነት ውስጥ እንገባለን ማለት ነው። ምክንያቱም... ለምሳሌ አዲስ አበባ የሆነ ሺ ሰው ሰብስቦ ባላደራ ካለ፤ ኦሮሚያም ይሄ ኦዲፒ የሚባል የኛ መንግስት አይደለም፤ ፍላጎቻችን ይሄ አይደለም ባለዳራ ነው #ተገንጥለናል ካለ ኢትዮጵያ አትኖርም፤ እንደዚህ አይነት ድራማ አያስፈልገንም።
.
.
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከየትኛውም ብሄር ብትሆኑ አሁን ያለው መንግስት መልካም ሲሰራ ደግፉት፤ መልካም ነገር ካልሰራ ንቀፉት፤ ነቅፋችሁ ማረም ካልቻለ በድምፅ በምርጫ ጣሉት፤ ከዛ ውጭ ያለ ድራማ ተገቢ አይደለም፤ #ወደማንፈልገው ነገር ያስገባናል ፕላስ የአዲስ አበባ ሰላምና ነፃነት ኦሮሚያ ሰላም ከሆነች፤ አማራም ሰላም ከሆነ፤ ደቡብ ...ትግራይም ሰላም ከሆነ ነው እንጂ አዲስ አበባ ብቻዋን የሆነ አምባሳደር ሹማ የሰላም ባለቤት መሆን አትችልም!" ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በመጨረሻም መልዕክት ለቲክቫህ አባላት፦

#FightCOVID19

እያንዳንዳችን #ጦርነት ላይ እንደሆንን አምነን መቀበል ይኖርብናል። መዘናጋት የህይወት ዋጋ ነው የሚያስከፍለን። የኛ ጤና መሆን የምንወዳቸው፣ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ሁሉ ጤና መሆን ነው። የምናደርገውን በመጠንቀቅ እናድርግ። በጤና ባለሞያዎች የሚሰጠውንም ትዕዛዝ እናክብር!

ኮሮና ቫይረስ እስካሁን መድሃኒት አልተገኘለትምና በተሳሳቱ አረዳዶች ተዘናግተን ጦርነቱን እንዳንሸነፍ፣ እጃችንንም ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] እንዳንሰጥ አደራ! አደራ!

መንግስት ለህዝብ የሚሰጣቸው መረጃዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ እናስገነዝባለን። የሚሰጡት መረጃዎችም ወቅታቸውን የጠበቁ ቢሆን መልካም ነው።

ጦርነቱን ከፊት ሆነው ህይወታቸውን ሰጥተው የሚመሩት፣ የሚታገሉና የሚያታግሉት የጤና ባለሞያዎቻችን አስፈላጊው ሁሉ የህክምና ቁሳቁሶች እንዲሟላላቸው ካልተደረገ እጅግ በጣም ከፍተኛ ዋጋ መክፈላችን አይቀርምና ይታሰብበት!

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት፦

"ከምንም ነገር በላይ ኮቪድ-19ኝን ለመግታት የሚደረገውን #ጦርነት ከፊት ሆነው ለሚመሩት የጤና ባለሞያዎቻችን በቂ የህክምና ቁሳቁስ ካልተሟላ የሚከፈለው ዋጋ ከባድ ነው። በተለይ ደግሞ ከከተማ ውጭ ያሉ የጤና ባለሞያዎች ሁኔታ በእጅጉ ያሳስበናል።"

#FightCOVID19
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአፋር ክልል "ህወሓት" ጦርነት ከፈተብኝ አለ። የአፋር ክልላዊ መንግስት ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው 'ህወሓት' ፥ "የሽብር ድርጊቱን ወደ አፋር በማስፋት የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል" ሲል ገልጿል። ክልሉ "ህወሓት" ጦርነት ከፈተብኝ ያለው በፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ነው። አፋር ክልል በመግለጫው ላይ ፥…
#Afar

ትላንት የአፋር ክልላዊ መንግስት በህ/ተ/ምክር ቤት ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው 'ህወሓት'፥ "የሽብር ድርጊቱን ወደ አፋር በማስፋት የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ #ጦርነት ከፍቷል" ማለቱ ይታወሳል።

ክልሉ 'ህወሓት' ጦርነት ከፈተብኝ ያለው ፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ነው ፤ የክልሉ መንግስት የተከፈተበትን ጦርነት ከህዝብ ጋር በመተባበር እንደሚመክት መግለፁ አይዘነጋም።

የአፋር ክልል ሰላም እና አስተዳደር ቢሮም ትላንት ጧቱ 2 ሰአት ጀምሮ "ህወሓት" በያሎ ወረዳ በንጹሃን አርብቶአደሮች ላይ በከፈተዉ ድንገተኛ ጥቃት በሰዉና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ሪፖርት አድርጓል።

ቢሮው፥ ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ አርብቶ አደሮች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ያሳወቀ ሲሆን ቡድኑ የተለያዩ የግለሰብ ቤቶችን ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን ገልጿል።

ህወሓት የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ ወደስፋራዉ የደረሰዉ የአፋር ልዩ ሃይልና የአካባቢዉ ህብረተሰብ የመከላከል እርምጃዎችን በመውሰድ የቡድኑን አላማ ማክሸፍ መቻሉን አስረድቷል።

'ህወሓት' በአፋር ክልል በከፈተው ጥቃት ወደክልሉ ይጓጓዝ የነበረው የሰብዓዊ ድጋፍ ተስተጓጉሏል።

የህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ብሎ የፈረጀው 'ህወሓት' አፋር ውስጥ ጥቃት መፈፀሙን አምኗል። ቡድኑ ጥቃት ፈፅመኩኝ ያለው የመንግሥት ደጋፊ ወታደሮች ላይ ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለAFP በሰጡት ቃል አፋር ክልል ውስጥ ጥቃት መፈፀማቸውን ገልፀው ጥቃቱ "ውስን ርምጃ ነበር" ብለዋል።

ጥቃቱ ያነጣጠረው በትግራይ እና አፋር ድንበር አካባቢ ተሰባስበው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ላይ ነበር ያሉት አቶ ጌታቸው፥ "ርምጃውን የወሰድነው እነዚህን ሃይሎች ወደ ኦሮሚያ እንዲመለሱ ለማድረግ ነበር፤ ይህም ተሳክቶልናል" ብለዋል።

telegra.ph/Afar-07-18

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጎረቤት ሱዳኖች የጦርነት ጉሰማ ላይ ናቸው ! የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር መጎብኛታቸው ተነግሯል። ቡርሀን ትንሹ ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙት አል ዑስራ እና ዋድ ኮሊ አካባቢዎች የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር ነው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ/ም የጎበኙት፡፡…
#Update

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር እየተካሄደ ያለው ምንድን ነው ?

በምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጨሆ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደሳለኝ አያና ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት የሰጡት ቃል ፦

- የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያ በኩል ያሉ የድንበር አካባቢዎችን በከባድ መሳሪያ ደብድቧል። ድብደባው ለቀናት የዘለቀ ነው። እስከ ትላንት ማክሰኞ ከሰዓት ድረስ ሲደበድቡ ነበር።

- ነዋሪዎች ግጭቱ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። አንዳንዶችም በአቅራቢያ ወዳሉ አካባቢዎች የመሄድ ሃሳብ አላቸው።

- ባለፉት ሶስት ቀናት በተፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት #በሰው_ላይ_ጉዳት_አልደረሰም። የከባድ መሳሪያዎቹ በእርሻ ቦታዎችና የግብርና ካምፖች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

- በሱዳን የከባድ መሳሪያ ጥቃት ምክንያት ነዋሪዎች ባለፉት ቀናት በእርሻ ማሳቸው ላይ የተለመደውን የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ከማከናወን ተቆጥበዋል።

- የንግድና የሥራ እንቅስቃሴ ተስተጓግሏል። ሱዳንና ኢትዮጵያ የሚገናኙበት የድንበር ከተማ የሆነችው የገለባት መተላለፊያ #ተዘግቷል

- የሱዳን ክስን ተከትሎ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በሁለቱ አገራት ወታደሮች መካከል ከሰኞ ወዲህ #ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን ሲዘግቡ የቆዩ ቢሆንም በአካባቢው ጦርነት አልተካሄደም፤ ያለው ሁኔታ ከሱዳን በኩል የሚፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ነው።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-06-29-2

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በደቡብ አፍሪካ ፤ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስትን ወልክለው ፊርማቸውን ያኖሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዛሬው የናይሮቢው ስምምነት በኃላ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር። አምባሳደር ሬድዋን ፤ ከዛሬው የቀጠለ ውይይት (በወታደራዊ ኃላፊዎች መካከል) የዛሬ ወር ገደማ (mid-December) በትግራይ ክልል መዲና #መቐለ ላይ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል። ዋናውና የውይይቶቹ ፍፃሜ…
#Update

በኬንያ ናይሮቢ ከህወሓት አመራሮች ጋር ውይይት ላይ የቆየው እና በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራው የመንግስት ልዑክ ዛሬ አዲስ አበባ ገብቷል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ወደ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃል ተከታዩን ብለዋል ፦

- የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የተፈራረመውን የሰላም ስምምነት ለመተግበር ቁርጠኛ ነው።

- ለሰላም እና ለህዝቡ ስንል የተፈራረምንባትን #እንፈፅማለን ፣ ለተግባራዊነቱም #እንታገላለን

- በውይይቱ በተሻለ ሁኔታ መግባባት ላይ ተደርሷል።

- ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ ኢትዮጵያ ብዙ ፈተናዎች ተፈትናለች ፤ ተገድዳ ወደ ጦርነት ገብታለች ፤ በተደረገው ውግያም በርካታ ውድመቶች ደርሰዋል።

- በርካታ የሰላም አማራጮች አምልጠዋል ፤ ከቅርብ ታሪኮቻችንን ተጠቅመን ወደ ቀደመ ሰላማችን ለመመለስ ዛሬ የተገኘውን የሰላም ንግግር ወደ ተግባር ለማውረድ ትልቅ ጥረት እየተደረገ ነው።

- ከዚህ በኋላ ይህን #ጦርነት ለመሸከም እንደ ኢትዮጵያ ማንም ጫንቃ የለም።

- የተበላሹ ነገሮች ወደ ነበሩበት እንዲመጡ መሠረት የጣለው የፕሪቶሪያው ስምምነት እና በናይሮቢ የተደረሰው ስምምነት የጋራ መግባባትን እንዲፈጠር ያደረገ ነው።

Credit : ኤፍቢሲ እና ኢብኮ

@tikvahethiopia
#አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መግለጫ አውጥቶ ነበር።

አብን በዚህ መግለጫው ፤ በየትኛውም አሰላለፍ እና አግባብ ስለአማራ ህዝብ የተሰለፉ ሀይሎች #ጦርነት ዘላቂ ጥቅምን ለማረጋገጥ አስቻይ እንዳልሆነ ሊገነዘቡት ይገባል ብሏል።

ይልቁን ጦርነት ህዝብን ለተደራራቢ የማህበራዊ ፣ ሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ድቀት ስለሚዳርግ ለሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄዎች ተገቢውን ስፍራ ሰጥተው ለክልሉ ሰላም መመለስ  ድርሻቸውን እንዲወጡ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

" የአማራ ህዝብ ከሌላው የሀገሪቱ ህዝብ ጋር ያለውን የወንድማማችነት እሴቶች ከሚንዱ ቅስቀሳዎች ፣ በራሱ እና በልጆቹ የተመሰረቱ ተቋማትን በተለይም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከሚያጠለሹ መልዕክቶች እንዲሁም የአማራ ህዝብ ማህበራዊ ረፍት እንዲያጣ ከሚመኙ አካላት በስልት የሚሰጡትን አጀንዳዎች በመጸየፍ ወደ ሰላም መድረክ የሚያመሩ መንገዶችን ሁሉ ለመጥረግ አቅሙ የፈቀደውን ርብርብ እንዲያደርግ " ሲል አብን አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#አሜሪካ

" የዋሽንግተን አጠቃላይ የመሳሪያ ሽያጭ መጠን 238 ቢሊየን ዶላር ደርሷል " ተባለ።

አሜሪካ በፈረንጆቹ 2023 ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሽያጭ አስመዝግባለች።

" የዋሽንግተን አጠቃላይ የመሳሪያ ሽያጭ መጠን 238 ቢሊየን ዶላር ደርሷል " የተባለ ሲሆን፤  ይህም በ2022 ከነበረው የ50 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ተመላክቷል።

ለሽያጩ መጨመር የሩሲያ ዩክሬን #ጦርነት ከፍተኛ ድርሻ አለው የተባለ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ የአሜሪካ መከላከያ ኩባንያዎች ለውጭ ሀገራት በቀጥታ ያደረጉት ሽያጭ እንደሆነ ነው።

ፖላንድ የአሜሪካን የጦር መሳሪያ በመግዛት ቀዳሚ ሀገር እንደሆነች ለተቀናጀ የአየር እና የሚሳኤል መከላከያ የውጊያ ትዕዛዝ ስርዓትም 4 ቢሊየን ዶላር ማውጣቷ ተመላክቷል።

"አሜሪካ ለውጭ ያቀረበችው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ባለፈው ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ሲል ፖለቲኮ ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን በዚህ ይከታተሉ ፦ https://publielectoral.lat/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@ThiqaMediaEth
ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ዘማሪው ወደ መንፈሳዊው ህይወት ሳይገባ በፊት ለረጅም ዓመታት ዘፋኝ የነበረ ሲሆን በሙዚቃ አድማጮች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆኑ ስራዎች ነበሩት።

ሙሉቀን መለሰ የዘፈንን ህይወት እርግፍ አድርጎ ከተወ እና ዘማሪ ከሆነ በኃላ የተለያዩ የመዝሙር ስራዎችን ለወንጌል አማኞች አቅርቧል።

ዘማሪው ከሀገር ወጥቶ አሜሪካ መኖር ከጀመረ ረጅም ዓመታት ያለፈው ሲሆን በዛው ባለበት ሀገር አሜሪካ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

ከዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ስራዎች አንዱ ፦

ኢትዮጵያ !

" ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያ ፈጥነሽ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ፤
በመከራሽ ዘመን የሚረዳሽ አምላክሽ ነውና ወደእርሱ ተጠጊ።

አድገዋል አውቀዋል ያልሻቸው #ልጆችሽ
ሁሉም እሾህ ሆነው እየወጉ #አደሙሽ
የአንድነት ማሰሪያው መቀነት ይኑርሽ ይኑርሽ፤
እግዚአብሔር ነይ ይላል ወደእሱ ተመለሽ።

#ጦርነት #ረሃብ #ስደት ደርሶብሻል፤
ችግር በየፈርጁ ተፈራርቆብሻል፤
በመከራሽ ብዛት የአፍረት ማቅ ለብሰሻል፤
የሚታደግ አዳኝ ኃያል ብሩት አጥተሻል።

ኢትዮጵያ ፈጥነሽ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ፤
በመከራሽ ዘመን የሚረዳሽ አምላክሽ ነውና ወደእርሱ ተጠጊ። "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#Sudan #Ethiopia

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ ሱዳን ከኢትዮጵያ በቀን የምትወስደው የኤሌክትሪክ ኃይል ከ200 ሜጋዋት ወደ 50 ሜጋዋት መውረዱን ገለጸ።

በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትወስደው የኤሌክትሩክ ኃይል በእጅጉ መቀነሱን ተነግሯል፡፡

ሱዳን #ጦርነት_ውስጥ_ከመግባቷ_በፊት ከኢትዮጵያ የምትገዛው የኤሌክትሪክ ኃይል በቀን እስከ 200 ሜጋዋት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን 50 ሜጋዋት እና ከዚያ በታች ሆኗል ሲል አገልግሎቱ አስረድቷል፡፡

ለሱዳን የሚቀርበው ኃይል ከመውረዱም በላይ " ለተጠቀሙት የኤሌክትሪክ ኃይል እየከፈሉ አይደለም " ብሏል።

በታሰረው ውል መሰረት #ለተጠቀሙበት_ካልከፈሉ አገልግሎቱን ማቋረጥ የሚቻል ቢሆንም ግንኙነቱ እንዳይሻክር ኢትዮጵያ ይህንን አላደረገችም ሲል ገልጿል።

ኢትዮጵያ ከሱዳን ከጅቡቲ እና ከኬኒያ የኃይል ትስስር ያላት ሲሆን በቀን እስከ ሁለት ቴራ ዋት ሀወር ለሶስቱ ሀገራት ኃይል እንምድታቀርብ ተነግሯል።

ጅቡቲ የምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል አብዛኛው ከኢትዮጵያ የሚሄድ ሲሆን ኬኒያም ከምትጠቀመው የኤሌክትሪክ ኃይል 10 ከመቶ ከኢትዮጵያ የሚሄድ ነው ተብሏል፡፡

#ShegerFM

#Sudan #Ethiopia

@tikvahethiopia