TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው 31 ቁጥር ማዞሪያ አካባቢ ዛሬ ጠዋት በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ  ስድስቱ ደግሞ  የአካል ጉዳት ደረሰባቸው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢዜአ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ተሳፋሪ ጭኖ ከቁስቋም ወደሽሮሜዳ ሲጓዝ የነበረ ሰሌዳ ቁጥሩ 10633 ኮድ አንድ የሆነ ሚኒባስ ታክሲ አቅጣጫውን ስቶ ከኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ምሶሶ ጋር በመጋጨቱ ነው።

በአደጋው ሁለት ተሳፋሪዎች #ሞተዋል፤ ጉዳት ከደረሰባቸው ስድስት ሰዎች መካከልም ሁለቱ በከባድ መጎዳታቸውም  ተመልክቷል። 

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። 

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነም የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል።

በአደጋው የሞቱት ሴቶች ሲሆኑ የተጎዱት ደግሞ ወንዶች መሆናቸውን ነው ኢንስፔክተር ማርቆስ የጠቀሱት። 

በአደጋው መስተዋቱን ጨምሮ #የተሽከርካሪው አካል መጎዳቱን በቦታው የተገኘው የኢዜአ ሪፖርተር ተመልክቷል።

የዓይን እማኞች እንደገለፁት አደጋው በተሽከርካሪው ፍሬን ችግር የተከሰተ ነው።

በታክሲው ተሳፍረው ሲጓዙ የነበሩት አቶ አንዷለም ለማ እንዳሉት በጠዋት ወደ ቢሮ ለመሄድ በጉዞ ላይ እያሉ አንዲት ተሳፋሪ መውረጃዋ ደርሶ “ወራጅ” ብትልም ታክሲው ሊቆም አልቻለም።

“ከዚያም ከደቂቃዎች ልዩነት በኋላ የታክሲው ረዳት ሰዎችን ከመንገዱ ዞር እንዲሉ ማስጠንቀቅ ጀመረ፤ ሹፌሩም የመኪናውን መሪ ይዞ ሲታገል ነበር “ያሉት አቶ አንዷለም ከዛ በኃላ መኪናው ተጋጭቶ ሲቆምና ከመኪናው ውጪም የተጎዳ ሰው ማየታቸውን ያስታውሳሉ።

ተሳፋሪው ከተረጋጋ በኃላ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን እንደሰሙም አክለዋል።

አሽከርካሪዎች ሲጓዙ የቴክኒክ ፍተሻ በማድረግ ራሳቸውንና ኀብረተሰቡን ከአደጋ መጠበቅ እንዳለባቸውም አቶ አንዷለም መልዕክት አስተላልፈዋል። 

ምንጭ፦ ኢዜአ
ፎቶ፦NTU(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ይርጋለም #ሞረቾ #አገረሰላም~የፀጥታ ሁኔታ!

ትናንት ግጭት እና ተቃውሞ በታየባት ሐዋሳ ከተማ ዛሬ አንፃራዊ መረጋጋት እንደሚታይ የጀርመን ራድዮ ገለፀ። የጀርመን ራድዮ ዘጋቢ እንደገለፀዉ ከሐዋሳ ውጪ በሞሮቾ፣ ይርጋለም እና አገረሰላም በተባሉት ከተሞች #አሁንም ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች እንዳሉ የዓይን እማኞች ሰቅሶ ዘግቧል። በሞሮቾ የሚገኝ አንድ የዓይን እማኝ እንዳለው ወጣቶች ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በነበራቸው ግጭት «የሚያውቃቸው ወጣቶች #ሞተዋል። መንገዶች በትላልቅ ድንጋዮች #ተዘግተዋል። ከሐዋሳ በዲላ በኩል ወደ ሞያሌ እና ኬንያ የሚወስደውም መንገድ ተዘግቷል።» አገረሠላም የሚገኙ የዓይን እማኞች እንደገለፁት ደግሞ «ትናንትና ሰዎች ሞተዋል። ወጣቶች ቤት #አቃጥለዋል።» በከተማዋ የመከላከያ ሰራዊት የገባ ሲሆን ዛሬ ላይ መጠነኛ መረጋጋት ይታያል። «ሆኖም ከተማዋ ውስጥ ዛሬም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል።» የሲዳማ ዞን ፖሊስ በሐዋሳ አጎራባች አካባቢዎች አሁንም አለመረጋጋት መኖሩን ለ ጀርመን ራድዮ አረጋግጧል። በሲዳማ በተለያዩ አካባቢዎች የታዩትን አለመረጋጋቶች ተከትሎ ደረሰ ስለተባለዉ ጉዳት ግን ፖሊስ መረጃ በማሰባሰብ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
" የችግሩ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ ነው "

በአማራ ክልል ፣ በሰሜን ጎንደር 202 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

በዞኑ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺ ዜጎች መጎዳታቸው ተገልጿል።

የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ይፋ እንዳደረገው ፤ በዞኑ ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺህ ዜጎች ተጎድተዋል፤ 202 ሺህ ዜጎችም አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ከፅህፈት ቤቱ በተገኘው መረጃ ፦

- ጃናሞራ ፣ ጠለምት ፣ የበየዳ ወረዳዎችን ጨምሮ፣ ምሥራቅና ምዕራብ ጠለምትና የተወሰኑ የደባርቅ አካባቢዎች በድርቅ ተጎድተዋል፡፡

- ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ሳቢያ 6 ወረዳዎች ለድርቅ ተጋልጠዋል።

- በድርቁ ሳቢያ 19 ሺህ 500 ሄክታር ሰብል ጉዳት ደርሶበታል።

- በዝናብ እጥረት 103 ሺሕ እንስሳት ለድርቅ አደጋ የተጋለጡ ሲሆን 53 ሺሕ የሚደርሱ እንስሳት በድርቁ ሳቢያ #ሞተዋል

- በጠለምትና ጃናሞራ ወረዳዎች በድርቁ ምክንያት ከ4 ሺሕ በላይ ዜጎች ከአካባቢያቸው ለቀው ወደ ወረዳ ማዕከላት ሄደዋል።

- ዞኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ለማቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡

- በድርቁ አካባቢዎች ላይ ተላላፊ በሽታዎች በተለይም #የኮሌራ_በሽታ ተከስቷል።

- ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ ለሚገኙ ዜጎች አስቸኳይ የዕለት ምግብ፣ መድኃኒቶች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ውሃና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አስፈላጊ ነው።

- የችግሩ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ ነው። በድርቁ ሳቢያ ዜጎች ለከፋ ችግር እየተጋለጡ በመሆኑ ሁሉም አካላት እንዲረባረቡ ፤ መንግሥት፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ አጋር አካላት የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያቀርቡ መልዕክት ተላልፏል።

እስካሁን ምን ድጋፍ ተደረገ ? ፅ/ቤቱ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ክልሉ ከአንድ ሺሕ 500 ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ ማድረጉንና ድጋፉን 14 ሺሕ ዜጎች ማድረስ እንደተቻለ ገልጿል።

Via EPA

@tikvahethiopia
#ናይጄሪያ

ናይጄሪያ ውስጥ አንድ ባለሃብት ገንዘብ ለማደል በጠራበት ዝግጅት ላይ በተፈጠረ ግርግር አንዲት የ8 ዓመት ሕፃንን ጨምሮ 7 ሰዎች ተረጋግጠው እንደ #ሞቱ ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ትላንትና እሁድ አልሃጂ ያኩቡ የተባለ ባለሀብት በሰሜን ምሥራቅ የባውቺ ግዛት ነዋሪዎች ወደ ቢሮው ከመጡ ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ ናይራ (የናይጄሪያ ገንዘብ) ለመስጠት ቃል ይገባል።

5 ሺህ ናይራ ወደ ዶላር ሲመነዘር 3 ዶላር ከ70 ሳንቲም ሲሆን፣ ወደ ብር ሲቀየር 210 ነው።

የባለሀብቱን የገንዘብ እደላ ጥሪ ተከተሎ በርካታ ሰዎች ይወጣሉ በዚህ ወቅት በተፈጠረ ግርግር ዕድሜያቸው ከ8 እስከ 55 የሚሆን 7 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አረጋግጧል።

ነዋሪዎች ግን የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተጠቀሰው ይበልጣል ብለዋል።

ብዙ ጊዜ እንዲህ ያለ እደላ/እርዳታ ላይ ወንዶች የእርዳታ ገንዘብ ሲቀበሉ መታየት  ስለማይፈልጉ ሴቶችን እንደሚልኩ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በዕለቱ የተፈጠረውን ነገር ለማጣራት ምርመራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

ቢሮው አካባቢ የጥሬ ገንዘብ ልገሳ ያሰናዳው ባለሀብቱ አልሃጂ ያኩቡ ማይሻኑ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

የናይጄሪያ የምጣኔ ሀብት #መላሸቁን ተከትሎ በርካቶች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል። 5 ሺህ ናይራ አንድን ቤተሰብ ለአንድ ቀን መመገብ ይችላል።

ባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ ናይጄሪያ የናሳራዋ ግዛት ዩኒቨርሲቲ ሩዝ ሲታደል ለመቀበል የወጡ የተወሰኑ #ተማሪዎች ተረጋግጠው #ሞተዋል

ባለፈው ወር የናይጄሪያ ገቢዎች አገልግሎት ሩዝ በቅናሽ ዋጋ ሲሸጥ በተፈጠረ ግርግር የተወሰኑ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቆ ነበር።

ናይጄሪያ ውስጥ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት በርካቶች የሚቀበሉት ደመወዝ ከወር ወር ሊያደርሳቸው እንዳልቻለ ቢቢሲ አስነብቧል።

Via https://publielectoral.lat/thiqahEth

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

" በተጣሉ ተተኳሾች እና ፈንጂዎች 103 ሰዎች #ሞተዋል ፤ አካላቸው ጎድሏል " - የቆላ ተምቤን ወረዳ

በትግራይ ማእከላይ ዞን የቆላ ተምቤን ወረዳ በጦርነቱ ምክንያት በርካታ ተተካሾች እና ፍንጂዎች ይገኛሉ።

እጅግ አስከፊውና ደም አፋሳሹን ጦርነት ተከትሎ በአከባቢው የተቀበሩትና የተጣሉት ተተካሾችና ፈንጂዎች በበርካታ ሰዎችና እንስሳት ላይ የሞትና የአካል ጉዳት አደጋ በማድረስ ላይ እንደሆኑ ተነግሯል።

በወረዳው በተቀበሩትና በተጣሉት ተተኳሾችና ፈንጂዎች እስካሁን 103 ሰዎች #ሞተዋል ፤ አካላቸው ጎድሏል።

አሁን ላይ አደጋውን ለመቀነስ ነዊና ጉያ  በተባሉ የቀበሌ አስተዳደሮች በባለሙያዎች የተደገፈ የማምከን ስራ መጀመሩን የወረዳው አስተዳደር አሳውዋል።

ህዝቡ በአከባቢው ከተለመደው የተለየ ብረት ሲያገኝ ከመንካት እና ከመቀጥቀጥ ተቆጥቦ ለጸጥታ አካላት እንዲያሳውቅ ማሳሰቢያ ተለልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቆላ ተምቤን ወረዳ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ነው ያገኘው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia