" የችግሩ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ ነው "

በአማራ ክልል ፣ በሰሜን ጎንደር 202 ሺህ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

በዞኑ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺ ዜጎች መጎዳታቸው ተገልጿል።

የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ይፋ እንዳደረገው ፤ በዞኑ ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ በተከሰተው ድርቅ 452 ሺህ ዜጎች ተጎድተዋል፤ 202 ሺህ ዜጎችም አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ከፅህፈት ቤቱ በተገኘው መረጃ ፦

- ጃናሞራ ፣ ጠለምት ፣ የበየዳ ወረዳዎችን ጨምሮ፣ ምሥራቅና ምዕራብ ጠለምትና የተወሰኑ የደባርቅ አካባቢዎች በድርቅ ተጎድተዋል፡፡

- ከግንቦት አጋማሽ ጀምሮ ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ሳቢያ 6 ወረዳዎች ለድርቅ ተጋልጠዋል።

- በድርቁ ሳቢያ 19 ሺህ 500 ሄክታር ሰብል ጉዳት ደርሶበታል።

- በዝናብ እጥረት 103 ሺሕ እንስሳት ለድርቅ አደጋ የተጋለጡ ሲሆን 53 ሺሕ የሚደርሱ እንስሳት በድርቁ ሳቢያ #ሞተዋል።

- በጠለምትና ጃናሞራ ወረዳዎች በድርቁ ምክንያት ከ4 ሺሕ በላይ ዜጎች ከአካባቢያቸው ለቀው ወደ ወረዳ ማዕከላት ሄደዋል።

- ዞኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ለማቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡

- በድርቁ አካባቢዎች ላይ ተላላፊ በሽታዎች በተለይም #የኮሌራ_በሽታ ተከስቷል።

- ድርቁ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ላይ ለሚገኙ ዜጎች አስቸኳይ የዕለት ምግብ፣ መድኃኒቶች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ውሃና የእንስሳት መኖ ድጋፍ አስፈላጊ ነው።

- የችግሩ ሁኔታ ከቀን ወደቀን እየከፋ ነው። በድርቁ ሳቢያ ዜጎች ለከፋ ችግር እየተጋለጡ በመሆኑ ሁሉም አካላት እንዲረባረቡ ፤ መንግሥት፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ አጋር አካላት የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያቀርቡ መልዕክት ተላልፏል።

እስካሁን ምን ድጋፍ ተደረገ ? ፅ/ቤቱ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ክልሉ ከአንድ ሺሕ 500 ኩንታል በላይ የምግብ ድጋፍ ማድረጉንና ድጋፉን 14 ሺሕ ዜጎች ማድረስ እንደተቻለ ገልጿል።

Via EPA

@tikvahethiopia