TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦዴፓ ለ29ኛ ዐመት ምስረታ በዓሉ ባወጣው መግለጫ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር ለመመስረት እታገላለሁ ብሏል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር #ዐቢይ_አሕመድ ዜጎች የእኔ ማለት ትተው የእኛ ማለት እንዲጀምሩ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ መጋቢት 19 ቀን 2011 ከአገር ውስጥና ከውጭ #ጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሾች👆

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

• አዲስ አበባ የሁሉምናት እንጂ የአንዱ ብቻናት የሚለው ትክክል አይደለም።

• በህገመንግስቱ የተቀመጠው የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለው የልዩ ጥቅም መብት ግን ሊረጋገጥ ይገባል፤ የሚለውን ሀሳብ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው ሊደግፈው የሚገባ ነው።

• ኢህአዲግ የቀድሞ ጥምረቱ አለ፤ ብዙዎች የተለያየን የሚመስላቸው የልዩነት ሀሳቦች ሲኖሩ አራቱ ፓርቲዎች በውስጣዊ ውይይት ብቻ ይገድቡት የነበረው ሂደት ቀርቶ ፓርቲዎቹ የልዩነት አቋማቸውን በአደባባይ መግለፃቸው ነው ጥምረቱ የሌለ የሚያስመስለው።

• ይህ አካሄድ ወደፊትም ይቀጥላል ሆኖም ተግባራዊ የሚሆነው በጋራ የወሰነው ሀሳብ ነው

• ይበልጥ ወደ አንድ ለመወሃድ የጀመርነው ሂደትም ይቀጥላል።

• የፌደራል መንግስት ተዳክሟል ለማለት መለኪያው መሆን ያለበት ሀገር ስትወረር መመከት ሲያቅተው ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በብቃት መመከት አልችል ሲል ነው።

አሁን ግን በዚህ መልኩ የሚገለፅ አንዳችም ተግዳሮት አልገጠመንም በክልሎች የሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ጣልቃ የማንገባው ክልሎች በራሳቸው መፍታት አለባቸው ብለን ስለምናምን ነው፤ ይህ ደግሞ ተገቢ ነው።

• ከኤርትራ ጋር ያደረግነው ስምምነት መሰረት ያደረገው ሰላምን ነው፤ በቀጣይ ኢኮኖሚ: ንግድ እና መሰል በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመስማማት በሂደት ላይ ነን፤ ስለዚህ ከህዝብ የተደበቀ ሌላ ስምምነት የለንም፡፡

• ዲያስፖራው አሁንም ሀገሩን ለመደገፍ የጀመረውን መንገድ ሊገፋበት ይገባል፤ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ በሚወጡ መረጃዎች ተስፋ የመቁረጥ ነገር ይታያል ይህ ተገቢ አይደለም ሁሉም ነገር ቀድሞ በተግባባንበት መልኩ እየተተገበረ ነው፤ ስለሆን ወደ ኋላ ማለት አይገባም

• በኮዬ ፌጬ የኮንደሚኒዮም ግንባታ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ወሰን ያለው ውዝግብ ተፈቶ ለኮንዶሚኒዮም ባለእድለኞች ቤቶቹ እንዲተላለፉ እየተሰራ ነው

• በኦዲፒና በአዴፓ እንዲሁም በኦዲፒ በራሱ ውስጥ አንድነት እንጂ ምንም አይነት የተለየ ልዮነቶች የለም ነግር ግን በመካከላቸው የልዮነት ሀሳብ ይኖራሉ እነሱንም በመነጋገር እየፈታን ነው

• ከለውጡ በሃላ ኢኮኖሚው በሚፈለገው ደረጃ ውጤቶች ያልታየው ኢኮኖሚው ችግር ውስጥ ሆኖ ስለተቀበልነው እሱን የማስተካከል ስራ እየተሰራ ቆይተናል፡፡ በዚህም በርካታ ሀገራት ድጋፍ ስላደረጉ ውጤት ማግኘት ተችሏል፡፡

• አሁን ላይ ኢኮኖሚው ከታመመበት ሁኔታ ላይ ወጥቶ ጤናማ ሆኗል፡፡

• የአማራና የትግራይ ክልል ውጥረት በቀጣይ በእርግጠኝነት የሚረግብና ወደ ሰላም የሚመለስ ነው፡፡ ሁሉቱም ወገን በኦሮሚያና በሶማሊያ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ያመጣውን ኪሳራ ስለሚያውቁ መካከላቸው ያለው ልዮነት በሰላም ይፈታሉ፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንዳትታለሉ...

(የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት)

በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ የተፃፉ በሚል በየቦታው #እየተሰራጩ ያሉ መፅሃፍትን በተመለከተ በርካቶች እየጠየቁን ይገኛሉ። በመሆኑም አሁን ገበያ ላይ የወጣ አንድም መፅሀፍ አለመኖሩን እንገልፃለን። ወደፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወጡ የህትመት ውጤቶችን ጽ/ቤቱ በይፋ የሚያሳውቅ ሲሆን ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ በሀሰተኛ ህትመቶች እንዳይታለል እናስገነዝባለን።

#PMOEthiopia
@tsegabwolse @tikvahethiopia
#update በጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሚመራውና ለ"ሸገርን ማስዋብ" ፕሮጀክት ገንዘብ የሚያሰባስበው የ"ገበታ ለሸገር" አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ ከቀትር በኋላ ተገናኝቶ የደረሰበትን ደረጃ ተወያይቷል። ኮሚቴው እጁ ላይ ያለውን ሥራ አጠናቅቆ በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውጤቱን ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ፕሬዝዳንት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ እና ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ በ43ኛው የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሠልጣኞችና የቡድን መሪዎችን ዛሬ ማምሻውን በተደገ የእራት ግብዣ ላይ አመሰገኑ። አትሌቶቹ ለሀገራቸው 5 ወርቅ፣ 3 ብርና 3 የመዳብ ሜዳልያዎችን በማስገኘት ከ63 ተሳታፊ ሀገራት በሜዳሊያ ሰንጠረዥ 1ኛ ደረጃ ላይ እንድትሆን አስችለዋል። ጠ/ሚሩ ለኮሚቴው አመራርና አብላጫ ውጤት ላስመሰገቡ አትሌቶች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማት አበርክተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ዉይይት ለተቀሩት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጠሚ/ር ጽ/ቤትና የጤና ሚኒስትር ባለሙያዎችን ያካተተ #ታስክፎርስ ተቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኛል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ ዛሬ ጠዋት በኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ከኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ተማሪዎች ጋር በመሆን ከፊታችን ለሚከበረዉ የኢድ በዓል ስታዲየም አካባቢን አጽዱ። የሙስሊም ወንድምና እህቶች የአንድ ወር ረመዳን ጾም ማብቂያ በተመለከተ የክርስትና እምነት ተከታዮች አጋርነታቸዉን በጽዳት አሳይተዋል።

ኢትዮጵያ❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ ለኤርትራ ህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት!

(ጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia