TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት እያካሄደ ነው። የም/ ቤቱ አባላት ጥያቄዎችን እየቀረቡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጠያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። እስካሁን ፦ - ከኦነግ ሸኔ፣ - ከአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ፣ - ከሰሜኑ የሰላም ስምምነት፣ - ከዜጎች መፈናቀልና ግድያ፣ - ወደ አዲስ…
#ፓርላማ

" እነኚህ ሰዎች ሰላም ቢኖር ምን ያጣሉ ? #ከህወሓት ጋር ሰላም ወረደ ሰላም አገኘን ምን አጡ ? #ከኦነግ_ሸኔ ጋር ሰላም ቢወርድ ምን ያጣሉ ? "

ዶክተር ከፈና ኢፋ (የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል) ጠቅላይ ሚኒስትሩን ምን ጠየቁ ?

" .... በኦሮሚያ ክልል ጦርነት በኢኮኖሚ ላይ በፖለቲካ ላይ ፣ በማህበራዊ ህይወት ላይ ያስከተለውን መጠነ ሰፊ ጥፋት እና ጉዳት ዘርዝሬ መጨረስ አልችልም፤ ህዝብ ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ነው።

ህዝባችም በጣም እየተንገላታ ነው፤ በቅርቡ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ታጥቆ ለሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የሰላም ጥሪ አቅርቦላቸዋል፤ ይሄ የሰላም ጥሪ ምን ላይ ደርሷል ? ጅምሩ ምን ይመስላል ? ህዝባችን በአሁን ጊዜ በጉጉት አይደለም እየጠበቀ ያለው ይሄን የሰላም ድርድር በፀሎት ጭምር ነው በፆም በፀሎት ጭምር የዚህን ድርድር መጀመር እየጠበቅን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው።

ስለዚህ #ሰላም ለተጠማው ህዝባችን ሰላም ለማውረድ በዚህ ረገድ መሬት ላይ ምን እየተሰራ ነው ?

ከኦነግ ሸኔም ጋር ይሁን ከህወሓት ጋር ለተደረገው የተሳካ ስምምነት ኢትዮጵያውያን ሆነው የሚቃወሙ ሰዎች አሉ፤ ይሄን የሚያደርጉት ከውሥጥም ከውጭም ነው።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ ሰላም ከምንም በላይ ብሄራዊ ጥቅማችን ነው ፤ ኢትዮጵያውያን ሆነው ከራሳቸው ብሄራዊ ጥቅም በተፃራሪነት መቆም ትርጉሙ ምንድነው ? ምን ለማግኘት ነው ? ምን ለማጣት ነው ?

እነኚህ ሰዎች ምን ያጣሉ ሰላም ቢኖር ? ከህወሓት ጋር ሰላም ወረደ ሰላም አገኘን ምን አጡ ? ከኦነግ ሸኔ ጋር ሰላም ቢወርድ ምን ያጣሉ ? መፈናቀል ነው የሚቀረው ፣ ተጨማሪ የሰው ስቃይ ነው የሚቀረው ፣ የንብረት መውደም ነው የሚቀረው፣ የመሰረተ ልማት መውደም ነው የሚቀረው ይሄን የሚቃወም ኢትዮጵያዊ ምን አይነት ኢትዮጵያዊ ነው ? ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ አመሰግናለሁ !! "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ማስታወሻ

ዛሬ በአዲስ አበባ " ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ-3 ' ይካሄዳል።

ምዕመናን ስትመጡ የሚከተሉትን እንዳትዘነጉ ፦

- ለጸጥታ አካላት እና ለበጎ ፍቃድ አስተባባሪዎች #ፍተሻ ትብብር ማድረግ።

- የሰላት መስገጃ ይዞ መምጣት።

- ለማፍጠሪያ የሚሆንና ከሙስሊም እህትና ወንድሞች በማካፈል ኢፍጣርን ለሌሎች በማጋርት የሚገኘውን አጅር ተቋዳሽ እንዲሆኑ ጥሪ ተደርጓል። ምግቦቹ እንደ ቴምር፣ ውሃ እና የታሸጉ ምግቦች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

- የዝግጅቱ ዋና ዓላማ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከሌሎች ጋር ኢፍጣርን በማጋራት የሚገኘውን አጅር እና ደስታ እንዲያጣጥም ከማስቻል ባሻገር ሙስሊሙ ህብረተሰብ ምንም ዓይንት ልዩነት ሳይገድበው ህብር ብሄራዊ አንድነነቱን በማሳየት ለሃገር #ሰላም እና #ዕድገት በጋራ አላህን የሚማፀንበት ዝግጅት ስለሆነ ከዝግጅቱ ዓላማ ውጪ ከሆኑ ድርጊቶች በመቆጠብ ኢስላማዊ ስነምግባርን ለሌሎች ዓርኣያ በመሆን ማሳየት ይገባል።

- ማንኛውም ለደህንንት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ከተመለከቱ ለበጎ ፍቃደኛ አስተባባሪዎች እና ለጸጥታ አካላት በአፋጣኝ አሳውቁ።

- በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በመጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ገንዘብ ስለሚሰበሰብ ከወዲሁ በረመዳን ለተቸገሩ ድጋፍ በማድረግ የሚገኘውን ታላቅ አጅር እንዲሸመቱ የአቅሞን ገንዘብ ይዘው ወደ ዝግጅቱ እንዲመጡ።

(ከአዘጋጆቹ)

@tikvahethiopia
" የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቀጣዩን ድርድር በማፋጠን ህዝቡ ለተጠማው #ሰላም ቅድሚ ሊሰጡ ይገባል " - ኦፌኮ

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በ2014 ዓ.ም 2ተኛ ጠቅላላ ጉባኤን አካሂዷል፤ በመደበኛ ስብሰባውም የተለያዩ ነጥቦችን የያዘ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም ፦

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያን ጨምሮ በአጠቃላይ በመላው ሀገሪቱ እየሞከረ ያለውን እርቅና ድርድር በመርህ ይደግፋል ብሏል።

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 5 ዓመታት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) መካከል የተፈጠረው ጦርነት መነሻው ፖለቲካዊ አለመግባባት በመሆኑ በሰሜን ኢትዮጵያ እንደተደረገው ጦርነት ሁሉ በሰላም እና በእርቅ እንዲቆም ደጋግሞ ጥሪ ማቅረቡን ኦፌኮ አስታውሷል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሰላማዊ መንገድ ድርድር መጀመራቸውን በደስታ እንደሚቀበል የገለፀው ፓርቲው የሁለቱ ወገኖች የመጀመሪያው ዙር ድርድር መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣዩ ድርድር በማፋጠን ህዝቡ ለተጠማው ሰላም ቅድሚ እንዲሰጡ አሳስቧል።

የሰላም ድርድሩ ከተኩስ አቁም ስምምነት ባለፈ የኦሮሞን ህዝብ በሚመለከቱ ውስብስብ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ቀሪ የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎችን ማሳተፍ እንዳለበት መረዳት ያስፈልጋልም ሲል አስገንዝቧል።

ከዚህ ባለፈ ኦፌኮ ፤ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመንግስት ታጣቂዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ እያደረሱ ያለው ህገወጥ ግድያ እስራትና ንብረት ማውደም፤ እንዲሁም በፓርቲው ደጋፊዎች፣  አባላት እና አመራሮች ላይ እየደረሰ ያለው እስራት ፣ ግድያ፣ ደብዛማጥፋት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠይቋል።

በተለያዩ ስም የመንግስት ካድሬዎች ያለ ደረሰኝ የሚሰበሰብ ገንዘብ እንዲቆም፤ ከመንግስት እና ከገዢ ፓርቲው ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ህገ ወጥ ንግድን ቁጥጥር እንዲደረግበትም ኦፌኮ ጠይቋል።

ሌላው ኦፌኮ በመግለጫው የዋጋ ንረትን በተመለከተ ያነሳ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የዋጋ ንረት በህዝብና በኢኮኖሚ ላይ ላደረሰው ጉዳት ገዢው ፓርቲ ሙሉ ኃላፊነት ሊወስድ ይገባል ብሏል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው  የዋጋ ንረት በገዢው ብልፅግና ፓርቲ የተሳሳተ ውሳኔ ምክንያት መሆኑን ፓርቲው (ኦፌኮ) ገልጿል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የግንቦት 2015 ዓ.ም የርክበ ካህናት ጉባኤ ባለ  10 ነጥብ መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል። ዛሬ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጥቷል። ቅዱስ ሲኖዶስ ምን አለ ? ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያናን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን ማሳለፉን አሳውቋል።…
#ሰላም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ግጭቶች እና አለመግባባቶች በውይይት ይፈቱ ዘንድ የሰላም ጥሪ አቀረበች።

ይህን ጥሪ ያቀረበችው የ2015 ዓ/ም የግንቦት ርክበ ካህናት ጉባኤ መጠናቀቁን ተከትሎ ትላንት በሰጠችው መግለጫ ነው።

ቤተክርስቲያኗ በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታዩትን አላስፈላጊ ግጭቶች የዜጐች መፈናቀል፣ ስደት ተወግዶ ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር፤ ለማድረግ ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ አስተላልፋለች።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ ቤተክርስቲያኗ በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላም እና ዕርቅ እንዲሰፍን ተመኝታለች።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ በፕሪቶሪያው የ #ሰላም_ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች #የመጀመሪያው_ዙር የተሀድሶና መልሶ የማቋቋም መርሀ ግብር ዛሬ ከመቐለ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ኩሓ በይፋ መጀመሩን ኢፕድ ዘግቧል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ወቅት ላይ መንግስት በትግራይ ያሉ ታጣቂዎችን ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ወደመደበኛ ህይወታቸው እስኪመለሱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

Photo Credit : EPA

@tikvahethiopia
ጋምቤላ . . . ኦሮሚያ

" በአካባቢው #ሰላም አስፍኛለሁ " - የሀገር መከላከያ ሰራዊት

ይህ ከጋምቤላ ወደ ሸበል ደንቢዶሎ የሚወስደው መንገድ ላለፉት 3 ዓመታት በፀጥታ ችግር ተዘግቶ ቆይቷል።

በዚህም ምክንያት ፤ ዜጎች ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግር ሲገጥማቸው ነበር።

አሁን ላይ ግን ሀገር መከለከያ ሰራዊት መንገዱ ለኅብረተሰቡ አገለግሎት መስጠት እንዲችል የሰላም ማስከበር በመስራት መንገዱ እንዲከፈት ማድረጉን አሳውቋል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት " በቀጠናው የተሰጠኝን የሰላም ማስከበር ግዳጅ በአግባቡ በመወጣት በአካባቢው ሰላም አስፍኛለሁ " ብሏል።

ማኅበረሰቡ በስፋት የሚገናኝበት እንዲሁም የገበያ ትሥሥሩን የሚያጠናክርበት መንገድ ዳግም በሰላም መደፍረስ እንዳይዘጋ የመንግሥት ኃላፊዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የመከላከያ ሰራዊቱ አስገንዝቧል።

በዚህ ቀጠና ባለፉት 3 ዓመታት በነበረው ግጭት ሕዝቡ ክፉኛ የተጎዳ ሲሆን በተለይ የመንገዱ መዘጋት በሕዝቡ  #የኢኮኖሚያዊ እና #ማኅበራዊ ሕይወት ላይ ከፍተኛ ቀውስ አስከትሏል።

#GambellaPressSecretariat

@tikvahethiopia
#ሰላም

" እርቅ ይውረድ ! የሰው ደም መፍሰስ ይብቃ ! ሰላም ይታወጅ ! ምድሪቱንም እናሳርፋት ! " - ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ አባታዊ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል።

ቅዱስነታቸው ካስተለለፉት መልዕክት የተወሰደ ፦

" ከአካላዊ ጦርነት እስከ ቃላት ውርወራ ብዙ ጥላሸት የመቀባባት ሰለባ ሆነው የወደቁት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ልጆቻችን ትምህርት ሆነውን ልባችን ዘንበል ባለማለቱ ለወደፊት ሊመጣ የሚችለው ሲታሰብ እጅግ ያስፈራልና በዐራቱም ማዕዘን ነፍጥ አንሥታችሁ ያላችሁ በሙሉ ያነገባችሁትን ገዳይ መሣርያ አውርዳችሁ ለሰላምና ለዕርቅ ቅድሚያ በመስጠት ለአንዲት አገራችሁ ሕልውና ተገዢዎች እንድትሆኑ፤ መንግሥትም ልበ ሰፊ ሁኖ ሁሉንም ለውይይት እንዲሰበስብ በጽኑ እንለምናለን።

በኢትዮጵያ ምድር ላይ ያላችሁ ሽማግሌዎች ሽምግልናችሁ ለዚህ ቀን ካልሆነ ለመቼም አይሆንምና በአገሩም ሽማግሌ የለም ወይ? መባሉ በሰማይ በምድር ያስወቅሳልና ልጆቻችሁን እንድትመክሩና እንድታስታርቁ ከዛሬ ጀምሮም ለሰላም ጠበቆች ሁናችሁ እንድትቆሙ አበክረን እንጠይቃለን።

በውጭ አገር የምትኖሩም #እናንተ_በሰላም_አገር_እየኖራችሁ ዘመዶቻችሁ በእሳት ሲጠበሱ ዝም ብሎ ማየት ስለማይገባ እስከአሁን ስታደርጉት እንደቆያችሁት ሁሉ አሁንም ለሰላሙ ብርቱ ጥረት እንድታደርጉ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

በተጨማሪም ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ግጭት ባለባቸው አከባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን ጥረትና እገዛ እንዲያደርጉ፣ ቤተ ክርስቲያንን የምንመራ ውሉደ ክህነትም መፍትሔ መሆን ሲገባን የችግሩ አካል ሆነዋል እየተባልን ነውና ውስጣችንን አጥርተን ለወገኖቻችን በአስታራቂነት ለመድረስ ጊዜው አሁን ስለሆነ ዛሬ እንድንነሣሣ መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን። "

ቅዱስነታቸው ዛሬ ባወጡት አባታዊ የሰላም ጥሪ ፤ " አሁን ያለው ችግር ወደ ቀጣይ አመት እንዳይሻገር ገትተነው ቀጣዩን አዲስ ዓመት በሰላም ለመቀበል እንችል ዘንድ ከጉልበት ሳይሆን ከልብ ሽብረክ በማለት እርቅ ይውረድ ! የሰው ደም መፍሰስ ይብቃ ! ሰላም ይታወጅ ! ምድሪቱንም እናሳርፋት ! " በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
" ያለፈው ዘመን ይበቃ ዘንድ ስለሰላም ልንጸልይ ይገባል " - ብፁዕ አቡነ አብርሃም

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ " እንደቀድሞ ጊዜ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን እያለች #ሰላም ከሀገር አይርቅም ነበር፤ ዛሬ በእኛ በአገልጋዮቿ ምክንያት ያን ሚናዋን አጥታለች " አሉ።

ብፁዕነታቸው ይህን ያሉት በ " ማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ " ላይ ተገኝተው ቡራኬና ቃለ ምእዳን በሰጡት ወቅት ነው።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በወቅታዊ የሀገሪቱ የሰላም ሁኔታ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፥ " "ቤተ ክርስቲያን አንድ ሁኑ ብላ ታስተምራለች ፤ ጥላቻን መገዳደልን ታወግዛለች፤ በንግግር በውይይት ፍቱ ትላለች " ብለዋል።

" ይህንን አቋሟን በበጎ የማይመለከቱ ግን ይኖራሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ " እንደቀድሞ ጊዜ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን እያለች ሰላም ከሀገር አይርቅም ነበር፤ ዛሬ በእኛ በአገልጋዮቿ ምክንያት ያን ሚናዋን አጥታለች " ያሉ ሲሆን " ወላዋይና አድርባዮች ስለሆንን፣ ምን አገባኝ ብለን መስለን ስላለን ሀገሪቱን ዋጋ እያስከፈልን ነው፤ የወገን ደምም ሲፈስ ማየት ተለምዷል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ያለፈው ዘመን ይበቃ ዘንድ ስለሰላም ልንጸልይ ይገባል" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የማህበረቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " - ብፁዕነታቸው

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት  የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን ተሻግረው የጣሊያን ወረራን አልፈዋል እንዲሁም በየዘመናቱ በተፈጠሩ የእርስበርስ ጦርነቶች ጉዳት ሳያደርሱባቸው እዚህ ደርሰዋል ብላለች።

ይሁን እንጂ አሁን ባለበንበት ዘመን በአካባቢው  በተፈጠረው ከፍተኛ የሰላም እጦትና ጦርነት  ምክንያት ከፍተኛ  የአደጋ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን በይፋ አሳውቃለች።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት በከፍተኛ የአደጋ ሥጋት ላይ መውደቃቸውን ገልጸው ፤ ቅዱሱን ቅርስ ከስጋት ነጻ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሁሉም አካል ወደ #ሰላም_መድረክ መምጣት እንዳለበት በቅድሚያ ጠቁመዋል።

" ይህ ካልሆነ ግን ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና   የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ  የቅዱስ ላሊበላ ቅርስና የአምልኮ ቦታ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባለድርሻ አካላት ቅዱሱ ቅርስ  ከአደጋ ስጋት ውጭ እንዲሆን ዓለም አቀፍ  ተቋማት የመንግስት አካላት እንዲሁም  የቅዱሱ ቅርስ  የጋራ ሀብትነት የሚያሳስበው ሁሉ  በጉዳዩ ላይ  በጎ ተጽእኖ በማሳደር ድምጽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " - ብፁዕነታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት  የአደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውን አሳወቀች። ቤተክርስቲያኗ ፤ በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በ900 ዓመታት ውስጥ ብዙ መከራን…
" የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቦታውም ቅዱስ ነው ህንጻውም #ሰላም ነው " - የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ

የአማራ ክልላዊ መንግሥት ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ " ላሊበላ ጉዳት ደረሰበት " በሚል በየማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው አለ።

የቅዱሱ ስፍራ ህንጻም ሰላም ነው ብሏል።

" የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቀደምት ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ ነው " ያለው ቢሮው " በዚህ የዓለም ቀደምት ቅርስ ስም ሐሰተኛ ፕሮጋንዳ እየነዙ፤ ሕዝብን እያደናገሩ አሸናፊ ለመሆን መሞከር ሞራላዊና ኅሊናዊ ኪሳራን እንጅ ድልን አያጎናጽፍም " ብሏል።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኘው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተደርጎ ከትናንት ጀምሮ የሚናፈሰው ወሬም መሠረት ቢስ ነው ሲል ሀልጿል።

" በላሊበላ ስም መቀደስ እንጅ የጥፋት ድግስ መደገስ አስፈላጊና ተገቢ አይደለም። " ያለው ቢሮው " የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቦታውም ቅዱስ ነው ህንጻውም ሰላም ነው " ሲል አሳውቋል።

በላሊበላ አካባቢ በተለያየ ጊዜ ግጭት እያገረሸ የሰው፣ የንብረት ጉዳት እየደረሰ የሚገኝ ሲሆን ሰሞኑንም በቀጠናው የመንግሥት ኃይሎች እና የታጠቁ ኃይሎች ዳግም ግጭት ላይ ነበሩ።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአካባቢው በተፈጠረው ከፍተኛ የሰላም እጦትና ጦርነት  ምክንያት
የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ከፍተኛ #የአደጋ_ሥጋት ላይ መውደቃቸውን አሳውቃ ነበር።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ የቅዱስ ላላበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ምክንያት በከፍተኛ #የአደጋ_ሥጋት ላይ መውደቃቸውን የገለፁ ሲሆን ቅዱሱን ቅርስ ከስጋት ነጻ ለማድረግ ይቻል ዘንድ ሁሉም አካል ወደ #ሰላም_መድረክ መምጣት እንዳለበት ጠቁመዋል።

" ይህ ካልሆነ ግን ቅዱሱን ቅርስ መጠበቅና   የአባቶቻችንን አደራ እንዳንበላ በአካባቢው የጦርነት ድምጽ እንዳይሰማ መደረግ አለበት " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ብፁዕነታቸው የቅዱስ ላሊበላ ቅርስና የአምልኮ ቦታ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባለድርሻ አካላት ቅዱሱ ቅርስ ከአደጋ ስጋት ውጭ እንዲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማት የመንግስት አካላት እንዲሁም የቅዱሱ ቅርስ የጋራ ሀብትነት የሚያሳስበው ሁሉ በጉዳዩ ላይ በጎ ተጽእኖ በማሳደር ድምጽ እንዲሆን ጥሪ አቅርበው ነበር።

@tikvahethiopia