TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

በአዲስ አበባ ቦሌ ድልድይ ስካይ ላይት ሆቴል አካባቢ የመብራት ፖል ወድቆ በአንድ ሰዉ ላይ የሞተ አደጋ ደርሰ። በቦሌ ክፍለ ከተማ ስካይ ላይት ሆቴል ፊት ለፊት ረፋድ 5 ሰዓት አካባቢ መብራት ፖል ተሰብሮ በስራ ላይ በነበረ የመብራት ሀይል ሰራተኛ ላይ #የሞት አደጋ አጋጥሟል፡፡

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ባለሙያዉ ሳጅን ምትኩ መንገሻ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት፤ በአካባቢዉ የሚገኝ አንድ የመብራት ፖል ለመንቀል በክሬን መኪና እየተሰራ ባለበት ወቅት ፤ፖሉ ከክሬኑ አምልጦ በሰራተኛዉ ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል፡፡

የመብራት ፖሉ በሰዉ ሃይል አልነቀል በማለቱ በመኪና ክሬን ፖሉን ለማንሳት በሚደረግበት ወቅት ፖሉ በሰረተኛዉ ላይ ማረፉንም ሳጅን ምትኩ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቡ ወዲያዉኑ ህይዎቱ ያለፈ ሲሆን የግለሰቡን ማንነት ለመለየት ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ እያደረገ ነዉ ብለዋል፡፡ የመኪናዉ አሽከርካሪም በቁጥጥር ስር መዋሉን ሳጅን ምትኩ አረጋግጠዋል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሃዱ ጋዜጠኞች ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ ተቋረጠ!

በኦሮሚያ ክልል የፊንፊኔ ልዩ ዞን የበረህ ወረዳ አቃቢ ህግ ከ67 ቀናት በፊት ነበር በአሃዱ ሬድዮ ጋዘጠኞች ላይ ከወራት በፊት በተሰራ ዘገባ ምክንያት ክስ የመሰረተው። ጋዜጠኛ ታምራት አበራ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ ሊዲያ አበበና ሱራፌል ዘላለም ክሱ የተመሰረተባቸው ጋዜኞችም ናቸው።

የወረዳው ፍርድ ቤትም በጋዜጠኞቹ ላይ 1ኛ ስም በማጥፋት፣ 2ኛ ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት እንዲሁም የብሮድካስት ህግን መተላለፍ በሚል ነበር ሶስት ክሶችን የመሰረተው። የበረህ ወረዳ ፍርድ ቤትም በጋዜጠኞቹ ላይ የቀረበውን ክስ ካዳመጠ በኋላ ጋዜጠኞቹን እንዲከላከሉ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ይሁንና ጋዜጠኞቹ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት ዛሬ የመከላከያ ምስክሮችንና ሰነዶችን ይዘው ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም በጋዜጠኞቹ ላይ የተመሰረተው ክስ በኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቢ ህግ ትዕዛዝ እንዲቋረጥ መወሰኑን የአሃዱ ሬድዮ ስራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በውስኔው ደስ መሰኘታቸውን የገለጹት ጋዜጠኛ ጥበቡ ክሱ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነትንና የጋዜጠኝነት ሙያን የሚጋፋ ነው ብለዋል። ጥፋት እንኳን ቢኖር ጉዳዩ መታየት ያለበት በብሮድካስት ባለስልጣን በኩል ነበርም ብለዋል ጋዜጠኛ ጥበቡ።

ጋዜጠኛ ጥበቡ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር የተመሰረተባችሁን ክስ አስመለክቶ ምን ድጋፍ አደረጉላችሁ ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄም ማህበሩ ምንም አይነት ድጋፍ አላደረገም ጉዳዩንም አላወገዘም ሲሉ ተናግረዋል።

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጎርፍ እና የእሳት አደጋዎች #በአዲስ_አበባ

በአዲስ አበባ ከተማ #ቅዳሜና #እሁድ ሁለት የእሳት እንዲሁም ሶስት የጎርፍ አደጋዎች እንደተከሰቱ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ በአደጋዎቹ ሳብያም የሰው ሂወት አለመጥፋቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያው አቶ ሲለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ራድዮ ገልጸዋል፡፡

የእሳት አደጋዎቹ የደረሱት በአዲስ ከታማ ክፍለ ከተማ መርካቶ በርበሬ በረንዳ ላይ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ ሲሆን በአደጋው ሳቢያም አንድ ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድቧል ተብሏል። ኮሚሽኑ ሀያ ሚሊየን የሚጠጋ ንብረት ከውድመት ታዲጌያለሁ ብሏል።

ሁለተኛው የእሳት አደጋ የደረሰው በኮሊፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ልዩ ስሙ አለም ባንክ አካባቢ በሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ ሲሆን በአደጋው 850 ሺ ብር የሚጠጋ ንብረት እንደጠፋና ስምንት ሚሊየን የሚገመት ንብረት ደግሞ ማዳን ተችላል፡፡

የጎርፍ አደጋዎቹ የደረሱት ደግሞ ሁለቱ በአራዳ ክፍለ ከተማ ሲሆን አንደኛው በወረዳ አምስት ሶር አምባ ሆቴል አካባቢ ሲሆን ሌላኛው የጎርፍ አደጋ ደግሞ በወረዳ ሁለት ጣሊያን ሰፈር አካባቢ በመኖርያ ቤት የደረሰ የጎርፍ አደጋ ነው። በሁለቱም የጎርፍ አደጋዎች በግምት ሁለት መቶ ሺ ብር የሚገመት ንብረት መጥፋቱ ተገልጿል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሂጅራ_ባንክ

ሂጅራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ሂጅራ ባንክ አክሲዮን መሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሄራዊ ባንክ ካገኘ አንድ ወር እንደሞላው ነው የተገለጸው፡፡

የሂጅራ ባንክ አክስዮን አደራጆች ሰብሳቢ አቶ አህባብ አብድላ እንዳሉት ላለፉት ሁለት አመታት በሀገር ደረጃ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲፈጠር የተለያዩ ጥናቶችን ሲያከናውኑ እንደቆዩ ተናግረዋል፡፡ ባንኩ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ስርአትን በማበልጸግ ለዘመናት በሀገራችን ምጣኔ ሀብታዊ እንቅቃሴ ውስጥ ባለው ውስን ተሳትፎ የሚታወቀውን የህብረተሰብ ክፍል በሀገሪቱ እድገት ላይ አዎንታዊ ሚና እንዲኖረው የማስቻል ስራ መስራቱንን ገልጿል።

የሂጅራ ባንክ አክሲዮን ማህበር አነስተኛው የአክሲዮን ሽያጭ 30ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው የአክሲዮን ሽያጭ ደግሞ 20 ሚሊየን ብር ነው ተብሏል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ አንድ ቢሊየን ብር የአክሲዮን ሽያጭ ለመሸጥ እንዳሰበም ተገለጿል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ

በኢትዮጵያ ቅፅበታዊ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሚትሮሎጂ ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ከክረምቱ ዝናብ ጋር ተያይዞ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ቅፅበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል። አልፎ አልፎ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከሚጠናከሩ የደመና ክምችቶች ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችልም ትንብያዉ ያሳያል፡፡ በመሆኑም ህብረተሰቡ ከመሰል አደጋዎች እራሱን እንዲጠብቅና #እንዲጠነቀቅ ኤጀንሲው አሳስቧል።

በአብዛኛዉ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጥሩ የእርጥበት ሁኔታ እንደሚኖር ትንበያዉ የሚያመለክት ሲሆን ይህም ለግብርናዉ የስራ እንቅስቃሰሴ ትልቅ ጠቀሜታ እንደሚኖረዉ ታምኖበታል፡፡ ቀድመዉ የተዘሩ እና በእድገት ላይ ለሚገኙ የመኸር ሰብሎች የሚገኘዉ እርጥበት በጎ ሚና አለዉ ተብሏል፡፡ ከዚህ ባለፈም ለቋሚ ተክሎች የዉሓ ፍላጎታቸዉን እንደሚያሟላለቸዉና ለአርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች የግጦሽ እና የመጠጥ ዉሃ እንዲያገኙ ያስችላል፡፡

በቀጣይ የሚኖረዉ የአየር ሁኔታ አዝማሚያ በተፋሰሶች ላይ ለዉጥ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡ በአብዛኛዉ የተከዜ፣ የኦሞ ጊቤ የአባይ፤ የላይኛዉና የመካከለኛዉ አዋሽ እና አፋር ደናክል ተፋሳሾች ከፍተኛ እርጥበት ያገኛሉ ተብሎ ተገምቷል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
ፎቶ: ፋይል

@tsegabwolde @tikvahethiopia