TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"National Exams will be administered for grade 10 from Sene 3-5,grade 12 on Sene 6,7,10 & 11 & grade 8 from 12-14/2011E.C. Good luck!" Araya G/Egziabher D/G NEAEA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ አባላት መልማይ ኮሚቴ በትላንትናው ዕለት 8 ዕጩ አባላትን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሰረት ኮሚቴው መጋቢ ዘሪሁን ደጉ መንግስቴን፣ አቶ መላኩ ስብሀት በዳኔን፣ አቶ ውብሸት አየለ ጌጤን፣ አቶ ብርሀነ ሞገስ ፍቅርን፣ አቶ ደመወዜ ማሞን፣ ወ/ሮ ብዙወርቅ ከተተን፣ ዶ/ር ጌታሁን ካሳን እና አቶ አበራ ደገፉ ነገዎን እንዲሁም አንድ ተጠባባቂን በዕጩነት መርጧል፡፡

የመልማይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር መሸሻ ሸዋረጋ እንደተናገሩት 8ቱን ዕጩ አባላት ለመምረጥ በስልክ፣ በፋክስ እና በኢሜል የቀረቡት 200 ገደማ ተጠቋሚዎች በ3 የማጣሪያ ምዕራፎች እንዲያልፉ ተደርጓል፡፡

ዕጩዎቹ በህግ፣ በፖለቲካ ሳይንስ፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ከምርጫ ጋር ተያያዥ በሆኑ መስኮች ስለመማራቸው በመጀመሪያው የማጣሪያ ምዕራፍ ታይቷል፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ አባላት መልማይ ኮሚቴው የመረጣቸውን 8 አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚልክና ለቦታው የሚፈለጉት የመጨረሻዎቹ 4 ሰዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚለዩ ተገልጿል፡፡

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የጋምቤላ ክልሎች የጋራ የሰላም እና የልማት የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናዎችን ከሰኔ 3/2011 ዓ.ም ጀምሮ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉበሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳሉት የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናዎቹን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ተማሪዎች ተረጋግተው በመፈተን የሚጠበቅባቸውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትና መላው ህብረተሰብ የተማሪዎችን ስነ-ልቦና የሚያጠናክሩ ሥራዎችን በመከወን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርኣያ ገ/እግዚአብሄር የዘንድሮ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከሰኔ 03/2011ዓ.ም እስከ ሰኔ 05/2011 ዓ.ም እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሰኔ 6፣7፣10 እና 11/2011 ዓ.ም እንደሚሰጥ ገልጸው ለ10ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተመዘገቡ ተማሪዎች 1,277,533 እና ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተመዘገቡ ተማሪዎች 322,317 ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ዓመት ከተማሪዎች ምዝገባ ጀምሮ የፈተና ህትመትና ሌሎችን ጨምሮ እስከ ሥርጭት ያሉ ሥራዎች ከዚህ በፊት ከነበሩት ዓመታት በተሻለ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የተከናወኑ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ አክለው መግለጻቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ዘገባ ያመለክታል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
YOU DON'T NEED TO BE
A DOCTOR TO SAVE LIVES
GIVE THE
GRACIOUS GIFT OF LIFE.
JUNE 09/2019 Sunday / ሰኔ 02/2011እሁድ[4:00pm-7:00pm]
#update በዱባይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ከመንገድ ምልክት ጋር በመጋጨቱ በደረሰ አደጋ የ17 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ለጉዳት ተዳርገዋል። ሟቾቹ የተለያየ አገራት ዜጎች እንደሆኑም ታውቋል።

መለያ ቁጥሩ በኦማን የተመዘገበው ተሽከርካሪው አደጋ ሲደርስበት 31 ሰዎችን አሳፍሮ በሸክ መሐመድ ዛይድ ጎዳና ላይ እየተጓዘ እንደነበር ፖሊስ አስታውቋል።

ከሟቾቹ መካከልም ስምንቱ የሕንድ ዜጎች መሆናቸውን የሕንድ ባለሥልጣናት አረጋግጠናል ብለዋል።

በዱባይ የሚገኘው የሕንድ ኤምባሲ የሟቾቹን ሕንዳውያን ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸውም አሳውቀዋል፤ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሕንዳውያንም ህክምና እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

የ50 ዓመቱ የአውቶብሱ አሽከርካሪ ቀላል ጉዳት ያጋጠመው ሲሆን ሕክምና እየተደረገለት ይገኛል።

የዱባይ ፖሊስ በይፋዊ የትዊተር ገፁ ላይ በተፈጠረው አደጋ ማዘኑንና ለተጎጅ ቤተሰቦችም መፅናናትን እንደሚመኝ አስፍሯል።

የፖሊስ ኃላፊው ማጅ አብዱላህ ካሊፋ አል ማሪ "አንዳንድ ጊዜ ተራ ስህተት አሊያም ግድ የለሽነት እንዲህ ዓይነት አስከፊ አደጋዎችን ያስከትላሉ" ብለዋል።

የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ሲሆን ስለ አደጋው ዝርዝር ሁኔታ የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ አሽከርካሪው የመንገድ ምልክትን በመጣሱ በድንገት መንገድ ለመቀየር ሲል አደጋው እንዳጋጠመው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የኦማን የአውቶቡስ አምራች ምዋሳላት " በአደጋው የተሰማቸውን ሃዘን የገለፁ ሲሆን ከሙስካት ዱባይ የሚሰጡትን አገልግሎት ለጊዜው ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ ዩኒቨርሲቲ...

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ማዕከል /UNESCO/ በአለም ቅርስነት የተመዘገቡ 12 ቱ የኢትዮጵያ የፅሁፍ ቅርሶች ''ግዕዝና ስነ ፈውስ'' በሚል መሪ ቃል በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ባለው አምስተኛው ሀገር አቀፍ የግዕዝ ጉባዔ ላይ ከቀረበ አውደ ርዕይ የተወሰደ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ለመለየትና ለመመልመል የተቋቋመው ኮሚቴ የሥራ ሂደትን በተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር እየተወያዩ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ውሳኔ...
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምክትል የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከሌሎች የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት እና ተማሪዎች ጋር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ጊቢ ውስጥ ችግኝ ተክለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 71ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2012 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikavhethiopia
#update ሱዳን ውስጥ ሁለት የአማፂያን መሪዎች እና አንድ የተቃዋሚው መሪ በፀጥታ ኃይላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የተቃዋሚ ኃይሎች ገለፁ። ይህ የሆነው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ወታደራዊው ምክር ቤት እና ከተቃዋሚ መሪዎች ጋር ሱዳን መዲና ካርቱም ላይ ከተወያዩ ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑ ነው።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ዓርብ ዕለት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተገኙት የሰሜን ሱዳን ህዝብ የነፃነት ንቅናቄ ዋና ፀሀፊ ኢስማኤል ጃላብ እና የታጠቀው ቡድን ቃል አቀባይ ሙባራክ አርዶል በቁጥጥር ስር የዋሉት ከስብሰባው ጥቂት ሰዓታት በኋላ እንደሆነ ተዘግቦአል። የተቃዋሚው መሪ ሞሀመድ ኤስማት እና የአማፂያን መሪዎቹ አባላት የት እንደታሰሩ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በሃገሪቱ የታየዉ ኃይል የቀላቀለ ብጥብጥ እንዲያበቃ እና ሀገሪቱም ወደ ትክክለኛው የዲሞክራሲ መንገድ እንድታመራ ወታደራዊ ኃይሉ ስልጣኑን በሲቪል ለሚመራ ኃይል እንዲያስረክብ ግፊት አድርገዋል። ካለፈው ሰኞ አንስቶ በከተማዋ በነበሩ ግጭቶች ቢያንስ የ60 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ...

ዛሬ በተጨዋች ወንደሰን ዮሐንስ መኖሪያ ቤት የሰፈሩ ልጆች እና ጓደኞቹ የሻማ ማብራት እና ፀሎት ፕሮግራም እያካሄዱ ይገኛሉ። ወንደሰን ከቀናት በፊት ነቀምት ከተማ ውስጥ በጥይት ተመቶ ህይወቱ ማለፉ አይዘነጋም።

በድጋሚ ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናት እንመኛለን!!

Via Yitba
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዉ በመንግስት የፀጥታ አካላት የተከለከለ መግለጫ አለመኖሩን ገለፀ፡፡

ጌት አማካሪዎች የንግድና ኢንቨስትመንት የተባለ ድርጅት ግን በዚህ ሳምንት ለሁለት ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳልሰጥ ተከልክያለሁ ብሏል፡፡

የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ ጌታነህ ባልቻ ለኢቲቪ እንደተናገሩት አዲስ የሚቋቋምን የቴሌቭዥን ጣቢያ አስመልክቶ ትናንት በሂልተን ሆቴል ሊሰጥ የነበረዉ መግለጫ በሆቴሉ የፀጥታ ሀላፊ በኩል መግለጫዉ በመንግስት አካላት ስለመከልከሉ ተነግሮናል ብለዋል፡፡

የሂልተን አዲስ ሆቴል በበኩሉ ጋዜጣዊ መግለጫዉ የተከለከለዉ ከሆቴሉ ጋር ውል የሌላቸዉ ግለሰቦች መግለጫዉን እንሰጣለን በማለታቸዉ ነዉ ብሏል፡፡

የሆቴሉ ጊዜአዊ የጥበቃ ክፍል ሀላፊ የሆኑት አቶ ስለሺ ተሰማ መግለጫዉ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንደሚሰጥ የተፈፀመ ዉል እንደሌላቸዉ ለአዲስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡

Via ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብሎክ 21 የተማሪዎች ህንፃ ላይ ድንገተኛ እሳት እንደተነሳ ተማሪዎች ጠቁመዋል። የሚመለከታችሁ አካላት አስፈላጊውን ሁሉ እንድታሰርጉ ተጠይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋን ኦሮሞ በሃያ ትምህርት ቤት ሊሰጥ ነው...

በቀጣዩ ዓመት አፋን ኦሮሞ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በሃያ ትምህርት ቤት ለመስጠት መታቀዱን በኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናገሩ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ቁጥሩ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ህዝብ እንደሚኖር የተናገሩት ዶክተር ግርማ፣ በዚህ ዓመት በሃያ ትምህርት ቤት ይሰጣል ተብሎ የታሰበ ቢሆንም፤ ከሰላም መደፍረስ የተነሳ አስር ትምህርት ቤት ብቻ እንዲወሰን መደረጉን ገልፀዋል፡፡ ይሁንና ይህን ቁጥር በቀጣዩ ዓመት ከፍ በማድረግ ወደሃያ ለማድረስ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያና ቤኒሽንጉል ጉምዝ አማካይነት የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ እንዲቋቋም በመደረጉ በኦሮሚያ በኩል የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው በአፋን ኦሮሞ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ትምህርት እንዲሰጥ ማድረግ ያስቻለ በመሆኑ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል፡፡

በዚህ ዓመት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በአስር ትምህርት ቤት በአፋን ኦሮሞ ትምህርት እንዲሰጥ መደረጉ እንደ ትልቅ ስኬት እንደሆነም ዶክተሩ አልሸሸጉም፡፡ ባለፈው በሁለቱ ክልልች የተደረገው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ወቅት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በመሆን ተዘዋውረው ትምህርት ቤቶቹን ማየታቸውን የገለፁት ዶከተር ግርማ፣ የረጅም ጊዜ የነበረው ጥያቄ ተመልሶ ማየት መቻላቸውን ጠቅሰው፤ ትምህርት ቤቱን ያዘጋጁት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መሆኑን ተናግረው፤ የኦሮሚያ ክልል ደግሞ መምህራኑን ወስዶና አሰልጥኖ እንዲያስተምሩ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና...

በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዮካራ በተባለ ቀበሌ ዛሬ ረፋዱ ላይ ከቀኑ 4 ሰዓት በደረሰ የመሬት ናዳ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ።

የወረዳዉ ዋና አስተዳደሪ አቶ እንግዳወርቅ ገነቱ ለfbc እንደገለፁት፥ ሰባት የእደ ጥበብ ባለሙያዎች ሸክላ ለመስራት የሚሆን አፈር ለማዉጣት አፈር በመቆፈር ላይ ሳሉ ነው ናዳው የደረሰው አንዲት ወጣትም ከአደጋው ህይወቷ መትረፉንም ነው ያመለከቱት። ሟቾች ሁሉም ሴቶች ሲሆኑ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸዉ።

በህይወት የተረፈችዉ ወጣት በአሁኑ ሰዓት በአረካ ከተማ በሚገኘዉ ዱቦ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለች ትገኛለች።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ...

"የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነርሲንግ ማስተባበሪያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ምንችል ታምር ለጎ/ዩ/አጠ/ሰፔ/ሆ/ል/ጤ/ሙ/ማህበር እንደገለፁት በአለም አቀፍ እና በሀገራችን ደረጃ የሚከበረውን “የነርሰ ቀንን “ ሰኔ 4/2011 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ይከበራል፡፡ ቀኑም የሚከበረው “የሞያ ትስስር ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል ነው፡፡የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች ማህበር ለሁሉም የሀገራችን ነርሶች እንኳን አደረሳችሁ እንላለን።"

Via Endal Bekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድጋሚ Alert‼️

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ብሎክ 21 የተማሪዎች ህንፃ ላይ ድንገተኛ እሳት እንደተነሳ ተማሪዎች ጠቁመዋል። እስካሁን የደረሰ አካል እንደሌለ እየሰማን ነው። የሚመለከታችሁ አካላት አስፈላጊውን ሁሉ እንድታድርጉ በድጋሚ ተጠይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

አርባምንጭ ከተማ 03 ሰልባጅ ተራ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተነስቷል። የሚመለከታችሁ አካላት ጥቆማው ይድረሳችሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የእሳት አደጋ ደረሰ። በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የደረሰው የእሳት አደጋ ዛሬ ሰኔ 1/2011 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ አካባቢ ጀምሮ ነው።

በወንድ ተማሪዎች መኝታ ቤት አካባቢ በቁጥር 21 እና 27 በሚል ተለይተው የሚታወቁ ሁለት የመኖሪያ ህንፃዎች በእሳቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በአደጋው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለ በስልክ የገለፁት የዩኒቨርስቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አህመድ መሃመድ በተማሪዎች ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ተናግረዋል።

እሳቱን ለማጥፋት ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደርና ከሃበሻ ቢራ ፋብሪካ በትብብር በተገኙ የአደጋ ጊዜ ተሽከርካሪዎች በመታገዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የነገሩን አቶ አህመድ ወደ ሌሎች ህንፃዎች ሳይሸጋገር ለመቆጣጠር እንዲቻል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል። ዳይሬክተሩ የቃጠሎው ምክንያት በውል እንዳልታወቀና እንደሚጣራ አስታውቀዋል።

ሰሞኑን መጠነኛ የተማሪ ግጭቶችን ያስተናገደው ዩኒቨርስቲው በግጭቱ ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው ባላቸው 58 ተማሪዎችን በስንብት በእገዳና በማስጠንቀቂያ መቅጣቱ የሚታወስ ነው።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia