#update አገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናዎችን ከሰኔ 3/2011 ዓ.ም ጀምሮ ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉበሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳሉት የትምህርት ሚኒስቴር ፈተናዎቹን ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል።

ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ተማሪዎች ተረጋግተው በመፈተን የሚጠበቅባቸውን ውጤት እንዲያስመዘግቡ በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላትና መላው ህብረተሰብ የተማሪዎችን ስነ-ልቦና የሚያጠናክሩ ሥራዎችን በመከወን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርኣያ ገ/እግዚአብሄር የዘንድሮ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከሰኔ 03/2011ዓ.ም እስከ ሰኔ 05/2011 ዓ.ም እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ሰኔ 6፣7፣10 እና 11/2011 ዓ.ም እንደሚሰጥ ገልጸው ለ10ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተመዘገቡ ተማሪዎች 1,277,533 እና ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተመዘገቡ ተማሪዎች 322,317 ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዚህ ዓመት ከተማሪዎች ምዝገባ ጀምሮ የፈተና ህትመትና ሌሎችን ጨምሮ እስከ ሥርጭት ያሉ ሥራዎች ከዚህ በፊት ከነበሩት ዓመታት በተሻለ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የተከናወኑ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ አክለው መግለጻቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ዘገባ ያመለክታል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia