TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአማራ ክልል በቁጥጥር ሥር የዋሉ ታራሚዎች "ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት" እንደሚፈጸምባቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ። ይኸ የተገለጸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በክልሉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የእንባ ጠባቂ ተቋም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ካደረገው ጉብኝት በኋላ ነው። ቋሚ ኮሚቴው "ታራሚዎች ያለበቂ ምክንያት ከአንድ ማረሚያ ቤት ወደ ሌላ #ከማዘዋወር ባለፈ አሁንም በክልሉ አንዳንድ ማረሚያ ቤቶች ዘንድ በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ እንደሆነ" ማረጋገጫ ማግኘቱን ምክር ቤቱ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። በታራሚዎች ላይ የሰብዓዊ መብት #ጥሰት ይፈፀምባቸዋል የተባሉ ማረሚያ ቤቶች ግን አልተገለጹም።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ውሎ...

ዛሬ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች #ሰልፎች ተደርገዋል። በአፋር ክልል "ለውጡ ወደ እኛ አልደረሰም" ያሉ ወጣቶች የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ከአዋሽ ከተማ ወጣ ብሎ መንገድ በመዘጋቱ የአዲስ አበባ ጅቡቲ ትራንስፖርት ለሰዐታት ተቋርጦ ነበር። የመንግስት ወታደሮችም ባንክ ቤቶችን በብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ሲጠብቁ ታይተዋል።

#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሊቾ ወሪሮ🔝

በስልጤ ዞን የአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ነዋሪዎች በበኩላቸው መንገድን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ጥያቄ በማንሳት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍኖተሰላም🔝

በአማራ ክልል #ምዕራብ_ጎጃም_ዞን #የፍኖተሰላም ከተማ ነዋሪዎች የመሬት ወረራን #በመቃወም ድምፃቸውን አሰምተዋል።

#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኒፕሲ ሀስል /ኤርምያስ አስገዶም/ን ለመዘከር በትላንትናው እለት በተዘጋጀው የሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት ላይ በተነሳ ረብሻ ከ19 በላይ ስዎች መጎዳታቸውን ፓሊስ ገልጿል። ከባድና ቀላል የመቁስል አደጋ የደረስባቸውም በአንቡላንስ ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

#VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የባልደራስ ምክር ቤት የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄ የለውም!!

ከጋዜጠኛ #እስክንድር_ነጋ መግለጫ በፊት የባላደራ ምክር ቤቱ የአቋም መግለጫ በጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ተነቧል።

በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ መግለጫ እንድትሰጡ መንግስት ፈቅዶላችሁ ነበር። ለምን አልተጠቀማችሁበትም? ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የቀረበለት ጥያቄ ነበር።

መልስ፦

እኛ ቤተመንግስት አንገባም። የህዝብ ድምፅ ነን። ለወደፊቱም ህዝብ መሃል እንጂ ቤተመንግስትም ሆነ ሌላ የመንግስት ተቋም ውስጥ ሆነን መግለጫ አንሰጥም። በሚቀጥለው ምርጫ የመወዳደር ፍላጎት ፈፅሞ የለኝም እንደ አጠቃላይ እራሱ የባልደራስ ምክር ቤት የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄ የለውም። ባቋራጭ ስልጣን ለመንጠቅ የሚባለው ነገር ከንቱ ውንጀላና የተነሳውን የመብት ጥያቄ ለማዳፈን የቀረበ ምክንያት ነው።

Via Nafkot Eskinder
@tsegabwolde @tikvahethiopia