TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

ፍላሚንጎ ከሰንሻይ አጠገብ ከሚሰራው ህንፃ ላይ ሁለት የኮንስትራክሽን ሰራተኞች #ወድቀው አንደኛው ህይወቱ አልፏል። አንደኛው ለህክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል። ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ ይገኛል።

ምንጭ፦ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኦሮሞ ትግል ከየት ወዴት"...

“የኦሮሞ ትግል ከየት ወዴት” በሚል ርዕስ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው። ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኦዲፒ ሊቀመንበር ዶክተር #አብይ_አህመድና የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር እና የኦዲፒ ምክትል ሊቀመንበር #ለማ_መገርሳ ናቸው። በውይይቱ ላይ የኦዲፒ ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ሽመልስ አብዲሳ በርዕሱ ላይ መነሻ ሐሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል። በውይይቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ወጣቶችና ባለሃብቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋምቤላ ነዋሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ‼️

በጋምቤላ ከተማ #ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ሲያዘዋውር ደርሸበታለሁ ያለውን አንድ #ተጠርጣሪ ግለሰብ #በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

በከተማውና አካባቢው የሀሰተኛ የብር ኖት ዝውውር #እየተበራከተ በመምጣቱ ህብረተሰቡ #ጥንቃቄ እንዲያደርግ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጋምቤላ ከተማ ኦፔኖ ቅርንጫፍ አሳስቧል።

በጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የፎረንሲክ ምርመራ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር #ቱት_ኑዑት ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው የልብስ ግብይት ያካሄደባቸው ባለሱቆች የሰጣቸው የብር ኖት ሀሰተኛ መሆኑን ከተረዱ በኋላ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ነው።

ፖሊስ ባካሄደው የማጣራት ስራ ግለሰቡ ለባሱቆች ከሰጣቸው 20 ሺህ ሀሰተኛ ባለ መቶ የብር ኖት በተጨማሪ አንድ ካርቶን ሀሰተኛ የብር ኖት ወደ ወረዳዎች እንደተሰራጨ መረጃ ማግኘቱን ተናግረዋል።

በወረዳዎች የተሰራጨውን ሀሰተኛ የብር ኖት ለመያዝም ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

”በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር በዋለው ግልሰብ ላይ  የምርመራና የማጣራት ስራ እየተከናወን እንደሚገኝ ጠቁመው ሂደቱ እንደተጠናቀቀም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የሚላክ ይሆናል “ብለዋል።

በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ የጋምቤላ ከተማ ኦፔኖ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ግሩም አበራ በበኩላቸው  በጋምቤላ ከተማና አካባቢው በርካታ ሀሰተኛ የብር ኖት ስርጭት  እንዳለ ምልክቶች ስለሚያሳይ ህብረተሰቡ  በግብይት ወቅት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በቅርቡ በአንድ ደንበኛ ወደ ባንኩ ሊገባ ከመጣ 90 ሺህ ባለ መቶ የብር ኖት ውስጥ 20 ሺህው  ሀሰተኛ የብር ኖት ሆኖ መገኘቱንና ጉዳዩንም ለፖሊስ በማሳወቅ እንዲያዝ መደረጉን ገልጸዋል።

ከአሁን በፊት ይገኝ የነበረው የሀሰተኛ የብር ኖት አንድና ሁለት ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ስራ አስኪያጁ በተወሰነ ብር መካከል ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሀሰተኛ የብር ኖት መገኘቱ በርካታ ስራጭት መኖሩን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ግብይት በሚያደርግበት ወቅት በተለይም በብር ኖቶች ላይ ያለውን የዘንግ ምልክቱን በማየት መጠቀም እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ ሰው››

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ "የዐመቱ የአፍሪካ ምርጥ ሰው" ተብለው ተመረጡ፡፡

የአፍሪካ ሊደርሺፕ ሜጋዚን የአውሮፓውያኑ 2018 የአፍሪካ ምርጥ ሰዎችን ምርጫ አካሂዷል፤ በውጤቱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ዐብይ አህመድ አሸንፈዋል፡፡

ዶ/ር ዐብይ በጠቅላላ መራጮች ከተሰጠው ድምጽ ከ85 ከመቶ በላይ ድጋፍ በማግኘት #መመረጣቸውም ታውቋል፡፡

በሰባት ዘርፎች በተደረገው ውድድር 123 ሺህ 446 መራጮች በመጽሔቱ ድረ ገጽ፣ 33 ሺህ መራጮች በመጽሔቱ ማኅበራዊ ገጽ እና ሦስት ሺኅ 400 መራጮች ደግሞ በኢ-ሜይል ድምጽ መስጠታቸውን የዝግጅት ክፍሉ አስታውቋል፡፡

የውድድሩ አሸናፊዎች በመጪው የካቲት ወር አጋማሽ በደቡብ አፍሪካ #ጁሀንስበርግ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ሺልማታቸውን እንደሚቀበሉም ታውቋል፡፡

አሸናፊዎቹም፡-

• የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር ዐብይ አህመድ

• የዓመቱ ምርጥ የአፍሪካ ሴት መሪ ናይጀሪያዊቷ የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄ መሀመድ

• በትምህርት ዘርፍ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ናይጀሪያዊው መሀመድ ኢንዲሚ፣ ኦሬንታል ኢነርጂ

• የዓመቱ አፍሪካዊ ምርጥ ሥራ ፈጣሪና ቀጣሪ ናይጀሪያዊው አቲኩ አቡበከር

• በፖለቲካዊ አመራር የዓመቱ ምርጥአፍሪካዊ የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ

• በበጎ አድራጎትና ለማኅበረሰብ ጉልህ አስተዋጽኦ በማበርከት የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ናይጀሪያዊውቶኒ ኢሉሜሉ፣ ሄይርስ ሆልዲንግ

• የዓመቱ አፍሪካዊ ምርጥ ወጣት የቦትስዋናው የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቦጎሎ ጆይ ኬንወንዶ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

የአፍሪካ ሊደርሽፕ መጽሔት በእንግሊዝ ሀገር ሕጋዊ ዕውቅና ኖሮት የሚታተምና አፍሪካዊ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ለዓለማቀፍ አንባቢዎቹ የሚያስተዋውቅ መጽሔት ነው፡፡ መጽሔቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዓለማቀፍ ኢንቨስተሮች፣ የንግድ ድርጅቶች ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የመንግሥታት ፖሊሲ አውጭዎች፣ ዓለማቀፍ ድርጅቶች ደንበኞች አሉት፡፡ደንበኞቹ በአፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ፣ እስያ፣ አውሮፓና አሜሪካ የሚገኙ ናቸው፡፡ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችም ከ900 ሺህ በላይ ቋሚና የተመዘገቡ ደንበኞች አሉት፡፡

ምንጭ፡- አፍሪካን ሊደርሺፕ ሜጋዚን(በአብመድ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

http://africanleadership.co.uk/breaking-prime-minister-abiy-ahmed-emerges-african-of-the-year-2018/
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች ተያዙ‼️

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በወረጃርሶ ወረዳ ጎሃ-ፂዮን ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችና የኮንትሮ ባንድ እቃዎች ለማዘዋወር ሲሞክሩ የተገኙ  20 ግለሰቦችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ ከህዳር 25/2011 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር  ቀናት  ባካሄድው  ድንገተኛ ፍተሻ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን  በሁለት የቤት መኪናና  በሶስት የነዳጅ መጫኛ  ቦቴ ተሽካርካሪዎች ውስጥ መያዙ ተነግሯሏል፡፡

የጦር መሳሪያዎች  ከጎረቤት ሃገር ገብቶ በአማራ ክልል በኩል ወደ መሀል ሀገር ለማዘዋወር ታልሞ  እንደነበር በድርጊቱ ተጠርጥረው ከተያዙት ግለሰቦች የምርመራ ቃል መረዳት እንደታቻለ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መንግስቱ ከተማ ለኢዜአ ገልጸዋል።

የተያዙት የጦር መሳሪያዎች ሁለት ብሬል መትረየስ፣16 ክላሽኮቭ፣ 43 ኤስኬኤስ ጠመንጃና 3 ሚንቶቭ እንዲሁም 12 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች 200 ከሚደርሱ ተተኳሽ ጥይቶች ጋር መሆኑን  አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ከአንድ ሚሊዮን 500ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው 89 ካርቶን ሽቶና ልዩ ልዩ  ሲጋራዎች  በቁጥጥር ስር  እንደዋለ አዛዡ አስረድተዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ድርጊቱን የሚፈጽሙት የህዝብ በዓላትንና ጨለማን ሽፋን በማድረግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ኢንስፔክተር መንግስቱ እንዳመለከቱት ተጠርጣሪዎቹ ሳናውቅ በአደራ የተቀበልነው እቃ ነው ቢሉም የሚሰጡት መረጃ እርስ በእርሱ የሚጋጭ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት ምርመራው በከፊል ተጠናቆ ፍርድ ቤት የሚቀርቡበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው።

ከተያዙት ተጠርጣሪዎቹ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ግለሰቦችን ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የህግ ባለሙያ  አቶ ኢሳያስ ጥበቡ የትኛውንም የጦር መሳሪያ በብዛትም ሆነ በተናጥል ያለ ፍቃድ መያዝ፣ ማዘዋወር፣ መሸጠና መለወጥ ከገንዘብ ቅጣት እስከ 15 ዓመት እንደሚያስቀጣ በህግ መደንገጉን ገልጸዋል።

እንዲሁም በህብረተሰብ ውስጥ የፀጥታና ያለመተማመን ስጋት እንዲሰፍን ምክንያት ሆኖ ከቀረበ ደግሞ  ቅጣቱ ሊከብድ እንደምችልም አስረድተዋል።

ሌላው የአካባቢው ነዋሪ የኃይማኖት አባት ቀሲስ ኃይለማሪያመ ኪሮስ የጦር መሳሪያ ግጭትን የሚያባባስና ወደ አልተፈለገ ሁኔታ  የሚከት በመሆኑ ዜጎች ለሰላም፣ ለፍቅርና ለመቻቻል ቦታ በመስጠት ወንጀልን መከላከል እንዳለባቸው መክረዋል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለነገ ተላልፏል! በድሬዳዋ ስታዲየም ዛሬ ሊደረግ የነበረው የሰላምና ፍቅር የሙዚቃ ኮንሰርት ለነገ መተላለፉን ለመስማት ተችሏል።

©አክቲቪስር ጃዋር መሀመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርቲስት ሄለን መለስ🛬ባህር ዳር ገባች!

የኤርትራ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ባሕር ዳር ገቡ፡፡ የኤርትራ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ዛሬ ባሕር ዳር ላይ ለሚኖራቸው የሙዚቃ ድግስ ነው አሁን ባሕር ዳር የገቡት፡፡

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹን ናሆም ዩሃንስ እና ሄለን መለስን የያዘዉ ልኡክ ባሕር ዳር ገብቷል፡፡

ልዑኩ ባሕር ዳር ዕለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና አድናቂዎቻቸው አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🙏222,222 TIKVAH-ETH🙏
#Update የአፋር ክልል ምክር ቤት ሰኞ በሚያደርገው አስቸኳይ ጉባዔ #አዲስ የክልል ርእሰ መስተዳድር ይሾማል።

Via-FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia