የጋምቤላ ነዋሪዎች ጥንቃቄ አድርጉ‼️

በጋምቤላ ከተማ #ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ሲያዘዋውር ደርሸበታለሁ ያለውን አንድ #ተጠርጣሪ ግለሰብ #በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

በከተማውና አካባቢው የሀሰተኛ የብር ኖት ዝውውር #እየተበራከተ በመምጣቱ ህብረተሰቡ #ጥንቃቄ እንዲያደርግ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጋምቤላ ከተማ ኦፔኖ ቅርንጫፍ አሳስቧል።

በጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና የፎረንሲክ ምርመራ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር #ቱት_ኑዑት ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው የልብስ ግብይት ያካሄደባቸው ባለሱቆች የሰጣቸው የብር ኖት ሀሰተኛ መሆኑን ከተረዱ በኋላ በሰጡት ጥቆማ መሰረት ነው።

ፖሊስ ባካሄደው የማጣራት ስራ ግለሰቡ ለባሱቆች ከሰጣቸው 20 ሺህ ሀሰተኛ ባለ መቶ የብር ኖት በተጨማሪ አንድ ካርቶን ሀሰተኛ የብር ኖት ወደ ወረዳዎች እንደተሰራጨ መረጃ ማግኘቱን ተናግረዋል።

በወረዳዎች የተሰራጨውን ሀሰተኛ የብር ኖት ለመያዝም ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

”በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር በዋለው ግልሰብ ላይ  የምርመራና የማጣራት ስራ እየተከናወን እንደሚገኝ ጠቁመው ሂደቱ እንደተጠናቀቀም ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የሚላክ ይሆናል “ብለዋል።

በኢትዮጰያ ንግድ ባንክ የጋምቤላ ከተማ ኦፔኖ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ግሩም አበራ በበኩላቸው  በጋምቤላ ከተማና አካባቢው በርካታ ሀሰተኛ የብር ኖት ስርጭት  እንዳለ ምልክቶች ስለሚያሳይ ህብረተሰቡ  በግብይት ወቅት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በቅርቡ በአንድ ደንበኛ ወደ ባንኩ ሊገባ ከመጣ 90 ሺህ ባለ መቶ የብር ኖት ውስጥ 20 ሺህው  ሀሰተኛ የብር ኖት ሆኖ መገኘቱንና ጉዳዩንም ለፖሊስ በማሳወቅ እንዲያዝ መደረጉን ገልጸዋል።

ከአሁን በፊት ይገኝ የነበረው የሀሰተኛ የብር ኖት አንድና ሁለት ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ስራ አስኪያጁ በተወሰነ ብር መካከል ብቻ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሀሰተኛ የብር ኖት መገኘቱ በርካታ ስራጭት መኖሩን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ ግብይት በሚያደርግበት ወቅት በተለይም በብር ኖቶች ላይ ያለውን የዘንግ ምልክቱን በማየት መጠቀም እንዳለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢ.ዜ.አ
@tsegabwolde @tikvahethiopia