TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አዲስ አበባ🔝

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህገ-ወጥነትን በምንም መልኩ #እንደማይታገስ ገለጸ።

አስተዳደሩ ያለ ልማት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎችን የቆርቆሮ አጥር ማንሳት መጀመሩን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በቅርቡ የህዝብና የመንግስት ውስን ሃብት የሆነውን መሬት ለበርካታ ዓመታት ያለ ልማት አጥረው በቆዩ ባለሀብቶች ላይ #እርምጃ መውሰዱ ይታወቃል፡፡

ባለሃብቶቹ አጥረው ካስቀመጡት ቦታ ላይ ንብረቶቻቸውን እንዲያነሱ ከአንድ ሳምንት በፊት መግለጫ ቢሠጥም ንብረቶቻቸውን ለማንሳት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።

በዚህም ምክንያት የከተማ አስተዳደሩ ህግና ሥርዓትን የማስከበር ኃላፊነትነቱን የመወጣት እርምጃ በዛሬው ዕለት መውሰድ መጀመሩን ጠቁሟል።

በዚህም የከተማዋ መሬት ልማት ማኔጅመንት ፅህፈት ቤት፣ የደንብ ማስከበር ፅህፈት ቤት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ የአጥር ቆርቆሮዎችን ማንሳት ጀምረዋል ነው የተባለው፡፡

አስተዳደሩ የህዝብን ሃብት ለተገቢው ልማትና የነዋሪዎች ተጠቃሚነት እንዲውል በጀመራቸው ተግባራት ህገ-ወጥነትን እንደማይታገስና ህግ የማስከበር ሃላፊነቱን እንደሚወጣ በመግለጫው ጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሁኑ እርምጃዬ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የጀመርኳቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች አካል ነው ሲልም አክሏል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የቢቢሲ የአፍሪካ የ2018 የአመቱ ምርጥ ተጫዋች አምስት እጩዎች ትናንት ይፋ ተደርገዋል፡፡ የዚህ አመት እጩዎችም መህዲ ቤናሺያ ከሞሮኮ፤ ካሊዱ ኩሊባሊ እና ሳይዶ ማኔ ከሴኔጋል፤ ቶማስ ፓርቴ ከጋና እንዲሁም ሞሀመድ ሳላህ ከግብጽ ሆነዋል፡፡ለእጩዎቹ የድምጽ አሰጣጥ ስነስርዓቱ ቅዳሜ እለት የተጀመረ ሲሆን እንደ አውሮፓዉያኑ እስከ ታህሳስ ሁለት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ የድምጽ ውጤት ምርጫው በተጠናቀቀ በአስራ ሁለተኛው ቀን ይታወቃል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ ስፖርት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለወጣቶች እና ተማሪዎች‼️

ውድ የኢትዮጵያ ልጆች የጥፋት ሀይሎች መጠቀሚያ እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ። በተለያዩ ምክንያቶች የትምህርት ተቋማት ውስጥ እጃቸውን ሰደው ሀገሪቷን ዳግም ውጥረት ውስጥ ለመክተት የሚሞክሩ ትንንሽ አሳዎች አሉ እነዚህም በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚለዩ እምነታችን ነው።

ተማሪዎች እና ወጣቶች በሰከነ መንገድ ትምህርታችሁን ትከታተሉ ዘንድ መልዕክታችን እናቀርባለን።

አንዲት ድሀ እና የመጨረሻ ድሀ ሀገር ነው ያለችን የዚህችን ሀገር ታሪክ የምንቀይረው በረባው ባልረባው አዲስ ነገር እየፈጠርን አይደለም።

ሀገር ምትቀየረው በስራ እና በትምህርት ብቻ ነው። ዘላለም አመማችንን የአለም ማፈሪያ ሆነን እንዳንኖር ጠንክረን እንስራ።

የማንም የፖለቲካ ደላላ መጠቀሚያ እንዳትሆኑ! እነሱ ችግር ቢፈጠር ነገ #ፈርጥጠው የሚሄዱበትን መንገድ አመቻችተው ነው እናተን የሚቀሰቅሱት ስለሆነም እኚህን የጥፋት ሀይሎች ከመከተለ ተቆጠቡ።

መንግስት ትልልቆቹ አሳዎች እንደያዘው በየመንደሩ ያሉትን ትንንሽ አሳዎች አድኖ የመያዝ ስራ ላይ መበርታት አለበት።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
የድህነት ታሪካችንን በትምህርት እና በስራ እንቀይር!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dessie🔝

GLOBAL ENTERPRENEURSHIP WEEK WAS CELEBRATED AT Dessie Golden Gate Hotel. The Celebration was Conducted by mutual Sponsorship of Enterpreneurship Development Center Ethiopia (EDC) and Wollo University:

🔹workshops , papers and traingis and Open Discussions were part of the program

🔹Young Enterpreneures were invited from Amahara Region

🔹Wollo university Staffs who have been working in Technology transfer were also partcipants of the Workshop and Training.

©Wube
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንጎለላና ጠራ ወረዳ‼️

በአንጎለላና ጠራ ወረዳ #ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከመንግሥት ካዝና ከ466 ሺህ ብር በላይ ለግል ለጥቅሟ ያዋለችው ግለሰብ በ18 ዓመት ጽኑ እሥራትና የገንዘብ ቅጣት ተጣለባት።

በሰሜን ሸዋ ዞን ፍርድ ቤት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ወይዘሪት ዘርትሁን ያዘው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ፍርድ ቤቱ በግለሰቧ ላይ ቅጣቱን የወሰነው በወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽህፈት ቤት ገንዘብ ያዥ ሆና ስትሰራ የመንግሥትን ገንዘብ ለግል ጥቅሟ ማዋሏ በመረጋገጡ ነው።

ተከሳሿ ወይዘሮ #አበበች_ጽጌ ከ2007 እስከ 2009 ዓ.ም ድረስ በጽህፈት ቤቱ ስትሰራ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀትና መንግሥታዊ ሰነድ በመደበቅ የሙስና ወንጀል መፈፀሟ በሰውና በሰነድ ማስረጃ እንደተረጋገጠባትም አስረድተዋል።

ግለሰቧ በአገር አቀፍ ደረጃ በውሃና በአካባቢ ንጽህና ፕሮጀክት (ዎሽ) ግዢ ከአቅራቢዎች ላይ የተሰበሰበ ሁለት በመቶ ገንዘብ 171ሺህ 417ብር ለግል ጥቅም ማዋሏ ተረጋግጦባታል ነው የተባለው።

እንዲሁም በ56 ደረሰኞች ላይ በበራሪው ትክክለኛዉን የገንዘብ መጠን በመመዝገብና የከፋዮችን ስም በመቀያየር የገቢ መጠኑን በመቀነስ ለመንግሥት መግባት የነበረበት 94ሺህ 90 ብር ሰነድ በማበላለጥ መጠቀሟም ነው የተገለፀው።

በተጨማሪም በራሪ ደረሰኞችን ለከፋይ በትክክል ቆርጣ ከሰጠች በኋላ በሁለተኛና ሦስተኛ ካርኒዎች ላይ አቀናንሳ 181ሺህ 16 ብር ለግል
ጥቅማቸው ማዋላቸው መረጋገጡን ባለሙያዋ ገልጸዋል።

ግለሰቧ ወንጀሉን ከፈጸሟ በኋላ ከአካባቢው በመሰወሯ ፖሊስ ወንጀለኛዋን አድኖ በመያዝ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብም ትዕዛዝ
ተሰጥቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለአምስት ዓመታት ከማንኛውም የእንቅስቃሴ መብቷ እንደታገደችም ተወስኖባታል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-AID 2🔝በዚህ መልኩ ነው የየቀኑን የገንዘብ እንቅስቃሴ ለህዝብ ይፋ የሚደረገው። ይህ በ @tikvahaid2 በሚል እና በተከፈተው የግል አካውንት እየተሰራ ያለ ስራ ነው። አባላት በጠየቁት መልኩ እና ከፍተኛ ሀላፊነት እና እምነት ጥለውበት የሚሰራ ስራ ነው።

🔹የመጀመሪያው ድጋፍ #በአፋር ሎጊያ ለሚገኘ አንድ የ17 አመት ትዳጊ #እናት የሚውል ነው። ቻናሉን ተቀላቅላችሁ ያለውን እያንዳድዷን እንቅስቃሴ መከታተል ትችላላችሁ። ድጋፉ 15,000 ብር ለማድረግ ሲሆን አሁን ላይ 5,547 ብር ተገኝቷል።

ነገ ይጠናቀቃል ይህ ዘመቻ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና-አብዴፓ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና ከአፋር ብሔራዊ ዲሞክራሲዊ ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አመራር ጋር ባለፈዉ ሳምንት የጀመሩትን ዉይይት ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀጥለዋል፡፡

በዚህ ዉይይት በአገር አቀፍ ደረጃ በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ በክልል ደረጃ እንዴት መካሄድ እንዳለበት ትኩረቱን ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱ መጨረሻ ለውጡን የበለጠ ለማሳካት እንዲቻል ነባር የፓርቲ አመራሮች በአዲስ አመራሮች #እንዲተኩ ተወስንዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የክልሉን ሰላምና ፀጥታ በበለጠ #በማጠናከር ህዝቡ የልማት ተጠቃሚነቱን የበለጠ ለማረጋገጥ እንዲቻል ሁሉም አመራር በጋር ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በሌላም በኩል የክልሉን ወጣቶችን ይበልጥ በማሳተፍ የህዝቡን የልማትና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች ለመመለስ አመራሮቹ ቃል ገብተዋል፡፡

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዴፓ‼️

የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) በቅርብ በሚያካሄደው ድርጅታዊ ኮንፊረንስና ጉባዔ በአገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴን በክልሉ  ለማስቀጠል ብቃት ያላቸው #ወጣት አመራሮችን እንደሚመርጥ ተገለጸ።

ፓርቲው በክልሉ የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ ላለፉት ሶሰት ቀናት በአዲስ አበባ ያካሄደውን ጉባኤ መሰረት በማድረግ  ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በዚህም ለለፉት ሶስት ቀናት ባደረጉት ግምገማ የለዩትን ችግሮችና ያስቀመጡትን የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

በሚኒስትር ማዕረግ የኢህአዴግ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አጋር ድርጅቶችና የሲቪል ማህበራት አስተባባሪ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ከውይይቱ በኋላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳሉት  ፓርቲውና የክልሉ መንግስት ከፍተኛ የአመራር ውድቀት እንዳጋጠመው በግምገማ ተለይቷል።

ከዚህም በተጨማሪ በአመራሩ መካከል ተወያይቶ መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ ከፍተኛ የሆነ የስልጣን ሽኩቻ፣ የክልሉን ሃብት ለህዝብ ጥቅም ከማዋል ይልቅ በኔትዎርክ ተደራጅቶ ለራስ ጥቅም የማዋል ችግርም መኖሩን ነው የገለጹት።

ለዚህም በጨውና ሌሎች በክልሉ ባሉት ማዕድናት ላይ የሚሰራ የማጭበርበር ስራም ጎልቶ መታየቱን በማከል።

የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችም በክልሉ አስተዳደር ላይ እንደሚታይም ተገምግሟል ብለዋል አቶ ፍቃዱ።

ከነዚህ ችግሮች ለመላቀቅም የተከሰቱትን ችግሮች ማስተካከል የሚችሉ አሰራሮች መዘርጋትና የአመራር ለውጥ ማድረግም እንደ መፍትሄ ተቀምጠዋል።

የክልሉ ፕሬዝዳንት ሃጅ ስዩም አወል በበኩላቸው እሳቸውን ጨምሮ በድርጀቱ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ ከፍተኛ አመራሮች ስልጣን ለቀው ወጣቶች እንደሚተኩ ተናግረዋል።

ይህን ለማድረግም በቅርቡ የአባላት ኮንፊረንስ እንደሚያደረጉና የፊታችን ህዳር 24 በሚካሄደው ድርጅታዊ ጉባዔም የክልሉን ህዝብ ፍላጎት የሚመጥን ለውጥ የሚያመጣ ውሳኔዎች ይታላለፋሉ ብለዋል።

እስከዚያው ደግሞ ህብረተሰቡ አካባቢውን እየጠበቀ በትዕግስት እንዲጠብቃቸው ጥሪ አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም ፓርቲው አጠቃላይ ሪፎርሙንና የአመራር መተካካትን ሲያካሄዱ ከግልኝነትና ቡድናዊ ስሜት ጸድቶ የህዝቡን ጥቅም ባማከለ መልኩ እንዲሆን አሳስበዋል።

የፌዴራል መንግስቱም አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል።

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update በአፋር ክልል ሰመራና ሎጊያ ከተሞች በኢንቨስትመንት ስም የመሬት #ወረራ እየተፈፀመ ነው፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia