TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያዳምጠው የሚገባ🔝

ሳምቡሳ ጠባሹ ሶርያዊ ስደተኛ በኢትዮጵያ፣ በሸገር ከልዩ ወሬፕሮግራም ቀርቦ እንዲህ አለ::

“የእኔ ሐገር ሶርያስ #ፈርሳለች#ቆንጆ ሐገር አላችሁ፤ ሐገራችሁን ጠብቋት”…ሶርያዊውን ሙዙሪ ጉድሃን አል ሙድሉሽ ከሐገሩ ያስወጣው አሰቃቂው የሶርያ ጦርነት ነው ኢትዮጵያ ያመጣው ደግሞ ፍቅር !

አዎ ፍቅር ! የሶርያን መፍረስ ተከትሎ ሐገር ለሐገር ሲዞር ሊባኖስ ደረሰ፡፡ እዛም ከአንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት ጋር ተዋድዶ ኢትዮጵያ ይዛው መጣች፡፡ “ምርጥ ሐገር…” ይላል፣ “በተለይ አየራችሁ ሲያምር…”

አዲሱ ገበያ ታክሲ ተራው ጋር መሸትሸት ሲል ሳምቡሳ ይጠብሳል፤ የሐገሩን ጣፋጮችም ይሸጣል፡፡ ከኢትዮጵያዊት ሚስቱ አንድ ልጅ ወልዶ አብረው እየኖሩ ነው፡፡ ሳምቡሳ እየጠበሰ፣ ጣፋጭ እየሸጠ ሚስቱን እና ልጁን ያስተዳድራል፡፡ አማርኛ ጥሩ ይናገራል፡፡ በ3 ወር ነወ የለመድኩት ይላል፡፡ ማንበብም ይችላል፡፡ መፃፍ እየሞከርኩ ነው ይላል፡፡ ሐማ የምትሰኘው የሶርያ ከተማ ውስጥ ነበር የሚኖረው፡፡ በአረብኛ ሥነፅሁፍ የመጀመሪያ ዲግሪ አለው፡፡ ምን ዋጋ አለው - የሶርያ ጦርነት ሲቀሰቀስ ሁሉም ነገር በንኖ ጠፋ፡፡

በጦርነቱ አንድም ዘመድ አልተረፈውም፡፡ በዚህች ምድር ያሉኝ ዘመዶቼ ኢትዮጵያዊቷ ባለቤቴ እና ልጄ ናቸው ይላል፡፡ የበርካታ ሙያዎች ባለቤት የሆነው ሶርያዊው ሙዙሪ ጉድሃን አል ሙድሉሽ፣ ከ250 በላይ ምግቦች መስራት እችላለሁም ነው የሚለው… ከምንም በላይ ግን ለኢዮጵያውያን የሚያስተላልፈው መልእክቱ ይህ ነው - “ሰላም ከሌለ ምንም ነገር የለም…”

ምንጭ:-ሸገር FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች🔝በትላንት ዕለት በተካሄደው #ታላቁ_ሩጫ_በኢትዮጵያ ላይ ከታዩት የፍትህ ጥያቄዎች አንዱ ነው። "ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ🔝

የአማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤቶች የጋራ #ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ በአጎራባች ወረዳዎች ዘላቂ ሰላም ለመፈጠር፣ ችግሮች ሲያጋጥሙ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት እና በፖለቲካዊ ዘርፎችም በጋራ ለመሥራት ስምምነቱ ተፈርሟል ነው የተባለው።

ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ፣ አሠራሮችን በማሻሻል ለወከሉት ሕዝብ በግልጽነትና በተጠያቂነት ለማገልገል፣ የተጀመረውን ለውጥም አጠናክሮ ለማስቀጠል ነው ስምምነቱን የአማራና ቤኒሻንጉል ክልል ምክር ቤቶች ትላንት የተፈራረሙት፡፡

የጋራ መድረክ በመመሥረትም በዓመት ሁለት ጊዜ እየተገናኙ ለመምከር ምክር ቤቶቹ ስምምነት አድርገዋል፡፡ ስምምነቱ አንድ የጋራ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚደረገውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
🇪🇹| ወደ ኢትዮጵያ በቀላሉና በርካሽ ዋጋ መደወል ይፈልጋሉ?

የRingAround Appን በስልካችሁ ላይ ጫኑ!
ዛሬውኑ ሲጭኑት
በሰሜን አሜሪካ $2 የመደወያ ዶላርን በነፃ እንሰጣለን!
በአውሮፓና በአውስትራልያ $1 የመደወያ ዶላርን በነፃ እንሰጣለን!

ለመጫን --> https://ringaround.lpages.co/et-tikvah-downloadringaroundapp
ዋሽንግቶን ዲሲ🔝በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮዽያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን "ለቤተክርስቲያን አንድነት ላደረጉት ጥረት" #ዕውቅና ሰጥቷል።

ምንጭ:- ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ🕊ሲዳማ!

ትናንት "ፍቅር በደልን አይቆጥርም " በሚል መርህ በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚያግዝ የዕርቅና
የሰላም ኮንፈረንስ በሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል አዳራሽ ተካሂዷል።

በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የደኢህዴን ሊቀ መንበርና የኢፌደሪ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወይዘሮ #ሙፈሪሀት_ካሚል፥ በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል ሰላም ሰፍኖ ዕርቅና የሠላም ኮንፈረንስ እንዲካሄድ ትልቅ አስተዋፅኦ የነበራቸውን አባቶች አመስግነዋል፡፡

ሰላም በእያንዳንዳችን ልቦና እና ቤት የሚገኝ በኛው ጥበቃ የሚጎለብት በመሆኑ ልንጠብቀው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ወጣቶች ሰላምን ከሚያደፈርሱ ቆስቋሽ ድርጊቶች እንዲጠበቁም አሳስበዋል፡፡

በዕርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ ከሲዳማና ወላይታ ዞን የተወጣጡ የኃይማኖት መሪዎችና አባቶች፣ ከሁለቱም ዞኖች የተወጣጡ የባህል ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ arts tv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🔝

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ላይነር በባሕር ዳር ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ላይነር በባሕር ዳር ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

አምባሳደሩ ከባሕር ዳር ከንቲባ ከሙሉቀን አየሁ ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይታቸውም ሶስት አበይት ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ፣በጣና ላይ የተጋረጠው እንቦጭ እና በግንባታው ዘርፍ ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ እንዲመጡ ምን መደረግ እንዳለበት ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ማይክል የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ፣በክልሉ መስህቦች ላይ በተጋረጡ ጉዳዮች እና ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ እንዲመጡ ከአቻ አሜሪካ ከተሞች ጋር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡ ቅርሶች ላይ አሜሪካ እየሰራች ነው፡፡ በቀጣይም እቅዷን ይፋ እንደምታደርግም ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ማይክል ራይነር ዛሬ ከሰዓተ በኋላ ደግሞ በባሕር ዳር የሚገኘውን የገነሜ ቤተመጽሀፍትን ይጎበኛሉ፡፡ቤተመጽሀፍቱም በኢምባሲው ወጪ እድሳት ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አምባሳደር ማይክል ራይነር ዛሬ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ማይክል ራይነር አምባሳደር ሆነው ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝት ያደረጉት ባሕር ዳር መሆኑ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegawolde @tikvahethiopia